Leave a comment

እኛ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ


 

– የባላባትና የጭሰኛ መደብ ብለው የተኮፈሱብን ፊውዳሎችን ያለምህረት ከጫንቃችን ላይ አሽቀንጥረን የገረሰስን

– ጣሊያንን ተዋግተን አሸንፈን በአርበኝነት የፎከርን

– የደርጉ መንግስት እናት ሃገር ወይም ሞት ብሎ መፈክር ሲያሰማ ለአንዲት ኢትዮጵያ ሀገራችን
ህይወታችንን ሳንሳሳ የገበርን

– የካፋ ክፍለሀገር ጠቅላይ ግዛት ፈርሶ በሲዳማ ክፍለሀገር ሥር ስንጠቀለል ያላመጽን

– ከ1000 ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዘን ሲዳሞና ወላይታን ሲናለማ እኛ ልባችን ሲደማ ትንፍሽ ያላልን

– ለዘመናት ጥረን ግረን ያለማናቸው እነ ሊሙ በበቃ ውሽውሽ ቴፒ በወንበዴ ሲዘረፍ ጎራዴ ያልመዘዝን ጥብመንጃ ያልወደርን

– ደናችን ተጭፍጭፎ ምደረበዳ ሲሆን አድማ ያልመታን በተቃውሞ ሰልፍ አደባባይ ያላጥለቀለቅን

– በመንገድ እጦት ሲንገላታ ክሊንክ ብርቅ ሆኖብን ሆስፒታል ሳይኖረን ድፍን 27 ዓመት ያስቆጠርን

-እኛው ጠረፍ ተከላካይ ድንበር ጠባቂ ሆነን ስናበቃ መሬታችን ተቆርሶ ሱዳን ሲሰጥ ሰሚ ያላገኘን

– በአብራካችን ክፋዮች ሆዳም ካድሬዎች በእነ ብርሃኑ አዴሎ፣ አድማሱ አንጎ፣ ክፍሌ ገብረማሪያም፣ ፀጋዬ ማሞ እና ሌሎች የቀን ጅቦች በቁማችን እየተበላን አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ የሆንን

– እኛ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ጭቁን ህዝብ 27 ዓመታት በሙሉ ተዘንግተን ኢትዮጵያዊነታችንን ተነጥቀን ግራ ሲያጋቡን ግራ ግራውን ስንጓዝ ለምን እንዴት ብለን በሃሳብ ከመሟገት በቀር ነፍጥ ያላነሳን

ብቻ እኛ ምን ያልሆነው አለ? ብዙ ብዙ ሌላ ሌላም ብዙ ብዙ ብዙ በደል በትከሻችን ተሸክመን አሁን ግን ከበደን ትከሻችንም ጎበጠ ወገባችንም ተሰበረ ግን ግን ማንም ሣያቀናን ማንም ሣይደግፈን ራሳችን በራሳችን ቀና ቀና ብለን ዙሪያ ገባችንን ሊናይ አምርረናል:: ተረተኞቹ ”ሞኝ ካመረረ,,,,,” ብለው ይሉ የለ ምንም እንኳን ገደብ የለሹ ትዕግስታችን እንደ ሞኝ ቢያስቆጥረንም ግን በቅቶናል።

ለማንኛውም ሐዋሳንም አሸብርቀናታል ወላይታንም አንቀባረናታል ያለፈው አልፏልና ክልላችን (የካፋ አስተዳደር አካባቢያችንን) ያለአግባብ እንደተወሰደ በትግል አስመልሰን ስናበቃ የተቀሩትን የመብት ጥያቄዎች በሂደት የምናስከብራቸው ይሆናል።

ይህ ካልሆነ ግን መንግስት ነኝ ባዩ በተንሸዋረረ ዓይኑ እኛን እኛነታችንን አስተዋይነታችንን ቅጥ ያጣውን ትዕግስታችንን ማየቱ የሚከፍለውን ዋጋ ምን አልባትም እጥፍ ድርብ ያደርገው ይሆናል፣ እኛማ መክፈል ያለብንን ድርብርብ ዋጋ መክፈል ከሚገባን በላይ ክፍለን ጨርሰናል።
ከዚህ በኋላ ተራው የመንግስት ነው እንዲህ ስንል ጉንጭ አልፋ ማስፈራራት እየቃጣን ሳይሆን የምራችንን እውነታችንን ነው።

መቼም በዚህ ጉዳይ ጠቅላያችን መተው ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ለምና አረንጓዴ ምድር እና እነእንቶኔን እነዚያን ስመጥር ጀግኖችን ያፈራች ታሪካዊ አከባቢ ብለው በለዘበ እና ማር በሚያዘንበው የቁልምጫ ንግግራቸው የህመም ማስታገሻ እንዲሰጡን ለአፍታም አናስበውም። ምን አላባት እሳቸው ቢያደርጉትም እንኳን ከወርቃማ ንግግሮቻቸው ይልቅ ፈጣንና ተግባራዊ ምላሽ ቢሠጡን ሳይሻላቸው አይቀርም።
እናም ይህ ቃል ከጎበዝ አለቃ እስከ ዘብ አለቃ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከባላገሩ እስከ ከተሜው ምሁሩ የእኛው የራሳችን ከበስተጀርባው አሸባሪም ተቃዋሚሚ አቃዋሚም አቋቋሚም የሌለበት እውነት እውነት ማንም የሌለበት እኛው ራሳችን እኛው ባለቤቶቹ የኛው ቃል ነው።

ካፋ ሚዲያ kaffamedia

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: