Leave a comment

በአሁኑ ሰዓት ሕዝቡ በተለይም ወጣቱ በአከባቢያችን የጀመረውን እንቅስካሴ በብልህነትና በቆራጥነት ለመቀጠል ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ (ለከፋ; ለሸካ; ለቤንች እና ለማጂ) ሕዝብ የተላለፈ ጥሪ!!! (ከአናሞ)


በአሁኑ ሰዓት ሕዝቡ በተለይም ወጣቱ በአከባቢያችን የጀመረውን እንቅስካሴ በብልህነትና በቆራጥነት ለመቀጠል ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ (ለከፋ; ለሸካ; ለቤንች እና ለማጂ) ሕዝብ የተላለፈ ጥሪ!!! (ከአናሞ)

የቀደሞ ከፋ ክፍለ ሀገር ሕዝብ ረጅም ዘመን የመንግሥትና የነጻነት ታሪክ ባለቤት የሆነ ጥንታዊ ሕዝብ መሆኑ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። በተለያየ ዘመን የህዝቡን ሀብት ለመዝረፍ፤ ዳር ድንበሩን እና ሉዐላዊነቱ ለመገርሰስ ተስፋፊዎች፤ አምባ ገነን መሪዎችና እና የክልላችን ተፈጥሮአዊ አቀማመጥና ሃብት ያጓጓቸው ዘራፍዎች ተደጋጋሚ ጦርነትና ወረራ ያደረጉበት ቢሆንም፤ አባትና እናቶቹ በከፈሉት እጅግ ግዙፍና አኩሪ መስዋእትነት ጠላቱን መክቶ በነጻነት የኖረ ህዝብ ስለመሆኑ ታሪኩ የማያሻማ ምስክር ነው። ይህ ህዝብ በባህሉ የመላ አፍረካ ህዝብ መገለጫ ነው ተብሎ የሚጠቀስ ታሪክ ባለቤት የሆነው የሁሉም የክልሉ ሕዝብ ሕብረትና መስዋእት ክፍያ ውጤት ነው። የዚህ አኩሪ ህዝብ ታሪክ፤ የክልሉ ተወላጅና ባለቤት የሆንነው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች በታሪካችን ኮርተን፤ አንድነታችንን ጠብቀን እና ከሌላው እህት ወንድም ኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የትውልድ ግዴታችንን እየተወጣን ብንገኝም፤ በተደጋጋሚ የተከሰተው ውስጣዊ ችግር፤ የስልጣን ፍትጊያ እና ሽኩቻ የታሪካችን አንዱ ገጽታ ሆኖ ቆይቷል። ኋላ ቀር የዕድገት ደረጃችን ላይ ፓለቲካዊ ችግሮቻችን ተጨምሮ መገኘታቸዉ፤ ህዝባችንን በነጻ ፈቃዱ ላይ የተመሰረተ ህዝባዊና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ባለቤት ለመሆን የሚያደርገዉን የረዥም ጊዜ ትግል ዉጤት አዘግይተዉታል ። በተለይም ዘራፍ ህወሓት በበላይነት የሚያሽከረክረው ኢህአዴግ የሥልጣን እርካቡን ከተፈናጠጠ ጊዜ ጀምሮ ህዝባችንን በከፋፋይ ፖለቲካ ጠምዶ፤ በአንድ ህዝብ መካከል ልዩነቶችንና ቅራኔዎችን በውሸት እፈጠረ የክልሉን አንጡራ ሀብት እየዘረፈ ፤ በክልላችን ሠላምና መረጋጋት እንዳይሰፍን፤ ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ያለው እድገት እንዳይኖር ብርቱ ምክንያት ሆኗል። ይህም ሁኔታ የሕዝባችንን ሞራል እየጎዳው በመምጣቱ አሁን የምንገኝበት እጅግ ፈታኝ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል።በመሆኑም ዛሬ ባለንበት ወቅት የሕዝባችን ህልውናና የሕዝቡ አብሮና ተቻችሎ መኖር በሁሉም የክልላችን ነዋሪዎች ጫንቃ ላይ ወድቋል። ነገር ግን ከኢህአዴግ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት የተከተልነው መንገድ፤ የክልል ማንነትን በመታደግ ላይ ልዩ ትኩረት መስጣታችን አይካድም። ይህም ሆኖ የተቃውሞ ትግሉ አንዴ ቦግ አንዴ ተግ ሲል ረዥም ጊዜ ቢያሣልፍም አሁን የደረስንብት ከፍትኛ ህዝባዊ ተቃውሞና እምቢተኝነት የወያኔን ሥርዐት በማፈራረስ ሂደት ላይ እንደሆነ ምልክት ሰጭ ነው ማለት የቻላል። ይህ ያለንበት ወቅት ያለውን አገዛዝ ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ያደረሰው ቢመስልም ቀጣዩ ምዕራፍ በራዕዩም፤ በተግባሩም በፍልስፍናውም ሆነ በፖለቲካ ስልቱ ዘላቂ ለሆነው ለሕዝባችን ሉዐላዊነትና፤ ለህዝባችን አንድነት መሠረት ያደረገ፤ የጋራ አንድነት ጉዞ ማመቻቸት እንዲችል፤ ይህ ትውልድ በአብሮነት ለመኖር የሚያደረገው ቀጣይ ጉዞው እና አንድነቱ በጠበቀ መልኩ ትግላችንን እንጨርሳለን፡፡ የኛ ትግል የሚሆነውና እየሆነ ያለውም የህዝባችንን የአንድነትና የአብሮነት ታሪክ፤ በትውልድ ቅብብሎሽና በመሰዋዕትነት የተገነባውን የሕዝባችንን የታፈረና የተከበረ በመሆኑ፤ ዴሞክራሲያዊና ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለአድልኦ በዕኩልነት መብታችን ተከብሮ መኖር የምንችልበትን አገርን መገንባት ድረስ ይዘልቃል። ከፊታችን ተጋርጦ የሚገኘውን ተግዳሮትና ችግር መወጣት የምንችለው፣ይህንኑ የማያወላውል እውነታ መቀበል ስንችል ብቻ ይሆናል። በእኛ ግምት ሁሉም የክልላችን ሕዝብ አርቆ አስተዋይ፤ አብሮና ተሳስቦ መኖሩን ፈላጊ፤ ከድህነትና ከስደት አሮንቃዎች ወጥቶ ራሱንና ተተኪ ትውልድን የተሻለ ኑሮ እንዲኖር ሁኔታዎችን አመቻች ለመሆን የሚችል ታላቅ ሕዝብ ነው። እኛም ያለብን ሃላፊነት ይህን ሕዝብ መደገፍ እንደሆነ እናምናለን። ህዝባዊ ዐመጽ ህዝብ ክቡር መስዋዕትነት የሚከፍልበት የትግልና የነጻነት ጉዞ የመሆኑን ያህል በብስለት፤ በብልሃት፤ በጥንቃቄ፤ በተደራጀና በእውቀት በተላበስ አመራር ተይዘዋል፡፡ እንደ ወያኔ/ኢህአዴግ ያለ ሃላፊነትና ለአገር ህልውና አደጋ ላይ መውደቅ ምንም ደንታ በማይስጠው አገዛዝ ዉስጥ፤ የአገሪቱ ቋሚና ዘላቂ ሃብት፤ ብሄራዊ ቅርስ የህብረተሰቡ መገልገያ ተቋሞች ወ.ዘ.ተ. ለአደጋው ሰለባ እንደሆኑ በማደረግ የሕዝቡን ትግል ለማኮላሸት የሚጠቀመው ሌላ ዘዴ መሆኑን ሕዝባችን በዚህ አጋጣሚ እንዲገነዘበው የሚንሻው ጉዳይ ነው። ስለሆነም- የክልሉ ምሁራኖች፤ ባለሙያዎች፤ ሕዝብ ወዳዶች በጋራ ያደራጁት በዉይይትና በጥራት ላይ ለተመሰረተ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ሕብረት (ደምኢሕሕ) ስር በመሰባስብ በአሁኑ ወቅት ክልላችን ከገባበት የታርክ አሮንቃ ይወጣ ዘንድ ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች በጥሞና በማጤን፤ በተቆርቋሪነት፤ በሃላፊነት ስሜትና የዜግነት ግዴታንም መሰረት በማድረግ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በትግሉ ውስጥ ተሳትፎ እንዲታደርጉና የሚታደረጉ ሃይሎች ሁሉ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ነጥቦች የትኩረት አቅጣጫ ላይ ከፈተኛ ግምት እንዲሰጡ ደምኢሕሕ ጥሪ ያደርጋል። 1 የፖለቲካ ጠቀሜታን ለማግኘትም ሆነ ለማስገኘት ህዝብን ለህዝባዊ እንቢተኝነትና ዐመጽ ለማነሳሳት አቅጣጫንም ለማስያዝ የሚደረጉ የፕሮፖጋንዳንና የቅስቀሣ ስራዎቻችን፤ ማንነታችንን፤ አንድነታችንን እንዲሁም እንደ ክልል አንድ ፤ እንደ ህዝብ አንድ ህዝብ፤ የጋራ ታሪክ የጋራ ማንነት ያለን የተዋለድንና የተቀላቀልን ልዩ ልዩ ጎሳዎችን በዉስጡ ያቀፈና የአንድ ክልል ልጆችና ለፍትህና ዴሞክራሲያው ስረዐት የቆምን መሆናችንን የሚያረጋግጥና መስረት የጨበጠ መሆን ይገባዋል። የሕዝብ ስርጭት ልዩነት (Diversity) ጌጥ እንጅ የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ መሆን የለበትም።

2 በየትኛውም ደረጃና አካባቢ ያሉ የወያኔን/ኢህአዴግን አገዛዝ የሚታገሉ ሃይሎች በትግሉ ሊጣመሩና ሊተባበሩ የሚችሉበትን የጋራ ብሄራዊ አጀንዳ በመቅረጽ የተቀናጀና የተቀነባበረ ህዝባዊ የትግል ዕምርታን ማሳየት አለባቸዉ።

3 የዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ግንባታ ባለ ብዙ ፈርጅ ከመሆኑም በላይ፤ ብሄራዊ፤ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ማሃበራዊ ጉዳዮች የሚስተናገዱበት ሂደት ነው። ታዲያ! ወደዚህ ፖለቲካዊ ሂደት እንዴት በጋራ እንገባለን? እንዴትስ ከግቡ እንደርሣልን? የሚሉትንና ሌሎችንም መሰረታዊ የዲሞክራሲና የሕዝብን ልዕልናን ለማስከበር የሚያስችል የሽግግር ሂደት በክልላችንና በመላ ኢትዮጵያ ምን መምስል እንዳለበት የሚመለከታቸው የፖለቲካ፤ የማህበረሰብ፤ የኃይማኖትና ሌሎች ሃይሎቸና የክልላችንና የሀገራችን ሕዝብ ስርጭት የሚወክሉ እውቅና ያላቸው ግለሰቦች የጋራ ምክክር እና ውይይት (ዳያሎግ) በማድረግ መታገያና መፍትሄ የሚሆን የጋራ የፓለቲካ ሠነድ ማዘጋጀትና ሁሉንም ያሳተፈ መሆኑን ማረጋገጥ ወቅቱ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን ማስገንዘብ እንሻለን። ስለሆነም- አገዛዝ ይመጣል፤ አገዛዝ ይሄዳል፤ መሪ፤ ፓርቲ፤ ርዕዮተ ዓለምም ይለዋወጣል፤ ነገር ግን አገርና ህዝብ በዚህ አይነቱ ቀመር የሚካተቱ ከቶ አይሆኑም። የአገርና የሕዝብ ሕይወት በአንድ ትውልድ ህይወት የሚገደብ ሊሆን አይገባም ። በመሆኑም፤ የአገር፤ የታሪክንና የትውልድን ሃላፊነታችንንና አደራን ለመወጣት ተባብረና እየተናበብን እንነሣ እያልን ሌሎች ወንድምና እህት ኢትዮጵያውን ሁሉ በጋራ ታሪካዊ አደራችንን በድል እንወጣ ለማለት እንፈልጋለን፡፡

ትግላችን ዘላለማዊ ውርሳችን ነፃነት ነው!!!!!!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: