Leave a comment

ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረት የተላለፈ ወቅታዊ መግለጫ


 

ኢትዮጵያ ሃገራችን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከምትታወቅባቸው የተፈጥሮ ሃብቶች አንዱና ዋነኛው ጥቅጥቅ ደን ሲሆን ከዚህም ደን ውስጥ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው የደን ሃብት ተጠቃሽ ስለመሆኑ አሻሚ የሌለዉ ሃቅ ነው። ምንም እንኳን በሃገር ደረጃ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች የደን ሃብት መመናመን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ቢመጣም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ማለት በኢሉባቦር፣በካፋ፣በሸካ፣እና ቤንች ማጂ ዞኖች የሚገኘው ጥቅጥቅ የተፈትሮ ደን በሕዝቡ ባለቤትነትና እንክብካቤ ተጠብቆ በመቆየቱ የተነሳ ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ለአየር ሚዛን መዛባት ጥብቅና እንድትቆም ያስቻላት ይኸው የደን ሃብት ነው። ይሁንና በሰሞኑ ከእነዚህ አካባቢዎች አንዱ በሆነው ሸካ ዞን 250 ሄክታር ደን ተቃጥሎዋል። እንደሚታወቀው የወያኔ መንግስት በኦሮሚያ ክልል በተለያዮ አካባቢዎች በተለይም በባሌ ተራሮች የነበረዉን ጥቅጥቅ ደን የኦነግ ሠራዊት መሽጎበታል በሚል የውንብድና አስተሳሰብ በቀላሉ ሊተካ የማይችል የደን ሃብት በማውደም የአገርንና የሕዝብን የመኖር ህልውና አደጋ ውስጥ መጣሉ ይታውሳል። በመሆኑም ከዚህ ተመሳሳይ እኩይ ተግባሩ በመነሣት በሸካ ዞን የሚገኘውን ከዚህ ቀደም በአካባቢው ህብረተሰብ ትግል ለባለሃብቶች እንዳይሰጥ በተከለከለ መሬት ለይ የሚገኘውን የደን ሃብት አያቃጥልም የሚል እምነት የለንም ። የሸካ ዞን ወይም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢ ካለዉ ልዮ የተፈጥሮ ፀባይ የተነሳ ዓመቱን በሙሉ ያለማቁዋረጥ ዝናብ የማይታጣበት ምድር በመሆኑ በየትኛውም የታሪክ አጋጣሚ የእሳት ቃጠሎ ተከስቶ አያዉቅም:: ይህ ተግባር ሆን ተብሎ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ሕብረትን እንቅስቃሴ ለመግታትና ብሎም አማጺያን ሊመሸጉበት ይችላሉ በሚል ሰንካላ ምክንያት የተፈፀመ እንደሆነ መላው የአከባቢ ህዝብ ያምናል:: ይህም ድርግት ሕዝቡን ያስቆጣና ያሳዘነ ከመሆኑም በላይ ድርጅታችንን በእጅጉ አሳስቦታል። ይህ ደን ለአካባቢው ሕዝብ ከሚሰጠው ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባሻገር በተለያዮ ጊዜያት ከሚነሱት ጠላቶቹ ራሱን በመሸሸግ ክፉውን የሚያሳልፍበትና እራሱን የሚከላከልበት ሁለተኛ ቤቱ እንደሆነ ታሪክ ምስክር ነው። በ1977 ዓ.ም በደርግ መንግስት የተተገበረውን የመንደር ምስረታ በመቃወም ጀግናው የሸካ ሕዝብ በዚህ ደን ውስጥ ሆኖ ነበር ደርግን ተዋግቶ መብቱን ያስከበረው። እናም ይህንን በቅጡ ጠንቅቆ የሚያውቀው የወያኔ መንግስትም ላለፉት 27 ዓመታት እያደረሰ ያለውን የግፍና የሰቆቃ አገዛዝ በመቃወም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቡ መደራጀትና እንቢተኝነቱን መግለፅ በመጀመረበት ማግስት ይህንን የተቀነባበረ ድርጊት መፈፀሙ ምን አልባትም ታሪክ ራሱን እንዳይደግም ስለመሆኑ ህዝቡ እና ድርጅታችን በሚገባ ተረድቶታል። ስለመሆኑም የወያኔ መንግስት በለመደው ተግባሩ ባደረገው የውንብድና ስራው ይህንን ደን ማቃጠሉ በተዘዋዋሪ በጥቂት ቁጥር ሊገመት የማይቻል ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ከመፈጸም የተለየ ወንጀል ያለመሆኑን እንዲያውቀውና በማናቸውም ሁኔታና ጊዜ በህግ ከመጠየቅ ነፃ እንደማያደርገው እናሳስባለን። በመጨረሻም መላው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብና ብሎም መላው የኢቶዮጵያ ሕዝብ ችግሩ የአገር በመሆኑ የተፈትሮ ሃብታችንን እንድንጠብቅና ይህንን አጥፊ ተግባር እየኮነንን በየትኛውም የትግል አቅጣጫ እንዲታገል በተለይም የሸካ ሕዝብም የጀመረውን የእንቢተኝነት እና የነፃነት ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥርያችንን እያቀረብን ድርጅታችን ከችግሩ አሳሳቢነት አኳያ ሁኔታውን አበክሮ የሚከታተልና የወያኔን መግስት ለማስወገድ ቀንና ማታ ያለመታከት የምሰራ መሆኑን እንገልፃለን።

እግዚአብሔር ሃገራችንንና ሕዝቡን ይጠብቅ!!!

Kaffamedia Kaffamedia

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: