Leave a comment

በደልና ጭቆና የበዛበት የካፋ ወጣቶችና ሕዝቦች እሮሮ


የተከበሩ ሙፈሪያት ካሚል አክብሮት የተሞላባትን ሠላምታችንን እያቀረብን ከዚህ በታች ያለዉን መልዕክት ስናቀርብለዉ የሚቻሎትን ያህል እንደሚያግዙንና ከፍ ሲሉም መልክታችን በእርሶ አማካኝነት ለሚመለከተዉ የመንግስት አካል እንደሚያደርሱ ተስፋ የካፋ ሕዝብ በወከላቸዉ አመራሮች የፖለቲካ ትግል ራዕይ በስከት የሚነገርላቸዉ ታሪክ አለ ብሎ ለመናገር ያዳግታል ብቻ ሣይሆን ያሳፍራልም
ለሩብ ምዕተ ዓመት ያህል በዞኑ ብቅ ጥልቅ ሲሉ የቆዩት አመራሮች ይልቁንም የአሁን ዘመን አመራሮች አሉታዊ ጎናቸዉና ችግሮቻቸዉ ነዉ ሚዛን የሚደፋዉ
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አቢይ አህመድ የዴሞክሪስ ስርዓትን በአስተማማኝ ሁኔታ እንመሰርታለን ባሉበት በዚህ ወቅት ቁጥራቸዉ የበዙ የኦሮሚያ አመራሮች የተለያዩ ዞኖች የፖለቲካ ሹማምንት አመራሮች ላይ ሥር ነቀል ለዉጥ መደረጉን ብንገነዘብም በከፋ ዞን ብልሹ የፖለቲካ አመራሮች ላይ ምንም ዓይነት ለዉጥ አለመደረጉና በወቅቱ በእነዚህ አመራሮች ላይ አንዳችም እርምጃ አለመወሰዱ በከፋ ህዝብ ላይ ከፍተኛ የሆነ ስጋት አጥሎበታል::
በከፋ ዞን በፖለቲካ አመራርነት ዉስጥ የሚሰባሰቡ ሰዎች ለእዉነተኛ የካፋ ሕዝብ ለማገልገል የፖለቲካ ትግል ቁርጠኛ ከመሆን ይልቅ ለጥቅም ለስልጣን በወሲብ ቅሌት በኮንትሮባንድ ንግድ በክልል ከሚገኙ የሲዳማና የወላይታ ተወላጅ ለሆኑት ሹማምንቶች ቅጥረኛ በመሆን እርሳቸዉ በፈጠሩት ኔትወርክ እየተሣሣቡና እየተጠራሩ የሥልጣን ዕድሜያቸዉን በማራዘም ወደ ሀብት ጉዞ የሚያደርጉት አካሄድ የዞኑን ሰላም እና ዕድገት ወደፊት እንዳይጓዝ አድርጓል::
ይህን ያህል ለመግቢያ ያህል ካወጋን ሐዋሪያዉ ቅዱስ ጳዉሎስ ለገላቲያን ሰዎች በፃፈዉ በገላቲያ ምዕራፍ 5 ቁጥር 15 ላይ ድንቅ መልዕክቱ “ነገር ግን እርስ በእርሳቹ ብትነካከሱና ብትብላሉ እርስ በእርሳቹ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ” በማለት የእርስ በእርስ ግጭትንና ዉጠቱን መጠፋፋት እንደሆነ ያስጠነቅቀናል::
ከቅርብ ግዜ ወዲህ በከፋ ዞን ብሔርን መሰረት ያደረጉ “ጥቅምና ሥልጣኔ ይነካብኛል የሚል ስጋት ባለበት በአንድ አንድ አካላትና አመራሮች የተቀነባበሩ በሕይወት በንብረትና አካል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከተሉ ብጥብጥና ግጭቶች በተለይ በካፋ ዞን በግምቦ÷ በጎጀብ÷ በወሺ ÷ዲምቢራ ÷በሺሾ እንዴ ÷ጨና በቢጣ ÷በኦዳ÷ በሞዲዮ÷ በማንኪራ በዴቻ ጠሎ ጨታ እና በሌሎች አከባቢዎች ተስፋፍቷል : እንደ ካፋ ባሉ ኩሩ ጨዋ እና የመፈቃቀር እና የመተሳሰብ ባህል ባለዉና እርስ በእርስ እጅግ ዉስብስብ በሆነ መልኩ የተቆራኙ ህዝቦችን እርስ በእርስ ለማጋጨት የሚደረገዉ የመጠፋፋት ፖለቲካ ዉጤት ነገ በካፋ ሕዝብ ሊካካስና ሊተካ የማይችል የኢኮኖሚ የማሕበራዊ የስነ-ልቦና ጉዳት የሚያደርስ እንደሚሆን ግልፅ ነዉ::
ይህ የተወሰነ ፖሌቲካዊ ግብን ለማገኘት ስልጣንን ለማርዘም የፈፀሙትን ወንጀል ዱካ ለማጥፋት በሙስና በኮንትሮባንድ ንግድ ሰፊዉን ለም መሬት ለሲዳማና ለወላይታ ተወላጆች ሽጠዉ ባገኙት የኮምሽን ገቢ ከጎጀብ ኬላ በመዝረፍ የያቤ ግቻን ደን ጨፍጭፈዉ ሽጠዉ ያገኙትን ሀብት እንዳይነካባቸዉ በዝሙት ምግባራቸዉ ሴቶች ለሹመት የሚያጩበት አሰራር እንዳይመክንባቸዉ ሲባል የሚደረግ ከክልል እስከ ኮንትሮባንዲስቱ እና ዉሰን ደላሎችና የጥቂት የፖሌቲካ አመራሮች ሴራ በዋነኛነት በስልጣን ያለዉ አመራርና አካል የተቀነባበረ ሴራ ነዉ ስለዚህም ምክኒያት ለአብነት ያህል ለማንሳት
1ኛ የውስን አመራሮች ቤተሰቦችና የቅርብ ሰዎቻቸው ከፍተኛ ባለሐብትና የቅንጦት ነሮ ወዘተና የዚህ ሁሉ ሀብት ምንጩ ከያቤግቻ ደን ስጨፈጨፍ የነበረ የጣዉላ ሽያጭ ከጎጀብ ኬላ የሚወርሱ ቡና ÷ ዘይት ÷ ስኳር ያለጨረታ ተሽጦ ወደ አመራሮች ካዚና በገባ ገንዘብ መሆኑ
2ኛ ከዞኑ መምሪያ ሓላፊ ከሆኑት አመራር ጋር በመቀናጀት ከእዉቁ ኮንትሮባንድሲቶች ጋር አመራሮች በጋራ የሚሰሩት የኮንትሮባንድ ንግድ
3ኛ በሌሎች የወረዳ ከተሞች ያልተደረገ ነገር ግን በአነዲት የቀበሌ ከተማ በሆነችዉ በሺሾ እንዴ ከተማ የተሠራዉ የቴክኒኪና ሙያ ኮሌጅ ፣ ሁለት 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ ዘመናዊ ጤና ጣቢያና ሆስፒታል በወረዳዎች መሀል ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል አለመኖሩ
4ኛ በልማት ማህበሩ ሥም በራሳቸዉ ኔትወርክ ሕዝቡን ያላሳተፈ የሀብት ምዝበራ
5ኛ ብቸኛዉ የቡና ብሔራዊ ሙዚየም የከብት ማደሪያ ከመሆኑ ባሻገር የዞኑ ሕዝብ የልማቱ ተጠቃሚ አለመሆን
6ኛ የክልሉ መንግስትም ሆነ በፌደራል የሚሻሙ የሲዳማ የወላይታ የጉራጌ የከምባታ ተወላጆች ብቻ መሆናቸው ለዚሁም መግለጫ ይሆን ዘንድ በክልል የተወከሉት ሴቷ አመራር የካፋ ብሄረሰብ ሳይሆኑ የጉራጌ ብሔረሰብ ተወላጅ መሆናቸው ፤ሌላው በክልል ተወካይ የሆኑትም አመራር ሙሉ ዕድጌታቸው በከምባታ አካባቢ ከመሆኑ አንፃር የካፋን ብሄረሰብ ባህላዊ ትስስሩን የማያውቁ ሲሆን ደግሞም ሌላው ተወካይ ተብዬው ጨርሶ የከፈኛ ቋንቋን መናገር መስማት መፃፍ መንበብ የማይችሉ ሲሆን እነዚህ ሦስት ግለሰቦች ከዚሁ በላይ በተገለፀው ዝርዝር ምክንያት የካፋን ብሔረሰብ የማይወክሉ በመሆናቸው ካፋ ዞን እንደብሄር በክልሉም ሆነ በፌደራል ተወካይ የሌሌው ባይተዋርና ብቸኛ ብሔረሰብ አድርጎታል::
7ኛ በታሪክ አጋጣሚ በ2002 ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ምርጫ ላይ እኛን ካፋን በመወከል ሁሌም በፓርላማ የካፋ ሕህዝብን ችግር ከመንሣት ባለፈ ካፋ በፓን አፍሪካ ያገኘዉን ክብር እንዳይቀጥል የከፋ ህዝብ የምርጫ ታዛቢ መሆን አይችልም በሚል ግምት ከአዲስ አበባ ባመጡ ታዛቢዎች የምርጫ ኮሮጆ ተሠርቆ ወደ ጫካ በመሸሸግና በገዋታ ወረዳ የተገደለው የመንጃ ብሔረሰብ ተወላጅ በአመራሮቹ ድብደባ ህይወቱ ማለፉ እየታወቀ ህይወት ያጠፉ አመራሮችን ለህግ ሣይቀርቡ በሀሰት በአመራሮች ደባ ወጣት ኑረዲን አህመድ የመታሰር ጉዳይ ህገ ወጥ መሆኑ
8ኛ በኢንቨስትመንት የካፋ መሬት የተያዘው በትግሬና በሲዳማ ተወላጆች መሆኑ ለአብነትም አሰፋ ዱካሞ ዘላለም ኮሽፍሬ ሲሆኑ ይህም በውስን አመራሮች ኔትወርክ መሆኑ
9ኛ አንድ አንድ አመራሮች ከሰኞ እስከ እሁድ የመንግስት የመንግስት መኪና መመላለሻ ሀና ጠዋት ከጊንቦ ዲሪ ወረዳ ቦንጋ እራት እና ለአዳር እንዲሁ ከቦንጋ ወደ ጊምቦ ዲሪ መመላለሻ ታክሲ መሆኑና ተመላላሽ ባለስልጣናት መሆናቸው
10ኛ የዞኑ በጀት የሚያልቀው ረጅም ርቀትን ከካፋ ወደ ሃዋሳ በመጓጓዝ መሆኑ
11ኛ የዳኝነት ስራው በትዕዛዝ በሌሎች ትዕዛዝ ከወረዳ ፍርድ ቤት እስከ ክልሉ ሠበር ችሎት ደረጃዉን ያልጠበቀ የፍትህ አሰራር መሆኑ
12ኛ በተለያዩ ጉባኤዎችና ዉይይቶች ላይ ታላላቅ ያገር ሽማግሌዎችን ትተዉ ደላላዎችንና የአመራሮች ጆሮ ጠቢ የሆኑ ጥቂት ወጣቶች መሆናቸዉን ከብዙ በጢቂቱ ለአብነት የሚጠቀሱ ተግባሮች ናቸዉ ይህ በካፋ ዞን የተፈጠረው የአመራሮች ሴራ ተከትሎ የመጣዉን ጣጣና አደጋ ስፖንሰር ያደረገው ማንኛውም አካል ሄዶ ሄዶ ጉዳቱ ለሰፊዉ ህዝብና ለራሱም ጭምር መሆኑን ብያስብ መልካም ነዉ:: ከላይ እንደገለፅነዉ የነዚህ የአመራሮች ኔትወርክ በብዙዎች ሃገር የሚደረገዉ የመጠፋፋት ፖሌቲካ ተጎጅዉ ሁሉም ነዉ በነዚህ ጥቃቅን አመራሮች የፖለቲካ ቁማር ማንም አትራፊ መሆን አይችልም:: ይልቁንም ሁሉም ኪሣራ ዉስጥ ይወድቃሉ በዚች ሃገር ማንም ለማንም ተንኮል ብያስብና የጭካኔ ጉዞ ተጉዞ ፖለቲካዊ ትርፍን አመጣለዉ፣ ሃብት አካብታለዉ ብሎ ቢታታር ትርፉ ማቅ መልበስ ይሆናል ስንል አጭር መልክታችንን እያቀረብን ይህንን አንገብጋቢ የካፋ ሕዝቦችን ጥያቄ ለክቡር ጠቅላይ ሚነስተራችን አቅርበው በቅርብ ቀን በዞናችን ስር ነቀል ለውጥና ዘላቂ መፍቴ እንደምናገኝ እርግጠኛ በመሆን ነው፡፡ በደልና ጭቆና በበዛበት በካፋ ወጣቶችና ሕዝባችን ስም እናመሰግናለን እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!!ካፋንም የበረከቱ ተቋዳሽ ያድርግልን፡፡አሜን!!!!!!!!

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: