Leave a comment

በዘመነ ኢሕአዴግ ከህገመንግስት አንቀፅ 39 ጋር ተዳምሮ የመነጨ ከፋፋይ ቋንቋ።


በዘመነ ኢሕአዴግ ከህገመንግስት አንቀፅ 39 ጋር ተዳምሮ የመነጨ ከፋፋይ ቋንቋ።

አንቀፅ 39፣ ብሔር / ብሔረሰቦችና ህዝቦች፣ ክልል፣ አናሳ ኢትዮጵያውነታችንን የምንፈልግና የምንወድ ዜጎች ሁሉ፣ ይሄ አፍራሽና የሃገራችን የኢትዮዮጵያን ህልዉና አደጋ ላይ በመጣል ላይ ያለዉን አንቀፅ 39ና ተያይዞ የመጣ ቋንቋ ከኢትዮዮጵያ​ ​ህገመንግስት መፋቅ ያለበት አንደሆነ አናምናለን።

ከሕገመንግሥቱ ብቻ ሳይሆን ከአትዮጵያ ህዝብ መዝገበ ቃላትም መሰረዝ አለበት ብለን አናምናለን። አንቀፅ 39 አራት በቁጥር የተዘረዘሩ ሀሳቦችን ያዘለ ሲሆን፣ የብሄረሰቦችን ቋንቋና ባህል ስለማዳበር ከምናገረዉ​ ​ ከቁጥር 2 በስተቀር ቀሪዉ ሶስቱ ከፋፍይ ሃሳቦችን ያዘለና ከዚህ በፊት የነበረንን የአንድ ብሔርና ሕዝብ ትርጉም ያጣመመ​ ​ነው።

በህዋሃት ታልሞ በኢህአዴግ ተግባራዊ የሆነዉ አንቀፅ 39፣ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ካካተታቸው አንቀፆች ሁሉ አጅግ አወዛጋቢና ከፋፋይ፣ አልፎም ኢትዮጵያ የምንለዉን የአንድነት መርህና መጠሪያችን፣ አልፎም ከዘመናት በፊት በነበሩት አባቶች የተነደፈችና በአባቶቻችን ደም የቆመችዉን ታላቅ ሃሳብ(idea) የሆነችዉን ኢትዮጵያን፣ ለማጥፋት ሆን ተብሎ የተነደፈ በመሆኑ፣ የመደመራችን መሰረቱና የመጀመርያ እርምጃ አንቀፅ 39ን ከሕገመንግሥቱ መፋቅ መሆን አንዳለበት የኢትዮጵያን አንድነት ለሚፈልጉ ወገኞች መናገር የሚያውቁትን ማስታዎስ ብቻ ነዉ።

የአትዮጵያ ህዝብ ህልዉናዉንና መብቱን ለማረጋገጥ የግድ መገንጠል አልያም በመገንጠል ማስፈራራት የለበትም። አንቀፅ 39 የሚፈቅደዉ ይሄንኑ ነው። ይህ ለአትዮጵያ አንድነት አንደማይበጅ የሩቅ ታሪክ ማምጣት ሳያስፈልግ ሰሞኑን በጅጅጋ፣ በካፋ ጋዋታ አከባቢና በቴፒ በጉጂ እንዲሁም በሌሎችም የኢትዮጵያ አካባቢዎች፣ ለዘመናት አብሮ በመከባበርና በመፈቃቀር በኖሩት ኢትዮጵያውያን መካከል እየተፈጠረ ያለዉን ግጭትና የደም መፋሰስ መመልከት ይበቃል።

በደቡብ ምዕራብ አትህዮጵያም በሻካና፣ በካፋ ዞኖች ለጆሮ የሚቀፉ ተግባርት እየተፈፀሙ አንደሆነ ይሰማል። የዚህ ሁሉ መነሻ አንቀፅ 39ና ከዚያ ጋር ተያይዞ የመጣዉ የብሔርተኝነት መዘዝ ነው።

ላለፉት 27 አመታት በሕገመንግሥቱ የሰፈሩና በህዝቡ አፍ አንዲገቡ የተደረጉ የአንቀፅ 39 አጃቢ ቃላቶችም ይህንኑ የአንቀፅ 39ን ከፋፋይ አላማ አንዲደግፉ የተነደፉ ናቸው። በፈረንጆች ከ1991 በፊት፣ በሌላ አባባል ከኢህአዴግ መመስረት በፊት በኢትዮጵያ የነበረዉን ቋንቋ የምናስታዉስ ሁሉ መመስከር የምንችለው፣ አነዚህ ቃላቶች ከኢህአዴግና በተለይም ከአንቀፅ 39 ጋር አብረው የተወለዱ ከዚህ ቀደም በህዝቡ አንደበት የማይታዎቁ መሆኑን ነው። በቅድመ-ኢህአዴግ ዘመን ለሚጠየቁ የዜግነትና የብሔር ጥያቄዎችና የሚሰጡት መልሶች አነዚህ ነበሩ።
ዜግነት፣ አትዮጵያዊ
ብሔር: አትዮጵያዊ
አንድ ህዝብ፣ የአትዮጵያ ህዝብ አንጂ ህዝቦች የሚባል ቋንቋ አልነበረም::

ይሄም ማለት ኢትዮጵያ የአንድ ብሔርና ህዝብ ሀገር በቁጥር የበዙ ብሔረሰቦችን ያዘለች ሀገር እንጂ ብሔሮችና ህዝቦች ያሉባት ሀገር አልነበረችም።
በርግጥኢትዮጵያ ከዘመነ ነገስታት ጀምሮ የአንድ ብሔር ባህልና ቋንቋ የበላይነትን ይዞ የቆየባት ሀገር አንደመሆኗ ብሄርሰቦች በቋንቋቸዉ፣ መማርና ባህላቸዉን የማሳደግ ዕድል ማግኘታቸዉ ተገቢ መሆኑ ከአንቀፅ 39 ዉስጥ የሚወሰድ ብቸኛ ሃሳብ ነው​።

ይህች ብዙ ብሄረሰቦችን ያቀፈች የአንድ ህዝብና የአንድ ኢትዮጵያዊ ብሔር ሀገር ሁሌም ፍፁም ሆና ልጆቿ በእኩልነት ታይቶ እኩል አድል አግኝቶ የኖሩባት ሀገር ባትሆንም፣ ድክመቷን እያጠናከርን፣ በጎደለባት አየሞላን የምንገነባት ሀገር አንጂ ወደ ጎን ትተናት አማራጭ የምንቀይስባት መሆን የለባትም።

ከላይ በጠቀስኳቸዉ የኢሕአዴግ ቃላቶች ክልልና አናሳንም ጨምሬአለሁ። ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ስንወያይ ክልል ለከብት አንጂ የሰዉ ልጅ በክልል አይታገድም ያለዉ አገላለፅ ትርጉም ያለዉ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። አቀራራቢዉ አባባል የቀድሞዉ ክፍለ ሀገር ነበር።ክፍለ ሃገር አንድ አካባቢ የእትዮጵያ አካል መሆኑን ይገልፃል። ሁላችንም የአንድ አናት ልጆች መሆናችንን ያስታዉሳል።

ምንም አንኳን የቀድሞዎቹ 14ቱ ክፍላተ ሃገራት ማለት ባይሆንም ለምንመርጠዉ የሀገሪቱ የአስተዳደር ክፍል፣ ቀድሞ ከፋ ክፍለ ሀገር ፣ ሸዋ ክፍለ ሀገር ፣ ሲዳሞ ክፍለ ሀገር አንደሚባለዉ አዲስ የምንፈጥራቸዉ የክፍለ-አስተዳደር ስሞች ‘ክፍለ ሀገር’ የሚል ተቀፅላ ቢታከልባቸዉ ከማራራቅ ይልቅ ያቀራርቡናል ብዬ አምናለሁ።

አናሳ የተባለዉን አጠራር በተመለከተ፣ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ሰዉ አናሳ አይባልም። በቁጥር ብዙ ያልሆነ ለማለት ከሆነ፣ ኢትዮጵያ በቋንቋ ሃብታም የብዙ ሊቃዉንቶች ሀገር ናትና የተሻለ መግለጫ ብንፈልግለት ይበጃል።

አንቀፅ 39 መች ተጠነሰሠ፣ ዐላማዉስ ምንድነዉ?
ለምለዉ የቀድሞ የTPLF ሊቀመንበር የተናገሩትን መጥቀስ በቂ ነዉ።
ለዚህ ጥያቄ መልስ አንዲሰጡ የተጠየቁት የቀድሞ የTPLF ሊቀመንበር የነበሩና በሃሳብ መለያየት ምክንያት ስልጣናቸዉን ለቀዉ ከ30 አመታት በላይ በዉጭ ሀገር የኖሩት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ሲናገሩ፣ በአንድ ወቅት ላይ TPLF አጅግ አየጠበበ መጥቶ ስለትግራይ ብቻ በማሰቡና አስከመገንጠልም ጭምር የሚል ሀሳብ በማምጣቱ፣ ይህንን ኃይል መታገል አንዳለብን የተረዳን ለኢትዮጵያ ደሞክራሲ የምንታገል የድርጅቱ አካላት ለመከፋፈልና ድርጅቱን ለመልቀቅ ተገደናል ብለዋል። ዶ/ር አረጋዊ በመቀጠል አጅግ ያስደነቀን ጉዳይ መጀመሪያ ከነበረዉ ከትግራይ ዉስን አስተሳሰቡ ወጥቶ እትዮጵያን የማስተዳደር አድል ካገኘ በሁሗ TPLF ይህን ከፋፋይ አስተሳሰቡን በህገመንግስት ጭምር ማስገባቱ ነው ብለዋል።

አጅግ የምያሳዝነው በየብሔረሰቡ ወያኔ ያደራጃቸው ካድሬዎች ይሄንን የጥፋት መንገድ በመስበክ ህዝቡን ከፋፍለው መቆየታቸዉ ብቻ አይደለም። በቅርቡ ከ ዶ/ር አብይ መምጣት ጋር ተያይዞ የመጣዉን የአንድነትና የኢትዮጵያዊነት ብሩህ ተስፋ አይተናል። በሀገር ዉስጥና በዉጭ ሀገርም የዶ/ር ዓብይን አላማ በመደገፍ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ድጋፍና ደስታ አንደነበረ ሁላችንም የምናስታዉሰው ነዉ። ነገር ግን ዶ/ር አብይ ያስተማሩንን ትምህርት አጣጥመን ለኢትዮጵያችን በተስፋ በተሞላንበት ሰዓት የብሔር ዉይይቶች ከየቦታው ይሰማሉ። ተስፋ የምናደርገዉ ጊዜ ዘለቄታ የማያገኙ ኃላፊና ጊዜያዊ ዉይይቶች አንደሚሆኑ ነዉ። በርግጥ የአትዮጵያ ህዝብ ቀና መሪ ካገኘ አንድነትን አንደሚመርጥ በቅርቡ ለጠቅላይ ሚኒስትራችን በታየዉ ድጋፍ ስላየን ፣ ነገሮችን በተስፋና በትዕግሥት አንድንመለከት ይረዳናል።

ብሔርተኝነት ለአትዮጵያ አይበጅም። የኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄ ለመመለስና ብሶቱን ለመፍታት ከብሔርተኝነት የተሻሉ አማራጮች አሉ። ሕዝቡን በትክክል የወፕከሉ በህዝብ ተሹመው በህዝብ የሚሻሩ ተዎካዮች ያሉበት በፈረንጆች አባባል Representative Democracy በመባል የሚታወቀው መንገድ አንዱ አማራጭ ነዉ። Representative Democracy, ሚዛናዊነቱን ከጠበቀ የፌደራል አስተዳደር ስርዓት ጋር ፣ ብዙዎች ያደጉና በማደግ ላይ ያሉ ሀገሮች የሚጠቀሙት በተግባር የተፈተነ ሂደት አንደመሆኑ አንድነታችንን ጠብቀን የጎደለብንን መሙላት የምንችልበት ስርዓት ነው።

ለመገንባት የምንፈልገዉ አዉነተኛዋን democratic ethiopia ስለሆነ ለአትዮጵያ የተሻለ አማራጭ አለ የምትሉ ካላችሁ መሰማቱ መልካም ነዉ።

ኢትዮጵያዊነታችንንና፣ አንድነታችንን ለሰበኩት ለዶ/ር አብይ አህመድ ያሳየነዉን ድጋፍ፣ አሁን ደግሞ ብሔርተኝነትን በመቃወም የኢትዮጵያዊነት ህልዉናችንን ለማስከበር፣ አንቀፅ 39 ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከአትዮጵያ ህገ-መንግስት አንዲፋቅ አጥብቀን አንጠይቅ። የተለያዩ አዉሮፓዊያን መንግሥታት የጋራ መንግስት ባቋቋሙበት ዘመን፣ አለማስተዋል ካለሆነ በስተቀር፣ ከአንድነታችንንና ኢትዮጵያዊነታችን የተሻለ አማራጭ የለንም።

አትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር።
ከአማኑኤል
ካፋ ሚዲያ kaffamedia

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: