Archive | January 2018

You are browsing the site archives by date.

ልብ በይ አፍሪካ


ልብ በይ አፍሪካ አፍሪካ ቀና በይ ንቂ ከእንቅልፍሽ ራስሽን ቻይ መሰደድ ይብቃሽ ሀብት ሞልቶ ተትረፍርፎ በአህጉርሽ ብዙ ማዕድናት አምቀሽ ይዘሽ ወርቁ አልማዙ ብሩ ታምቆ ሆድሽ ዛፍና ቅጠሉ ቡናው ፍራፍረው ሞልቶ ከጓሮሽ ታዲያ ምን ጎሎሽ ነው ስደት ያማረሽ የቆጥ አውርድ ብላ ጥላ የብብትዋን የሰው ስታሳድድ አስቀምጣ የራስዋን ዓለም ላይ በተነች ውድ ልጆቹዋን ያልተነካ እምቅ ሀብት ይዛ በጉያዋ ለልጆችዋ […]

መግለጫ በወልዲያ እና በሌሎች አካባቢዎች


ሰሞኑን በጥምቀት በዓል አከባበር እና በተከታታይ ቀናት በወልዲያ እና በሌሎች አካባቢዎች በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች በተወሰደ ህገወጥ ርምጃ ምክንያት የሰላማዊ ዜጎች ህይወት መጥፋቱን አስመልክቶ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ሕብረት የተሰጠ መግለጫ በየትኛውም ሀገር ሃይማኖታዊም ሆኑ ባህላዊ የአደባባይ በዓላት በሰላም ይጠናቀቁ ዘንድ መንግስት ተገቢውን ጥበቃ ሊያደርግላቸው እንደሚገባ ይታወቃል። በሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ በርካታ በዓላትን ለዓመታት ሕዝብ ወደ አደባባይ በመትመም በሰላም እያከበረ ወደቤቱ ሲመለስ ኖሯል። በዓላትን ለማክበር ወደ አደባባይ የሚወጡ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ህዝቦች ለዘመናት በአምባገነን መንግስታት ይደርስባቸው የነበረውን በደል በየበዓላቱ ላይ በዜማ ሲገልፁ መቆየታቸውን ማንም የሚያውቀው እውነት […]

የሀገር ኩራት


የሀገር ኩራት ጦረኛ መጥቶብኝ የዛሬ መቶ ዓመት ህዝቤን አሰልፌ ከፈለኩኝ መስዋዕት ወገን ለመታደግ ለካፋ ነፃነት ግን ምን ያደርጋል ጊዜ ጣለኝና እጃቸው ገባሁኝ ታሰርኩ በካቴና ተሸንፌ ሳይሆን በሸዋ መኳንንት እጄ የታሰረው በወርቅ ሰንሰለት ከራሴ ላይ ዘውዱም ቢወሰድ በጉልበት አልተንበረከኩም ለሚኒልክ መንግሥት እኔም አንተም ንጉሥ ማንበላለጥ ግብር አልገብርም እጄንም አልሰጥ ብሎ የመለሰ በኩራት በድፍረት ጋኪ ሻረቾ ነው የካፋ […]

ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረት እና ከጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር የቀረበ ጥሪ


ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረት እና ከጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር የቀረበ ጥሪ የተከበራቹ የኢትዮጵያ ህዝቦች፣ በሃገራችን ላይ እየደረሠ ያለውን ጭቆናና የግፍ አገዛዝ በመቃወም በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር በመደራጀት በትግል ላይ የምትገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ። ለ26 ዓመታት በወያኔ መንግስት የግፍና የጭቆና ቀንበር አገዛዝ ሥር በመውደቅ ለበርካታ የሰብአዊና የዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች የተጋለጠው የኢትዮጵያ ህዝብ ተቃውሞውንና እንቢተኝነቱን በሃገሪቱ አራቱም አቅጣጫዎች […]

የነፃነት ትግል ጥሪ


የነፃነት ትግል ጥሪ በረዥሙ ታሪክህ በአስተዳደር ጥበብ፣ በጀግንነትህና በተፈጥሮ ሀብትህ የምትታወቀው ውድ የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች እና ማጂ ህዝብ ሆይ ምንም እንኳ ባለፉት ተከታታይ መንግስታት በደረሰብህ ግፍ፣ ጭፍጨፋ፣ ጫና እና በደል አንገትህ ደፍተህ ለመኖር ብትገደድም አሁን የግፍ ፅዋ ሞልቶ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ እህቶችህና ወንድሞችህ ጨቋኙን ሥርዓት ለማስወገድ የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም መጪው ሥርዓት […]

የደኢሕዴን ዝምታ ሚስጢሩ ምን ይሆን?


የደኢሕዴን ዝምታ ሚስጢሩ ምን ይሆን? የህወሃት የትግል ታሪክ እንደሚያስረዳን ከሆነ የትግራይ ህዝብ የነፃነት ጥያቄ ለመመለስና ነፃ ለማውጣት ቢሆንም ወዳጆቻቸው በነበሩ ባለፈርጣማ ክንድ ሃገራት ድጋፍና ጣልቃ ገብነት በለስ ቀንቶአቸው የደርግ መንግስት (አገዛዝ) እንደተገረሰሰ ኢትዮጵያን የማስተዳደር ሥልጣን ቁንጮ ላይ ሊወጣ ችሏል። ህወሃትም በትረ ሥልጣኑን ከጨበጠ ከዓመታት በኋላ በአመራሩ መካከል የተፈጠረው መፈረካከስና ቡድንተኝነት ተከትሎ የአንደኛው አንጃ አቀንቃኝ ነው […]

ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨቱ የወያኔ ሤራ በከፋ፣ ቦንጋ ከሸፈ


ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨቱ የወያኔ ሤራ በከፋ፣ ቦንጋ ከሸፈ በዓለማችን ላይ ለሰው ልጅ የዕለት ተዕለት ኑሮ በአስፈላጊነታቸው ከታወቁ መሠረታዊ የምግብና መጠጥ ፍላጎቶች ባሻገር ማህበራዊ መስተጋብርን በመፍጠርና በማጠናከር አብዛኛዎቹ የዓለም ሀገራት ህዝቦች ራሳቸውን ከድብርትና ከድካም የምያላቅቁበት ምናልባትም ትልልቅና ባለ ብርቱ ክንዳማ ሀብታም ሃገራትን አብላጫውን የሀብት ሚዛናቸውን በማጦዝ የሚታወቀው አረንጓዴ ወርቅ ቡና ስለመሆኑ ብዙዎችን የሚያስማማ ነው ዘርና ሃይማኖት ሣይለይ የጾታ […]

የእናት ሀገር ጥሪ


የእናት ሀገር ጥሪ ነቃ በሉ ልጆች ምንድነው ዝምታው ቀስቅስ ወንድምህን ወቤ ወቤ በለው ከሰሜን አማራ ከኦሮሚያ ቄሮ እየተጣራ ነው በአንድነት አብሮ ቡሾ ቤቶ ጩሎ እያለ ሲጣራ ፋኖ ከቄሮ ጋር አብሮ እያቅራራ አለሁኝ በልና ተነስ ተቀላቀል ከትግሉ ጎራ ከፋ፡ ሸካ፡ ማጂ፡ በንች፡ ደቡብ መልስ ስጡ ድምጻችሁ ይሰማ ዝምታ አያዋጣም እናት ሀገር ታማ የምች መድሀኒት ካለ ከጓሮአችሁ ፈጥናቹ ድረሱ […]

ከደቡብ-ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ኅብረት እና ከጋምቤላ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ አንድነት በሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የተሰጠ መግለጫ፤


ከደቡብ–ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ኅብረት እና ከጋምቤላ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ አንድነት በሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የተሰጠ መግለጫ፤ እንደሚታወቀው የህወሓት–ኢሕዴግ መንግሥት ባለፉት 26 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ተፈናጦ የአፈና፣ ጭቆና፣ ብዝበዛና ግድያ ቀንበሩን በመጫን የዜጎችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ከመርገጥ አልፎ ለዘመናት ገንብቶት የኖረውን አብሮነትና የመቻቻል ባህል በብሔር ተኮር ፖለቲካ በመተካት የዘር ጥላቻ እንዲነግሥና ሃገሪቱ ወዳልተፈለገ አቅጣጫና ብተና እንዲሁም ወደ […]