Leave a comment

በቦንጋ ከተማ በተደረገዉ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ዉይይት ላይ የተነሱ የህዝብ ጥያቄዎች


በዛሬ ዕለት በቦንጋ ከተማ በተደረገዉ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ዉይይት ላይ የተነሱ የህዝብ ጥያቄዎች መልስ የሚሹ ከመሆናቸዉም ባሻገር በብዙዎች ዘንድ ግርምትን ፈጥረዋል።

እንደሚታወቀዉ ዞኑ ከሌሎች ማዕከላዊ ዞኖች ጋር ሲነጻጸር ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልገዉ መሆኑ ከሁሉም ወረዳዎች በተወዉጣጡ ተወካዮች ያለጥርጥር ቀርቧል።

በብዙ የዞኑ ህዝብ ክፍሎች ትልቁ ትኩረት በተሰጠዉ በዚሁ ታላቅ መድረክ የዞኑ መሪዎችና ተመሪዎች ምን ያህል ተለያይተዉ ይኖሩ እንደነበርና ምንስ ያህል በደል በተመሪዎች ላይ ሲደርስ እንደነበር በዝርዝር ቀርቧል።

ከዚህም ባሻገር የብሔራዊ የቡና ሙዚዬም ባለቤት አልባ መሆን ከገዋታ ተወካይ ሴት አርሶ አደርም ሳይቀር ቅሬታ ቀርቧል።

ታዲያ ከላይ የተጠቀሱ ችግሮች እንዳሉ ሌላ ምን ግርምት እንደተነሳም ትንሽ ለመጠቆም ያክል:-

– የእኛ አከባቢ ደቡብ ከሚባለው ድርጅት በአስቸኳይ ተለይቶ የእራሱን አስተዳደር መመሥረት አለበት

– በክልል በዞና በወረዳዎች ሁሉ ያሉት ባለሥልጣናትና ካድሬዎች በአስቸኳው ከሥራቸው እንዲነሱና በምትካቸው ችሎታ ባላቸው በተማሩ አካላት እንዲተኩ

– የክልሉ ሆነ የዞኑ አመራሮች ለምን ከጠ/ሚ አቢይ ጋር እንዳልተደመሩ

– ሳይለም ላይ በሁለቱም አቅጣጫ ሃያ ሃያ ኪ.ሜ እርቀት የመብራት አገልግሎት ለሚሰጥ ሶላር ተብሎ 2 ሄክታር መሬት ተወስዶ ከቻይና ኮንትራክተር ጋር ለስራ ዉል ከተገባ በኋላ የገባበት ያለመታወቁ

– የዞኑም ሆነ የወረዳዉ አመራር ቦታዉን ተቀብሎ ውል ከገቡ በኋላ ስጠየቁ ለጉዳዩ እንግዶች ነን ማለታቸዉ

– የሳይለም ህዝብ የመሰረተ ልማት ጥያቄ የቀድሞ ጠ/ሚ/ር መለስ ዘናዊ ቢሮ ድረስ ሄዶ ለመጠየቅ እስከ አዲስ አበባ ሄደዉ በአንድ የዞኑ ተወካይ ተይዘዉ የኦነግ አባላት ናቸዉ ተብሎ ለእስራትና መከራ መዳረጋቸው

– ከቢጣ ሳይለም መንገድ እንዲሰራ 33 ሚሊዮን ብር በጀት ተይዞ ጥናቱ ካለቀ በኋላ የበላዉ ጅብ ያለመጮሁ

– በሁሉም ወረዳዎች ያሉ አርሶ አደሮች ያመረቱትን ቡና ለገበያ ማውጣት ህገ ወጥ ነው ሲባሉ ነገር ግን ቡናቸውን ቀምቶ ለራሱ የሚጠቀም ህገወጥ የሆነው የህግ አካል ህጋዊ መሆኑ

– በጣሊያንና ደርግ የተሰሩ ት/ቤቶችና ጤና ጣቢያዎች አገልግሎት እየሰጡ ባሉበት አሁን ላይ የሚሰሩ አመት ሳይቆዩ መውደቃቸው

– በዴቻ ወረዳ የመደመር ቲሸርት የለበሱ ወጣቶች ለእስር እንዲዳረጉ ልዩ ክትትል መደረጉ

– በጨታ ወረዳ አምቡላንስ ለአመራሮችና ሚስቶቻቸዉ ሰርቪስ እየሰጠ እናቶች መንገድ ላይ መውለዳቸው

– በጨታና ጠሎ ወረዳ ያሉ የቡና እንቬስትመንቶች ባለቤታቸው ያለመታወቁ……ወዘተ እና ሌሎች በጣም ብዙ በሳል ጥያቄዎች በዛሬዉ መድረክ የተነሱ ሲሆኑ
በኢፌደሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፌጉባኤ በተመራዉ በዚሁ መድረክ ዞኑ ለአስተዳደር ወስን በሚመቹ አከባቢዎች መከለል ሳገባው የደቡብ ክልል ዉስጥ መቀላቀላችን ከባድ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግር አስከትሎብናል ሲሉ ተሳታፊዎች ጠይቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በእንቬስትመንት ስም በህገ ወጥ የተያዙ መሬቶች ላይ መፍትሔ ልበጅ ይገባል ተብሏል።

የኢፌደሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፌጉባኤ ወ/ሮ ሙፌሪያት ከሚል በበኩላቸዉ በእንቬስትመንት ስም ያለ አግባብ የተያዙ መሬቶችን ዞኑ በአግባቡ ለይቶ እንዲያነሳም ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
የክልልና ሌሎች መሰረታዊ ጥያቄዎችም ደረጃ በደረጃ በሚመለከተው አካል እንደሚፈቱም ቃል ገብተዋል።

ከቦንገቾ
ካፋ ሚዲያ kaffamedia

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: