Leave a comment

የካፋ ደንና ውበት በውስጡ ልዩ ትርጉም ያላቸውን ዕፅዋት የያዘ ነዉ፡፡ ከነዚህም ዋንኛውና የታወቀዉ ካፋ ለዓለም ያበረከተችዉ ገፀ በረከት ቡና ነዉ፡፡


By:SHIMEKIT TADELE GEBABO
19/05/2018

የካፋ ደንና ውበት በውስጡ ልዩ ትርጉም ያላቸውን ዕፅዋት የያዘ ነዉ፡፡ ከነዚህም ዋንኛውና የታወቀዉ ካፋ ለዓለም ያበረከተችዉ ገፀ በረከት ቡና ነዉ፡፡ስለካፋ ሲነገር ስለቡና በተገቢዉ መጠን ባይነገር ትክክል አይሆንም፣ ….
ካፋ የቡና መገኛ ብቻ ሳትሆን ከምኒልክ ወረራ በፊት በአፍሪካ አህጉር ከፍተኛ የቡና አምራች ሀገርም ነበረች (ብሩስ 1804፣246 VOL III):: ቡና ከካፋ ለመገኘቱ ከብዙ የታርክ ፀሐፊዎች መካከል አንዱ ማክስ ግሩል የተባለ ፀሐፊ እንዲህ ይላል፡፡
“…ከዓለም ህዝብ አብዛኛዉ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህች ሀገር (በካፋ) የበቀለዉን (የተገኘዉን) ፍሬ (ቡና) ጭማቂ ስለሚጎነጭ፣ የዚህች አፍሪካዊት ሀገር (የካፋ) ስም ቢያንስ ዓመቱን ሙሉ በየቀኑ በብዙ የዓለም ህዝብ አፍ ይጠራል፡፡ ቡና (በካፋ) የተገኘዉና መታወቅ የጀመረዉ ታሪክ መመዝገብ (መፃፍ) ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ሲሆን፣ አጠቃቀሙም ወደ መላዉ ደጋማዉ የኢትዮጵያ ግዛት የተሰራጨዉ ከዚሁ ሀገር ነበር፡፡ ከዚያም በ9ኛዉ ክ/ዘመን አጠቃቀሙ በፔርሺያ (ኢራን) ይታወቅ ጀመር…” (ማክስ ግሩል 1932፣ ገፅ 169)፡፡
“…….The name of this African country is nevertheless on the lips of many every day of the year, since a great part of the population of the world daily drinks the juice extracted from the berry of a plant which originally grew in kaffa-coffee. Coffee has been in kaffa since the down of history and it was from kaffa that in early time the use of the extract of the “kaffa bean” spread over the entire Ethiopian highland. In 9th c A.D its use came to be known to the Persians…”(max gruhl 1932; 169).
“…ከሁለት ምዕተ ዓመታት በፊት ብሩስ እንዳስተዋለዉ፣ ካፋ የቡና ተክል መገኛ እንደሆነ በጣም ይታመናል፣ ከካፋ-አማራ ጦርነት በፊትም በአፍርካ ዋና የቡና አምራች ምድር እንደነበር ይነገራል፡፡ በየዓመቱም ካፋ 350000 ኪሎ ግራም የሚሆን ቡና ወደ ዉጭ ትልክ ነበር…” (ላንጌ 1982 ገፅ 8)፡፡
“…kafa may very well be, as Bruce(1804) noted two centuries ago, the birth place of coffee plant. Prior to kafa-amhara war, kafa was said to have been “the principal coffee producing land in Africa”,….kafa was exporting some 350,000 kilo grams of the valuable bean annually…”(Lange 1982:8).
“…ቡና የኢትዮጵያ ዋና የኢኮኖሚ ምንጭ ሲሆን ምንጩም ካፋ መሆኑ ለዘላለም የሚታወስ ነዉ….”(ኦሬንት 1969፡37)፡፡
“ቡኖ” የቡና የካፍኛ መጠሪያ ቃል ሲሆን በኢትዮጵያ በአብዛኛዎቹ ቋንቋዎችም የዚሁ ቃል መነሻ ሆሄ ተቀጥላ ሆሄያት እንዳለና ሁለተኛዉ ሆሄ እየተለወጠ ለተመሳሳይ ነገር (ለምሳሌ ሲጠብቅና ሲላላ ቡና፣ቡን፣ቡኔ፣ቡኒ ወዘተ) በሚል በመጠሪያነት ያገለግላል፡፡
የቡናን ከካፋ አወጣጥና አሠረጫጨት በተመለከተ አንድ የዐረብ ሰዉ በነፍሱ ቆርጦ የቡና ዘር ከካፋ በማዉጣት አረቢያ እንደወሰደና በየመን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲተከል እንዳደረገም ይነገራል (ማክስ ግሩል 1932፡172)፡፡ ቡና በዐረብ አገሮች እስካሁንም በመነሻዉ ቦታ የተሰጠዉን ስያሜ በመያዝ ቡና ተብሎ ይጠራል፡፡ ከየመንም በሆላንዶች አማካይነት ወደ ሩቅ ምስራቅ ለመሠራጨት በቅቷል፡፡ ዛሬ በዓለማችን ከፍተኛ የቡና አምራች ሀገር ብራዚል ስትሆን ወደዚች ሀገር የተወሰደዉም በፖርቹጋሎች አማካይነት መሆኑ ይታመናል፡፡ ቡና በ10ኛዉ ክ/ዘመን በመካ መዲና ይጠጣ ነበር፡፡ ቡና በአዉሮፓዊያን ዘንድ በ1600 ዓ.ም. ይታወቅ የነበረ ሲሆን በአዉሮፓ የቡና ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የተከፈተዉ በጣሊያንዋ የቬኑስ ከተማ በ1645 ገደማ ነበር፡፡ ከዚህ ቀደም ብሎ በ1632 ዓ.ም. አካባብ ደግሞ በሺ የሚቆጠሩ የቡና መጠጫ ቤቶች ካይሮ ከተማ ይገኙ ነበር፡፡ ከዚህ ወቅት ጀምሮ ቡና በመላዉ አዉሮፓና በዓለም ለመሠራጨት በቅቷል (ማክስ ግሩል፣ 1932፡172፣selamta vol 13; 1996; selamta vol 16,1999;selameta vol 18, 2001)::
ከዚህ ሌላ ቡና ከካፋ ስለመገኘቱና ከዋና ዋና የገብ ምንጮችም አንዱ እንደነበረ ብሩስ (1804)፣ ኒዉማን (1902)፣ ስትሮበ (1963) እና ሌሎችም በስፋት እንደጻፉበት የኋለኞቹ እነ ላንጌና ግሩል ያረጋግጣሉ፡፡
ካፋ ዉስጥ ቡና የሚገኘዉ ተተክሎ በእንክብካቤ ከሚያድገዉ ተክል ብቻ ሳይሆን ምንጩ ከሆነዉ ከጫካ ዉስጥ ከሚገኘዉ አዉቆ በቀል በመልቀም ጭምር ነዉ፡፡ ይህንንም አባባል ማክስ ግሩል እንዲህ በማለት ያረጋግጣል፡፡
“…በብዙ ሺህ ፓዉነዶች የሚመዘን የዓለም ምርጥ የቡና ፍሬ በየዓመቱ እየወደቀ በጫካዉ ጥላ ሥር የሚበሰባስበት አገር…” (ማክስ ግሩል ፣1932)
“…where thousands of pounds of the finest coffee beans in the world fall to the ground every year and not beneath the shade of the forests…” (gruhl, m. 1932)፡፡
{ካፋ የቡና መገኛ (በቀለ ወ/ማሪያም አዴሎ፡ የካፋ ሕዝቦች እና መንግስታት አጭር ታርክ፣ 2004/1996 ዓ.ም. ፡40-44}፡፡

ለካፋ ዞን ባለድርሻ አካላት/ባለስልጣናት (የካፋ ዞን ፓርላማ አባላት፣ የካፋ ዞን አስተዳደር፣ የካፋ ዞን ባህልና ቱሪዚም፣ ወዘተ.) እባካችሁ ለትውልዳችሁ የማይሞት ጥሩ ታሪክ ስሩ!!! ለማንኛውም የህዝብ የልማት ጥያቄ ሌት ተቀን ከልብ ስሩ፡፡ ከናንተ በላይ ለካፋ የሚቆረቆር ልመጣ አይችልም፡፡ በፍቅር ተባብረን ካፋን በማበልጸግ ለኢትዮጵያ እድገት ለአፍሪቃ ኩራት የበኩላችንን ሚና እንጫወት፡፡
SHIMEKIT TADELE GEBABO
19/05/2018፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: