2 Comments

ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ሙዝየምን በተመለከተ የተሰጠ የአቋም መግለጫ


ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ሙዝየምን በተመለከተ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

በቦንጋ የተገነባው ብሔራዊ የቡና ሙዚየም ባለቤት ማነው?

አፋጣኝ ምላሽ የሚያሻው አንገብጋቢ ጥያቄ

32655642_1835541106509111_6779998252063260672_n

የኢፌድሪ መንግስት ፕረዝዳንት የነበሩት አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ እና የተለያዩ የፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት በ1999 ዓመተ ምህረት የመሠረተ ድንጋይ ሲያኖሩ::

በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠው በ2000 ዓመተ ምህረት የሚሊኒየም በዓል በብሔራዊ ደረጃ ከመከበሩ ጋር ተያይዞ በማስታወሻነት የተለያዩ ሃገራዊ ፕሮጀክቶች እንዲገነቡ በመንግስትና በወቅቱ በዓሉን እንዲያስተባብር ከተሰየመው ብሔራዊ የሚሊኒየም በዓል አከባበር ኮሚቴ መወሰኑ ይታወሳል::

በመሆኑም ከእነዚህ ታላላቅ ሃገራዊ ፕሮጄክቶች አንዱ በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የተገነባው ብሔራዊ የቡና ሙዚየም በዋናነት ተጠቃሽ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ ከመሆኗ ቀጥሎ የምትታወቅበት ለዓለም በገፀበረከትነት ያበረከተችው ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ልዩ ሥሙ ማኪራ በመሆኑ ነው።

ምንም እንኳን በወቅቱ ለኢትዮጵያ ታሪክ የተዛባ አመለካከት ያላቸውና ከርካሽ ጥቅም በመነጨ እኩይ ፍላጎት ባላቸው አንዳንድ የፌደራል ባለሥልጣናት እና አንዳንድ የኦሮሚያ ክልል አመራሮችና ባለሃብቶች ግንባታውን ለማደናቀፍ ጥረት ቢደረግም በእነ አቶ ሥዩም በረደድ የሚመራው ብሔራዊ የሚሊኒየም በዓል አከባበር ኮሚቴ የጉዳዩን አሳማኝነት በተጨባጭ መረጃና ማጣቀሻዎች በማስረገጥ የሃሳብ የበላይነት ውሳኔ ላይ ሲደርስ በዘመኑ የኢፌድሪ መንግስት ፕረዝዳንት የነበሩት አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ እና የተለያዩ የፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት በ1999 ዓመተ ምህረት የመሠረተ ድንጋይ ተጥሎ ግንባታው በዚሁ ዓመት ተጀምሮ በባለድርሻ አካላት ሁሉን አቀፍ ርብርብ ተደርጎ በ2007 ዓ. ም የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስቴር አቶ ኃይለማሪያም ደሣለኝ በተገኙበት ለምረቃ በቅቷል።

32696420_1835541126509109_8509457444722704384_n

የኢፌድሪ መንግስት ፕረዝዳንት የነበሩት አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ እና የተለያዩ የፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት በ1999 ዓመተ ምህረት የመሠረተ ድንጋይ ሲያኖሩ::

በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት አቶ ኃይለማሪያም ደሣለኝ ባሰሙት ንግግር እንደገለፁት ካፋ የቡና መገኛ በመሆኗ የተገነባው ይህ ሙዚየም የሃገር ሃብት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ዓይነት ምርምሮችና ጥናት የሚጠቅም በመሆኑ የፌደራል መንግስት በዚህ ረገድ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል ማለታቸው የሚዘነጋ አይደለም። ይሁንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት ንግግርና የገቡት ቃል ምንም ውጤት ያላስገኘ በመሆኑ ሙዚየሙ ባለቤት አጥቶ ለተሰራለት ዓላማ ሣይዉል በመፈራረስ ላይ ይገኛል።

32667390_1835541136509108_3193623323506376704_n

የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስቴር አቶ ኃይለማሪያም ደሣለኝ በቦንጋ የተገነባውን አለም አቀፍ የቡና ሙዚየም በማስመረቅ ላይ

እናም የጉዳዩ አሳሳቢነትን በተመለከተ በዚህ ሠሞን የኢዮጵያ ብሮድ ካስት ኮርፖሬሽን አንድ ጋዜጠኛ የአከባቢውን ነዋሪዎች አስተያየት በመቀመር ዜናውን ሚዛናዊ ከማድረግ አኳያ ምላሽ እንዲሰጡ የማይመለከታቸውን ግለሰ በመጋበዝ: የተጋበዙት ግለሰብም በጉዳዩ ላይ ምንም መረጃ እንደሌላቸው በማስመሰል ድምፃቸውን በሥልክ ያሰሙት የኢፌድሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የህግ ጉዳዮች አገልግሎት ዳይረክተር አቶ በላቸው ድሪባ የሠጡትን አሳፋሪና አሣዛኝ ምላሽ ፓርቲያችንና ህዝባችንን በእጅጉ አሳዝኗል: አስቆጥቷልም።

በቅድሚያ እኝህ ግለሠብ የዚህን ሙዚየም ግንባታ ዳራ እና ለምን በማን ተገነባ የሚለውን ምንም ዓይነት እውቀትና መረጃ እንደሌላቸው በማስመሰል እውነቱ ወይም ሀቁ ከላይ የገለፅነው ከመሆኑም በላይ በወቅቱ ጉዳዩና ግንባታው የተመራበት ሥትራቴጂክ ፕላንና ሥራውን የመሩት የኮሚቴ አባላት በአካል በሚዲያ ቀርበው ማስረዳት እየቻሉ ሙዚየሙ በዞኑ ህዝብ ፍላጎት ነው የተገነባው በማለት መናገራቸው ሚንስቴር መ/ያ ቤቱ ይህን እና ሌሎችንም ሥራዎች ያለ እውቀትና ያለ መረጃ ብሎም አቅም በሌላቸው ባለሙያዎች መታጨቁን ያመለክታል።

እንደሚታወቀው ምንም እንኳን ካፋ የቡና መገኛ መሆኗን የሃገራችን ህዝብ አይደለም ዓለም በአደባባይ እየመሰከሩ ያለው እውነት ሲሆን በድርጅታችን እምነትና በተከበረው የካፋ ህዝብ አመለካከት ካፋ ማለት ኢትዮጵያ: ኢትዮጵያ ማለት ካፋ የሚል የማይሸረሸር ፅኑ ቁርኝት መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።
ሆኖም ታሪክን ወደ ጎን በመተው ከእውነት ጋር በተቃርኖ የሚተያዩ አካላት ዛሬም የህዝብና የመንግስትን ሥልጣን ሽፋን በማድረግ የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ ለማራመድ እየሞከሩ ስለመሆናቸው የአቶ በላቸው ድሪባ የተዘበራረቀ እና በእጅጉ ከእውነት የራቀ ምላሽ ማሣያ ነው።

በእርግጥም እንደዚህ ዓይነቱ የተፈረካከሠ እና ጨለምተኝነት የተረጋገጠበት አመለካከት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር እና መላው የሃገራችን ህዝብ የሚመኟትን አዲሲቷን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ አስቸጋሪና እንቅፋት መሆኑ ግልፅ ነው:: ጉዳይ በአጭሩ መፍትሔ ካልተሰጠው በቀር ትውልድን ከትውልድ: ሕዝብን ከሕዝ እንዲሁም መንግሥትና ሕዝብን የሚያጋጭና ወዳልተፈለገ ጎዳና እንዳያመራ ከአሁኑ ስጋታችንን ለመግለፅ እንወዳለን:: ስለዚህ መንግስት ሚዛናዊ እና ፍትሀዊ በሆነ መርሆ በመታገዝ ጉዳዩን መስመር እንዲያሲዘው እያሳሰብን ድርጅታችን ከመላው ህዝብ ጋር በመሆኑ ተፈጻሚነቱን በጥብቅ እንደሚከታተለው ለመግለፅ እንወዳለን ።

የተዛቡ አመለካከቶችን እየታገልን አንዲት ኢትዮጵያን እውን እናደርጋለን።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረት

2 comments on “ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ሙዝየምን በተመለከተ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

 1. That is a a very wise, intelligent and professional comment. Every one knows that the world recognises Kaffa as home land of coffee Arabica.

  The local/current rent seekers want to mobilise our good friends and neighbours for the wrong cause? In fact my first hand information is that Jimma farmers recognise that they believe that they are are still in Kafa.

  The current nominal leader /the then M.O. Agriculture/ had honoured and enjoyed the celebration of Limu or whatever as home land of coffee some 25 years back; refer to Tobia newspaper/ purposey or ignorantly. May be he was moved by just because of a drama by country director of the Country director of Oxfam US a ;;;;; Aberra who considers himself a researcher; who flattered with the the Genius Meles about the topic 25 years back; while the latter actually knew much more than that. The former did that to ensure his position /the WRONG WAY/. Meles knew and talked much more about the people of Kaffa, Jimma and Wollega to his colleagues than the coffee and he laughed/grimaced at Aberra.

  If Coffee is not from Kaffa then it is a point of debate.

  Otherwise if Ethiopia doesn’t recognise Kaffa as home land, then we will move to the next door and we can with the the full fledged history and benefit as well as benefit out of our intellectual property; the same way our predecessor proposed to move to Rwanda /to the late King some 80 years back when we were dispossessed of our land rights/. I have the facts about several issues than the coffee itself.

  If we don’t get an official intellectual property rights about Kaffa as home land right from the Ethiopian intellectual property rights office; then ”Hulum Yidebelaleqal’; everything will be spoiled; and we don’t want that; because WE ARE WISE.

  Like

 2. Please edit and remove repetitions. I was emotional.

  Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: