1 Comment

ማሳሰቢያ፣ ለመንግሥት ሃላፊዎች  


ማሳሰቢያ፣ ለመንግሥት ሃላፊዎች

 

በደቡብ ክልል ምዕራባዊ ዞኖች፣ ሰፊ ለም መሬት እያለ፣ ወጣቶች ብቻ ሳይሆኑ፣ በርካታ ገበሬዎችም ጭምር፣ መሬት እንደሌላቸዉ ለረጅም ጊዜ፣ በተደጋጋሚ ሲቀርብ የነበረ ጥያቄ ነዉ፡፡ ለምሳሌ ካፋ ዉስጥ ይህ ጉዳይ፣ በ1998 ዓ.ም. ለቀድሞዉ ጠ/ሚ/ (በወቅቱ የመንግሥት ተጠሪ ሚ/ር) እና የክልሉ ድርጅት መሪ ለነበሩት አቶ ሃይለማሪያም የቀረበ ሲሆን፣ በየጊዜዉ ለመጡ የክልሉ ሃላፊዎች የቀረበ ቢሆነም ተገቢዉን ምላሽ ግን አላገኘም፡፡

 

ማንም የሚያዉቀዉ በአገሪቱ ባለፉት አሥር ዓመታት የተደረገዉ የሰፈራ ፕሮግራም፣ በመንግሥት ታቅዶ፣ በየክልሉም በአባል ድርጅቶችና በክልል መንግሥታት መተግበሩ ይታወቃል፡፡ መንግሥትም ዕቅዱን ለአጋሮች ጭምር አሳዉቆ ድጋፍ ማግኘቱ የታወቃል፡፡ በደቡብ ክልል የታቀደዉ ሰፈራ ደግሞ ከዞን ወደ ሌላ ዞንና፣ ሰፋሪዎች በያሉበት ዞን ከአንዱ ወደ ሌላ ቦታ እንደሚሆን፣ የሚሰፍረዉ የቤተሰብ ብዛት ጭምር በመንግሥት ግልፅ ተደርጎ ነበር፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ለዓለም ጭምር ያሳወቀዉ ጉዳይ፣ አድሏዊ በሆነ መንገድ ከየዞኑ የሚደረገዉን ሰፈራ ዞኖች ራሳቸዉ እንዲደግፉት የደቡብ ክልል ትቷል፡፡ ሰፈራዉ በሙሉ የሚደረገዉ በምዕራብ ዞኖች ዉስጥ በመሆኑ፣ የተደረገዉ አድልኦም የተለመደ በመሆኑ፣ የሚገርም አይደለም፡፡

 

በዚህም መሰረት ሁሉም ተሟልቶላቸዉ፣ ከደቡብ ዞኖች ብዙ ኪ.ሜ. ርቀዉ ተጉዘዉ ሰፈራ ተደርጓል፡፡ ለእነዚህ ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ርቀዉ ለሰፈሩት ወገኖች፣ መሰረተ-ልማት ተሟልቶ፣ የእርሻ ግብዓት ተሟልቶ፣ ፀጥታዉ ተጠብቆ፣ ከፍተኛ እንከባክቤ ተደርጎ ነዉ፡፡ በሂደቱ ተቀባይ አካባቢዎች በራሳቸዉ ወጪ ክትትልና ድጋፍ አድርገዋል፡፡ የአካባቢዉ ህዝብ ግን፣ቀዬዉ በሰፈራና፣ በኢንቨስትመንት ስም ሲሸነሸንና፣ ሲዘረፍ፣ እያየ ህግ በማክበር ብቻ የበይ-ተመልካች ሆኖ ቆይቷል፡፡

 

ወደ ሌላ ቦታ ለማስፈር፣ መሰረተ-ልማትና ሌላ ድገፍ ማድረግ ያልቻሉ ዞኖችም በአጎራባች ወረዳዎች ከማስፈር ይልቅ፣ የተወሰኑ ወጣቶችን በያሉበት አካባቢ አደራጅተዉ፣ ለዘመናት ህዝቡ በወል ጠብቆ ይዞት የነበረዉን የግጦሽ መሬት በማከፋፈል፣ የግብር ይዉጣ ሥራ ሰርተዋል፡፡ በዚህ የተወሰኑ ወጣቶችን ዝም ማድረግ የተሞከረ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ግን መላ ህዝቡ ከስምንት ዓመታት ወዲህ የወተት የግጦሽ ቦታ በማጣት፣ ላምና ጥጃዋን ቀርቶ፣ ለቀለቡ የሚያርስበትን አንድ በሬ እንኳን መንከባከብ ስላቃተዉ ያለዉን ሁሉ ሽጦ ወደ ባሰ ድህነት ዕየወረደ ነዉ፡፡ የተወሰኑት ልጆቻቸዉን ከትምህርት አስቅርተዉ ላማስጠበቅ ሲመክሩ፣ ልጅ የሌላቸዉ አሮጊቶችና ሽማግሌዎች ደግሞ ከአቅማቸዉ በላይ የከብት እረኛ መሆን መፐክረዋል፡፡

 

በአሁኑ ወቅት ህዝቡ፣ ከመቶ ዓመት በፊት እንደሆነዉ፣ ወተት ቀርቶ፣ እበት እንኳን መናፈቅ ጀምሯል፡፡ የመሬት ጥበት ባለባቸዉ የአገሪቱ አከባቢዎች እንኳን፣ እስካሁን የተንጣለለ የጋራ የግጦሽ መሬት ተከልሎ፣ እንስሳት ይርመሰመሳሉ፡፡ በተቃራኒዉ፣ ከዞን ዉጪ ለሚደረግ ሰፈራና ለኢንቨስትመንት መሬት እየተመደበ ባለበት አካባቢ፣ ለዉስጥ ሰፈራ ድጋፍ አይደረግም በማለት፣ ጥቂት ወጣቶችን በግጦሽ መሬት እንዲሰፍር ማድረግ፤ ህዝቡንም ከብቶችህን በየጓሮህና፣ በማሳህ ዉስጥ ጠብቅ፣ ካልሆነም ሽጥ ማለት፣ በዚህም ህፃናትን ያለ ወተት፣ ገበሬዉን ያለበሬ ማስቀረት ለህዝብ ከቆመ መንግሥት የማይጠበቅ፣ ሌላዉ ታሪክ ይቅር የማይለዉ ግፍ፡ ሲሆን ዉጤቱም አስከፊ ነዉ፡፡

 

አሁን ደግሞ ወጣቱ መሬት ሲጠይቆ ቆይቶ፣ ተስፋ ሲቆርጥ፣ ከተለመደዉ አካሄድ ዉጭ፣ በራሱ መንገድ ከኢንቨስተሮች የተረፈዉን ደን መከፋፈል ጀምሯል፡፡ በመሰረቱ ወጣቱ በዚህ መንገድ ደኑን መዉረሩ አይደገፍም፡፡ ጥያቄዉ ግን ሰርቶ ማደግ ከሆነ በአግባቡ ሊፈታለት ይገባል፡፡ የወጣቱ የመሬት ጥያቄ ሰርቶ ለመልማት ከሆነ፣ እንደሌሎች ወጣቶች፣ በተገቢዉ መንገድ ሊደገፍ ይገባል፡፡ በመሆኑም የነበረዉ አመራር ቢያበላሸዉም፣ አሁን ያለዉ መንግሥት ይህንን ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥቶ፣ አድሎዉን እንዲቀለብስ፣ በቃሉ መሰረትም፤ በጥናት ላይ ተመስርቶ፣ ደኖችን በማይነካ መንገድ፣ ለመሬት አልባ ወገኖች በሙሉና፣ በተለይም ለወጣቶች፣ በህጋዊ መንገድ፣ የመሬት ዕደላ እንዲያደርግ ይገባል፡፡ ለሌሎች ሰፋሪዎች እንደተደረገዉም፣ የክልሉ መንግሥት፣ በጀት መድቦ፣ ድጋፍ ማድረግ፣ መሰረተ-ልማት ማሟላት፣ ዘር፣ መሳሪያና ሌሎች ለመቋቋም አስፈላጊ ነገሮችን መደጎም፣ በሰፈራዉም አካባቢ ፀጥታዉን ማስጠበቅ ይጠበቅበታል፡፡

 

ይህ ካልሆነ ግን ግልፅ የሆነ ማግለል፣ ንቀትና፣ ጥላቻ እንደቀጠለ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በአግባቡ ባልተመራ ሁኔታ፣ ወጣቱ በዙሪያዉ ያለችዉን የቀረችዉን ደን ካወደመ፣ ጉዳቱ የአገርና የዓለም ሁሉ መሆኑም ሊታወቅ ይገባል፡፡ እየታየ ያለዉ ግጭት፣ የንብረት ዉድመትና፣ አሁን ደግሞ ከጫፍ እስከ ጫፍ ደን ላይ መስፈር ትክክላኛ መንገድ አይደለም፡፡ ሥራ ያጣ፣ ኑሮዉ በመንገድ ላይ የሆነ፣ ወጣት ግን ከሁዋላዉ የሚገፋፋዉ ሃይል ካለ፣ ሊገነፍል ይችላል፡፡ መንግሥት ህዝቡን ማወያየትና ማደራጀት፣ ለቁልፍ ችግሮች ፍትሃዊ መፍትሄ መስጠት፣ ህግና ሥርዓት ማስከበር ይጠበቅበታል፡፡

ከG.C

ካፋ ሚዲያ kaffamedia

One comment on “ማሳሰቢያ፣ ለመንግሥት ሃላፊዎች  

  1. Who cares? I am recording the progress since this article was poted. In fact I am very clear about what is written and expected that someone would take note of this. It is a pity; now the current mini-topic is the case of property rights of Coffee. The story will go on. Everyone seems pathetic; no one analyses, no one plans, no one forecasts and puts this in to a plan from all sides. I predict the agenda for tomorrow is Kaffa Regional State or death. I am quite confident that the property right will be declared. Already the Ministry has apologized; which is a lazy game for me. People will demand more in this line and maybe will get it. Can we start doing things the right way? Can we change the viscous cycle to virtuous cycle?

    Dr Habtamu A.A.

    Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: