Leave a comment

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ የክልል ጥያቄ አዲስ ጠቅላይሚንስቴር ስለመጡ ሣይሆን ትዕግሥታችን የመጨረሻው ጫፍ ላይ ስለደረሰ መሆኑ ሊታወቅልን ይገባል::


በቀደመው ዘመናት ማለትም ከሁለት አስርተ ዓመታት በፊት ኢትዮጵያን ባስተዳደሩ (በገዟት) ሥርዓቶች የካፋ ጠቅላ ይግዛት በኋላም የካፋ ክፍለ ሀገር እና በደርግ ውድቀት ማብቅያ ወቅት ላይ የካፋ አስተዳደር አካባቢ ተብሎ ይጠራ የነበረው የኢትዮጵያ አንድ አካል የሆነው ግዛት በወያኔ የአስተዳደር ዘመን መናገሻዋ ጅማን ወደ ኦሮሚያ ሌሎችን በየራሳቸው ማለትም የም: ዳውሮ ዞንና ኮንታ ልዩ ወረዳን ጨምሮ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል ካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች: ማጂ ከ1000 (አንድ ሺህ) ኪሎ ሜትር በላይ አቋርጦ ወደ ሀዋሣ እንድንካተት ተደርጓል።

በመሆኑም በተለይም እኛ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አከባቢዎች ካፋ ፣ ሸካ፣ ቤንች: ማጂ፣ ጅማ: የም፣ ዳውሮና ኮንታ በባህል በቋንቋ እና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የአንድ ሣንቲም ሁለት ገፅታ ስንሆን እንደ አንድ ማህበረሰብ የምንቆጠረው ግን ደግሞ በታታሪነት: በታማኝነታችንና ብሎም በጀግንነታችን ታዋቂ የሆንን በትክክል ብንቆጠር ወደ 10 ሚሊዮን የሚገመት ህዝብ ቁጥር ያላው ታላቁ የኢትዮጵያ አካል ፍትሀዊ ባልሆነ መንገድ መብታችን ተደፍጥጦ ሠሚ ያጣ ጩኸት ስንጮህ ድፍን 27 ዓመታት ተቆጥሯል ።

በትክክለኛ እና በጤናማ አእምሮ ለሚያስብ ማንኛውም ዜጋ ከ1000 ኪ.ሜ. በላይ ሀገር አቋርጠን እንድንተዳደር መደረጉ ምን አልባትም ከአስከፊ የቅኝ አገዛዝ ወይም በቀድሞ አጠራር የባርነት ቀንበር የመጫን ያክል ነው ቢባል ማጋነን አይደለም።

የወያኔ መንግስት ለራሱ ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ተፈፃሚነት በተከተለው የተዛባ አሰራር እኛ ደቡብ ምዕራብ ዞኖች ራሳችንን ችለን እንደ አንድ ክልል መዋቀር አለብን ብለን በተለያዩ አጋጣሚዎች ጠንካራ ጥያ ቄ ብናነሣም የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ያለው አገዛዙ አልፎ አልፎ የእኛን ብሶት ለማስተጋባት የሞከሩ በርካታ ባለስልጣናት ደብዛቸው እንዲጠፋ ተደርገዋል።

እናም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ከተነጠቃቸው መብቶች መካከል ቅደም ተከተሉን ለማስጠበቅ ካልሆነ በስተቀር በርካታ አሣፋሪና በታሪክ ተወቃሽ የሚያደርጉ በድሎችና የግፍ ፅዋ እንድንጎነጭ ተደርጓል።

ደጋግመን እንደምንለው በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦችን በውስጣቸው አቅፈው የያዙ የቴፒ: የበበቃ: የውሽውሽ: የጎጀብ: የገማድሮ: የሊሙ ቡናና ሻይ ተክል ድርጅቶች ከዚህም ባለፈ በየዓ መቱ ለመንግሥት ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ እንደሚያስገቡ እየታወቀ ለወያኔ ጋሻ አጃግሬዎች በነፃ ተላልፈው እንዲሰጡ ተደርገዋል።

የሆነው ሆኖ በህዝቡና በአካባቢው ላይ እየተፈፀሙ ካሉት አሳዛኝና ተደራራቢ በደሎች ከብዙ በጥቂቱ ለመግለፅ ያክል እንጂ ለግዜው ቀዳሚው አጀንዳችን የክልል ጥያቄያችን በአስቸኳይ እንዲመለስ የሚል ይሆናል። መቼም የክልል ጥያቄያችንን ለማስመለስ “ክተት ሠራዊት: ምታ ነጋሪት” አለማለታችን እንደ ሞኝ አስቆጥሮን ለመብቱ እንደማይታገል ወኔ ቢስ አስፈርጆን ከሆነ ሀቁ ይህ አይደለም። እስከ ዛሬም የታገስነው ጊዜ ይፈተዋል ብለን መሆኑ ሊታወቅልን ይገባል።

በመሆኑም አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ሃገሪቱ በአዲስ ጠቅላይ ሚንስቴር ነገር ግን በአ ረጀና በአፈጀ የወያኔ ፖሊሲ የምትመራ ሲሆን ጠቅላያችን ተወሳስቦ እንደ ሸረሪት ድር ተተብትቦ የቆየውን የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር ለመመለስ እየተፍጨረጨሩ ሥለሆነ በዚያውም ለዘመናት ሲንከባለል የቆየውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ችግር በጅምላው እንዲመልሱልን እንዳልሆነ እሳቸውም ሆኑ ሌላውም አካል እንዲገነዘብልን እንሻለን ።
ስለሆነም በአዲስ መሪ ችግሩን እንደ አዲስ አድርገን በወረተኝነት አባዜ ሣይሆን ያመረርነው ብሶታችን ሞልቶ ሥለገነፈለ ትዕግስታችን የመጨረሻው ጫፍ ላይ ስለደረሰ መሆኑን ዙፋናቸውን ሀዋሳ ከተማ ያደረጉት የሲዳማው ንጉስ ደሴ ዳልኬና የፖለቲካ መዘውሩን በተንቆለጳጰሠ ንግግር የሚያምታታው ተስፋዬ ቤልጄጌና የቀድሞው ር/መስተዳደር የአሁኑ ዴኢህዴን ሊቀመንበር አቶ ሺፈራው ሽጉጤ ቶሎ በፍጥነት መክረውበት በዚህ መራር ጥያቄ ምክንያትና ውጤቱ እያቅለሸለሻቸውም ቢሆን አመዛዝነው የችግሩን አሳሳቢነት ለጠቅላያችን አስረድተው ውለው ሳያድሩ ለቆረፈደውና ለኮመጠጠው አቤቱታችን ፍትሀዊ ምላሽ እንዲሰጡ አበክረን እንጠይቃለን።

ነገር ግን እንደለመዱት ጉዳዩን እንደተራ አሉባልታና ረብ የለሽ ጩኸት አድርገው ቢመለከቱት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚጣሉት ከእኛ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሣይሆን ከመላው የዓለም ህዝብ ጋር መሆኑን ይረዱት። እኛ ይህን ስንል ማስፈራራታችን አለመሆኑን አውቀው በሠከነ እና ሚዛናዊ በሆነ እይታ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡን ነው። አበቃን ልብ ያለው ልብ ይበል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ
ካፋ ሚዲያ kaffamedia

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: