Leave a comment

በአበበ ገላውና በቤተሰቦቹ ላይ ሽብርና ፍርሃት ለመፍጠር የሞከረው የህወሃት ጀሌ ተጋለጠ


(አዲስ ቮይስ) በጋዜጠኛ አበበ ገላው እና በቤተሰቡ ላይ  ህገወጥ በሆነ መንገድ  በተከታታይ ስልክ በመደወል ሽብርና ፍርሃት ለመፍጠር  የሞከረው ግለሰብ ማንነት ተጋለጠ።

ጋዜጠኛ አበበ ገላው የግለሰቡን ማንነት ለማጣራት ለበርካታ ሳምንታት ጥንቃቄ የተሞላበት ክትትልና ምርመራ መደረጉን  እና ድምጹም  ልምድ ባላቸው የፎረንሲክ ኤክስፐርቶች የተመረመረ መሆኑን ገልጾ በዚሁ መሰረት ይህን ህገወጥ የሆነ ድርጊት ሲፈጽም የነበረው ግለሰብ ሙሉጌታ ካህሳይ የተባለ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ጀሌ መሆኑእንደተደረሰበት  ገልጿልግለሰቡ በተለይ በአለፈው ወር ላይ ወደ ኢሳት ሬድዮ የአድማጮች መልእክት መቀበያ በመደወል በተለይ ለጋዜጠኛው በተወው መልእክት ደምህን እንጠጣለን እንዲሁምቤተሰቦችህን እንፈጃለን፣ በአዲስ አበባ ያለህን ቤት እናቃጥላለን የሚሉ ሁለት ተከታታይ መልእክቶችን አስቀምጦ እንደነበር ታውቋል።

አበበ ገላው “ምንም እንኳን የሚቃጠል ቤት እና ንብርት ባይኖረኝም ከእኔ ስላማዊ የትግል እንቅስቃሴ  እና የጋዜጠኝነት  ስራ ጋር በተያያዘ ምንም በማይመለከታቸውን ደካማ ዜጎች ላይ ወንጀል ለመፈጸም መዛት የህወሃቶችን  አስነዋሪ ድርጊት ብቻ ሳይሆን የሞራል ዝቅጠት የሚያሳይ ድርጊት ነው ፣” ሲል ድርጊቱን አጥብቆ አውግዟል።

በትርፍ ሰአቱ በታክሲ መንዳት ስራ የሚተዳደረው እና ለበርካታ አመታት በለደን ቀንደኛ ከሚባሉት የወያኔ ተወካዮች አንዱ የሆነው ሙሉጌታ ካህሳይ አምስት የሚሆኑ የማስፈራሪያና የግድያ ዛቻ ያዘሉ መልእክቶችን ያስተላለፈ ሲሆን በተደጋጋሚ ጋዜጠኛው በቀድሞው ጠ/ሚ  መለስ ዜናዊ ላይ  ያሰማውን ተቃውሞ በመጥቀስ “የሞት ቅጣት ይገባሃል” ማለቱን ለማወቅ ተችሏል። በእንግሊዝ አገር ደቡባዊ የለንደን ክፍ ል የሚኖረው ሙሉጌታ ካህሳይን በህግ እፋረደዋለሁ እንዲህ አይነት ህገወጥ ሽብር ፈጠራ ፈጽሞ በቸልታ መታየት አይገባውም በማለት አበበ ገላው ተናገሯል።

ግለሰቡ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ባስተላለፈው  አንድ መልእክት የሚከተለውን ተናግሯል፤ “ደምህን እነደምንጠጣው ልነግርህ ነው። በድጋሚ በአዲስ አበባ  ቤት እንዳለህ ደረሰነበታል። እናቃጥለዋለን፣ ቤተሰቦችህን፣ አንተንም እነገድላችዃለን። ላደረከው ነገረ የሞት ቅጣት ይገባሃል፣ በርግጠኝንተ እነጨርሳሃለን። እመነኝ አንለቅህም። የፈለገ ያህል ግዜ ይውሰድ፣ አነተን ቤተሰብህን አንድ ባነድ እናድናችኻሃለን። ቤቶችህንም በቅርቡ እናጋያቸዋለን።”

በሌላ መልእክት ደ ግሞ “እያንዳንዱን እርምጃህን እየተከታተልን ነው። አንተና ቤተሰብህን እናጠፋችሃልን።አንድ ቀን እነጨርስሃለን። የወሰደውን ግዜ ይወሰድ ደምህ በመንገድ ሲፈስ እናያለን። ወይ አንተ ወይ ቤተሰብህ መወገድ አለባችሁ።” በማለት ሽብርና ፍርሃት ለመፍጠር መሞከሩን ለማወቅ ተችሏል።

አበበ ሙሉጌታ ካህሳይ ከብዙዎች አንዱ መሆኑን ጠቅሶ ህወሃቶች በአገር ቤት የሚያደርሱትን ሽብር ፈጠራ በስደት በምንኖርበት የነጻነት ምድር ፈጽሞ ሊፈጽሙት አይገባም ለዚህም ህዝባችን በያለበት በህብረት መነሳት ይገባዋል በማለት ጥሪውን አቅርቦ የጉዳዩን ዝርዝር ከዚህ ዜና ጋር ከተለቀቀው ቪድዮ መረዳት ይቻላል በማለት አስረድቷል።

ጋዜጠኛ አበበ ገላው ዛቻና ሽብር እኔንም ሆነ ለነጻነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊያንን ፈጽሞ እንደማያዘናጋ የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪካዊ ጠላቶች የሆኑት ህወሃቶች ሊረዱ ያስፈልጋል ብሏል።

Poated by: Kumilachew

http://freedomofspeech4.wordpress.com/2013/02/04/639/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: