Leave a comment

የከፋ ሕዝብ እናት መካን አትሆንም


የከፋ ሕዝብ እናት መካን አትሆንም!
ከአናሞ

አባቶቻችን በተለያዬ ግዜ በከፋ ሕዝብ ላይ የተቃጣውን ወረራ በትግልና በፅናት ታግለው ተምሳሌት የሆኑትን ያህል ዛሬ ከኋላው የተነሱት ሁሉ በብልፅግናና በስልጣኔ ቀድመውት በጨለማ ውስጥ ይገኛል። ትናንትም ሆነ ዛሬ ሕዝቡን ካለበት አስከፊ ሁኔታ ለማውጣት አያሌ ልጆቹ መስዋዕት ከፍለዋል። ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ረግጦ የያዘው ዘረኛና ዘራፊ ቡድን ያሳየውን ያህል ጭካኔና ሕዝብ አጥፊ እርምጃ በረጂም ታሪኩ ከገጠሙት መከራዎች ሁሉ የባሰ ነው።
ትናንትም ለነፃነት መታገሉን ያላቆመው የከፋው ህዝብ ልጅ ዛሬ በተለይም ወጣቱ የግፍ አገዛዝ እንዲያከትም ከዳር ዳር ተጠራርቶ የፃነት ድሉን መጎናፀፍ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ህፃናት ያለአሳዳጊ፣ ወጣቶች ያለነገ ተስፋ፣ አዛውንቱ ደግሞ ያለጧሪ የሚኖሩባት የሰቆቃ ሕዝብ መሆን እንዲያበቃ የሞት የሽረት ትግል ማካሄድ ወሳኝ ነው። ይህንን ብሩህ ተስፋ እውን ለማድረግ ድምፃቸውን ስለአሰሙ ብቻ በጠራራ ፀሃይ በአጋዚ ጥይት ግንባር ግንባራቸውን እየተመቱ የወደቁት ህፃናት፣ ጎልማሶችና አዛውንት በቴፕ በሚዛን መብታቸውን ስለጠየቁ ብቻ እንደጠላት ጦር በጠራራ ፀሀይ በአውሮፕላን የተገደሉ ህዝባችን ደም ከንቱ የሚቀር አይሆንም። ሕዝባችን ፍርሃትን አሸንፈው ወጥቷልና።
የዘረኞች ክንድ እየላመ፣ ቀናቸውም እየጨለመ በመሄዱ የሚያደርጉትንና የሚራመዱትን መንገድ እያስተዋሉ ሳይሆን የበለጠ ወደመጥፊያቸው እየተንደረደሩ ነው። አውቃችሁም ይሁን ሳታውቁ ለአገልጋይነት ውስጣቸው ተሰልፋቸወሁ ያላችሁ የወያኔ ካድሬዎች የተሳፈራችሁበት መርከብ ከመስጠሙ በፊት በማምለጥ አሁኑኑ ይህን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቁ። እዚህ ላይ እውነተኛ ለውጥ እንዲመጣ የሚታትሩትን የታሪክና የህዝብ ባለውለታ መሆናችሁን ልንታስታውስ እንወዳለን።
ከዚህ ዘራፊና አስከፊ ስርዓት ውድቀት በኋላ “የት እንወድቅ ይሆን?” ብለው ከሚያስቡ የዋሆች ብዙ መለየት አለብን። የከፋ ሕዝብ ዙርያ ገባውን መቃኘት ያስፈልጋል። ለህዝብ መብት በመታገላቸውና በመጮሃቸው በዘረኞች መንጋጋ ውስጥ ሰሞኑን ተይዘው በአካል ደቅቀው፣ በመንፈስ ግን ገዝፈው የወጡትን ወጣቶቻችንን ስናይ፣ ለሕዝባቸው ያላቸውን ራዕይ በአንደበታቸው የተናገሩትን ስንሰማ የከፋ ህዝብ ከሌሎች ወንድምና እህት ህዝብ ጋር ነፃ ይወጣል እንድንል እንገደዳለን። የሰሞኑ ጀግና የከፋ ሕፃን ሕዝቡ እንዲደራጅ ተልዕኮ ወረቀት እያሰራጨ በወያኔ ነብሰ በላ ወታደር ተይዞ ማነው ያሰማራህ ስባል እኔ ለመብቴ ለመታገል የማንንም ትዕዛዝ አልሻም ያለው የ12 አመት ሕፃን ነው። የዚህን ህፃን ተጋድሎ ወደፊት ከህዝባችን ነፃነት በኃላ የሚዘከር ይሆናል፡፡ ይህ የህዝቡ ያልተገደበ ስሜት ያራዳቸው አምባገነኖች የመውደቂያቸው ማፋጠኛ የሆነውን አስቸኳይ አዋጅ ማወጃቸውን ስናይ የዚህን ያህል ትልቅ ህዝብ ለዚህን ያህል ጊዜ ማሰብ በተሳናቸው መገዛቱ ይቆጫል፣ያንገበግባል።
ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት በወያኔ ሲዳጥ ተጨፍልቀው ነጥረው የወጡ የአምባገነኖች መቅሰፍትና የህዝብ ተስፋ የሆኑ አክትቭስቶች በአገርና በመላ ዓለም ተሰራጭተው የክልላችን አየር በመረጃ እያጥለቀለቁ በመሆናቸው የጨለማ ሃይላትን መደበቂያ በማሳጣታቸው እነዘህን መንገዶች ለመዝጋት ይዋትታል።
ሳይማር ያስተማራቸውን ህዝብ ያልዘነጉና እውቀታቸውን በተለያየ አጋጣሚ እያካፈሉ የነገውን የከፋ ህዝብ ከሌላ ኢትዮጵያ ህዝብ እኩል ለመገንባት ትውልዱን የሚያስተምሩ ብዙ ወጣት ያለው የከፋ ህዝብ ወድቆ አይቀርም።
ለወያኔዎች መቅሰፍት ለህዝብ ደግሞ ተስፋ የሆኑ ወጣቶቻችን ሃይላቸው የማይገደብ ምንጫቸው የማይነጥፍ ነጎድጓድ በመሆን ትግሉን ይቀጥላሉ። የሕዝቡን ተሰፋ የነጠቁ ጉግ ማንጉጎች ትቢያ እየሆኑና እየተፍረከረኩ ታሪክ ወዳዘጋጀላቸው ስፍራ ያዘግማሉ።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: