1 Comment

አቤልና ቃየል ከአንድ አባትና እናት እንደተወለዱ ካፋና ሸካም ከአንድ እናትና አባት የተወለዱ ወንድማማች ናቸው


አቤልና ቃየል ከአንድ አባትና እናት እንደተወለዱ ካፋና ሸካም ከአንድ እናትና አባት የተወለዱ ወንድማማች ናቸው

“የእውነት ኣምላክ ዝም ኣትበል ስላለኝ” ኣለ የካፋ ኣንበሳ በካፍና ሸካ መካከል የተፈጠረው ኣላስፈላጊ ችግር ያሳሰበው ወጣት እናም “የእውነት ኣምላክ ዝም ኣትበል ስላለኝ” ሲል እውነታውን ለመመስከር ኣስተያየቱን በFB ላይ አሰፈረ እኔም የሱን ኣስተያየት ተመርኩዤ ለመፃፍ ተነሳሳሁ::
በርግጥ በዘመናችን ነቢያት የሉም;: ነገር ግን እግዚአብሔር በኣንድም በሌላም መንገድ ይናገራል የሚናገረው በሰው ኣድሮ ነው:: ከቅዱስ መፅሐፍ እንደምንረዳው ከክርስቶስ ልደት በፊት እግዚአብሔር በየጊዜው በተነሱ ነቢያት ላይ ኣድሮ ለእስራኤላውያን መልእክት ያስተላልፍ ነበር ሲያጠፉም ሲያለሙም በመጨረሻው ግን ለኣንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በነቢያት መልክት ማስተላለፍ ኣቆመና እራሱ ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ተወልዶ በኣካል በምድር ላይ በመመላለስ ኣስተምሮ በመጨረሻም ሐዋርያትን ኣሰልጥኖ እንዲያስተምሩ ውክልና ሰጥቶ ዳግመኛ የሚመጣው ለፍርድ መሆኑን ገልፆ ወደመጣበት ወደ ስማይ ኣረገ ሐዋርያትም ትምህርቱን ከኣፅናፍ እስከ ኣፅናፍ እያስተማሩ ከኛ ዘመን ኣስተምሮታቸው ደረሰ::

ይህን ያነሳሁት ሐዋርያዊ ስብከት ለማሰማት ሳይሆን እግዚአብሔር በኣንድም በሌላም መንገድ ይናገራል ኣድማጭ ከተገኘ ለማለት ነው::

በመሰረቱ ሸካ ማነው? ካፋስ?? ከታሪክ እንደምንረዳው ካፋና ሸካ የኣንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ኣንድ DNA ኣንድ ደም ያላቸው ወንድማማች ህዝብን ሁለት ህዝብ ኣድርጎ ለመከፋፈል ለመጠቀም ወንድማማችን ከማጣላት እርስ በርስ በማጨፋጨፍ ትርፍ ለማግኘት መሞከር ያለፈበትና የከሰረ የፖለቲካ ኣካሄድ ነው:: ሁለት ዝሆኖች ቢጣሉ የሚጎዳው ዝሆኖቹ የቆሙበት መሬት ላይ የበቀለው ለምለም ሳር ነው ካፋና ሸካን ያልሆነ የሆኑውን ውዥንብር
በተለያዩ መንገዶች በማሰራጨትና በማተራመስ የመጣውን ለውጥ እንዲቀለበስ በዚህም ካፋና ሸካ በህብረት ኣንድ ሆነው ከቆሙ ጥንካሬ ስለሚኖራቸው ጥቅማችን ይቆማል ብለው የፈሩ ወገኖች እያደረጉ ያለው ነጥሎ የመምታት እስትራቴጅና ሴራ እንጂ በእውነት ለሸካ ህዝብ ከመቆርቆር የመነጨ በጎ ሀሳብ ኣይደለም::

ሌላው ጉዳይ ኣማራን ማእከል ኣድርጎ ሸካን ኣማራ ከኣካባቢየ ውጣ ሲል ካፋ ከጎናችን ኣልቆመም በሚል ሰበብ ካፋን ካማራና ከሸካ ህዝብ ጋር የማናቆር ሥራ ሲሰራ ሽማግሌዎችና የሀይማኖት ኣባቶችም ሆነ ሌሎች ዳር ቆመው የሚመለከቱት ምን እስከሚሆን ነው??? ከሚኒሊክና ከኦሮሞ ወረራ በፊት የዚህ ኣካባቢ ህዝብ ራሱን የቻለ መንግሥትና ከዘመናችን የዴሞክራሲ ኣስተዳደር ያልተናነሰ ሚክረቾ (ፓርላማ) የነበረውና ምርጫ በህዝብ ድምፅ የሚወስንና ህዝብ መሾምም መሻርም የሚችልበት የኣስተዳደር ስርዓት እንደነበረው ታራክ ይነግረናል ታዲያ ዛሬ ያለው የዚህ ኣኩሪ ታሪክ ባለቤት ምን ነክቶት ነው እንደዚህ ኣይነት ታይቶና ተስምቶ ከማይታወቅ ብጥብጥ ውስጥ እየገባ ያለው??? ቆም ብሎ ማስተዋል ለምን ተሳነው?? ካለፈውስ ስህተት ለምን ኣይማርም?? በ1897 ዓም የወራሪውን የሚኒልክ ጦር 9 ወር የፈጀ እልህ ኣስጨራሽ ጦርነት በወራሪው የበላይነት እንዲጠናቀቅ ያድርረጉ ታሪክ ይቅር የማይላቸው ከህዝቡ መካከል የወጡ በጊዞያዊ ጥቅም የተደለሉ በመጨረሻም መጠቀሚያ ከተዱረጉ በኃላ የተገባላቸውን የስልጣን ቃል ኪዳን ባለመተግበሩ ለራስ ወልደጊዮርጊስ ወታደር በባሪነት ተላልፈው እንደተሰጡና ህዝቡ 3/4 እንዲገደል ሌላው እንዲሰደድና እስከዛሬ ኣስተዳደራዊም ሆነ ኢኮኖማያዊ ግፍና በደል እንዲሁም ሞራላዊና ሳይኮሎጂካዊ ተፅእኖ ያመጡበትና ለዛሬው ኃላ ቀርነት ምክንያት የሆኑና በዘመኑ በማህበራዊዉም ሆነ በኢኮኖሚው ታላቅ የነበረው ህዝብ ያሳነሱ ግለሰቦች ዛሬ ደግሞ በዘመናዊ ኣጠራር ካድሬዎች በውስጡ ተሰግስገው ጥቅማቸውንና ሥልጣናቸውን ለማስጠበቅና የመጣውን ለውጥ ለመቀልበስና ወደኃላ ለመመለስ ዋናው ስትራቴጅኣቸው ህዝብን ከህዝብ ማጋጨት መሆኑን የሸከቾም ሆነ የኣማራው ህዝብ መገንዘብ ይኖርበታል::

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት በተለያየ ምክንያት ወደ ኣካባቢው የሚመጣውን ማንኛውንም ብሔር ብሔረሰብ ተቀብሎ ሲያስተናግድ ዘር ጎሳና ብሔር ሳይለይ የኖረ የዋህና እንግዳ ተቀባይ ህዝብ የእጁን ኣላገኘም:: እንደሞኝ ተቆጥሮ በገዛ መሬቱና ሀብቱ ሌሎችን ባለፀጋ ሲያዱርግ እርሱ ደህይቶ የኖረ ህዝብ ሊከበርና ሊደነቅ ይገባዋል:: የደቡብም ሆነ የደቡብ ምራብ ኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ለሰሜኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ባለውለታ በመሆኑ ሊመሰገን ይገባዋል:: ለምን ቢባል ኣካባቢው በድርቅ በተጎዳበት ዘመን መጠለያ የሆነው የዚህ ኣካባቢ ህዝብ መሆኑ መዘንጋት የለበትም:: የዚህን ኣካባቢ ህዝብ ልዩ የሚያደርገው እንግዳን የመቀበል ልምድ እንጂ እንግዳ ሆኖ ወደ ስሜንም ሆነ ወደ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ኣልፈለሰም ርሀቡንም ጥማቱንም ተፈጥሮ በሰጠው ፁጋ ከመጠቀም ውጭ::የማንንም እርዳታ ሳይጠይቅ ራሱ በራሱ እያስተዳደረ ያለ ኩሩ ህዝብ ነውና ቴፒ ላይ ያለው ኣማራ በእውነት ሸከቾ ይውጣ ብሎ ከሆነ ዘመኑ የይቅርታ ስለሆነ ይቅርታ ጠይቆ በሰላም ኣብሮ መኖር ኣለብት እንጂ በእንግድነት መጥቶ ያስተናጉዱውን ህዝብ ይዉጣ ማለት ያጎረሰበት እጁን መንከስ ይሆናል ጥንቃቄ እናድርግ::

በተረፈ ሸካና ካፋን ለማቃቃርና የተጀመረውን ለውጥ ለመቀልበስ ደፋ ቀና የምትሉ በወንድማማች መካከል መግባትና ማለያየት ጊዜው ያለፈበት ስለሆነ ህዝቡን ለከፋ ብጥብጥ መቀስቀው ውሎ ኣድሮ ዋጋ ያስከፍላልና እጃችሁን ስብስቡ::

በመጨረሻም የእድሜ ባለፀጋ የሆናችሁ የኣካባቢው ኣዛውንት ጉድጏዳችሁ የተማሰ ልባችሁ የተራሰ በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ እንድታገኙ ኣጥብቃችሁ መሥራት ይጠበቅባችኃል:: ከዚህ ባሻገር የሀይማኖት ኣባቶችም በዚህ ጉዴይ ላይ ልታስቡበት የሽምግልና ሥራ መስራትና ማስታረቅ በሶማሌ ክልል የደረሰው ትምህርት ሊሆን ይገባል

መንግስትም ጉዳት ከደረሰ በኃላ ሽር ጉድ ኣይበጅምና ሰላምን ማስከበር ይጠቅማል ሰነፍ እረኛ ከሩቅ ይመለሳል

ወጣቶችም እባካችሁ ህይወት እንዳይጡፋ ንብረት እንድይወድም የበኩላችሁን ኣስተዋፅኦ ኣድርጉ ስሜታዊ ከመሆን ተቆጠቡ

እንደ ኢሳት ያለ ታላቅ ኣስተዋፅኦ ያለው ሚድያ የተዛባና ኣድሏዊ የሆነ መረጃ ዘግቧል የሚል ቅሬታ ከሸከቾ ሰብኣዊ መብት ተከራካሪዎች የቀረበ ስለሆነ ራሳችሁን መፈተሽና ለህዝቡ መግለፅና ለወደፊቱ ስህተቱ እንዳይደገም ያስፈልጋል:: በቱጨማሪ ኢሳትም ሆነ ሌሎች ሚዲያዎች ይህን ኣካባቢ እንደ የእንጀራ ልጅ አድርጎ ከማየት ብትቆጠቡና እንዳስፈላጊነቱ የዜና ሽፋን ብትሰጡ ያስመሰግናችኃል

ከዚህ ውጥ የደቡብ ሚድያ ተብየው ምን እየሰራ ይሆን???
ፋንታዬ መኮ
ካፋ ሚዲያ kaffamedia

One comment on “አቤልና ቃየል ከአንድ አባትና እናት እንደተወለዱ ካፋና ሸካም ከአንድ እናትና አባት የተወለዱ ወንድማማች ናቸው

  1. የካፋና የሸካ ጉዳይ በጥልቀት መታየት የሚገባዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ ሁለቱም የአንድ ህዝብ (የጎንጋ ህዝብ አካል) መሆናቸዉን፣ ብዙ የታሪክ ምሁራን ጽፈዋል፡፡ ከጎንጋ ህዝቦች መሃል በኩታ ገጠም መሬት ላይ የሚገኙ በቋንቋም ሆነ በባህል ከሌሎቹ የጎንጋ ህዝቦች ይልቅ የሚቀራረቡ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ወንድማማች ሆነዉም፣ ሁለቱም በየራሳቸዉ ንጉሥ ሲተዳደሩ የነበሩ፣ በተከታታይ በተደረገባቸዉ ወረራ የተደፈጠጡ ናቸዉ፡፡ ቀድሞ የሸካ መንግሥት ድል በሆነበት ጊዜም፣ በወቅቱ ተደጋጋሚ ወረራዎችን የመከተ ሲመልስ በነበረዉና እስከ 1889 ዓ. ም. ነፃ ወደ ነበረዉ የካፋ መንግሥት የተሰደደዉን የሸካ ንጉሥና የተከተለዉን ህዝብ ተቀብሎ በዴቻ ወረዳ አስተናግዶት ነበር፡፡ ከዚያም ካፋ፣ የሸካን ንጉሥና ወታደሩን በወታደራዊና ድርጅታዊ ጉዳዮች ደግፎትና አጠናክሮት፣ ሸካ ተመልሶ የራሱን መንግሥት ማቋቋሙን እስከዛሬም ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ እንዲያዉም በርካታ የሸካ ሰዎች ዛሬም ካፋ ዉስጥ በተለይም ዴቻ ወረዳ ዘመዶች እንዳሏቸዉ ይናገራሉ፡፡ ዓላማቸዉ ምን እንደነበረ ባይታወቅም፣ በአንድ ወቅት የደቡብ ገዢዎች በአቶ ቢተዉ በላይ ትዕዛዝ ሁለቱን ዞኖች አንዲቀላቀሉ በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት፣ ካፈቾ-ሸካቾ የሚባል ዞን ተመስርቶ ነበር፡፡ ገና ጥንትም ራሳቸዉን ችለዉ በሁለት ተደጋጋፊ መንግሥትነት ሲተዳደሩ የነበሩ ህዝቦች፣ ያለምንም ዉይይትና የህዝብ ተሳትፎ ሲጨፈልቁ፣ በተለመደዉ ታዛዥነትና ጉዳይ ፈፃሚነታቸዉ የሁለቱም ዞኖች ካድሬዎች እንደተባበሩ ይታወቃል፡፡ ቢሆንም፣ ታሪክን የህዝቡንና የካድሬዎቹን የራሳቸዉን ሥለ ልቦና ያላገናዘበ፣ ምንም ዓይነት ቅድመ-ዝግጅትና ዉይይት ያልተደረገበት፣ በትዕዛዝ የተመሰረተ ዞን ስለነበረ፣ እንደገና ተመልሶ ሁለት ዞኖች ሆነዋል፡፡ በአንድነት በነበሩበት አጭር ጊዜም፣ አርቆ አሳቢ የሸካ እና የካፋ ልጆች፣ ህዝቡ ተቻቻሎ አብሮ እንዲቆም ብዙ ለፍተዋል፡፡ በዚህም ወቅት ግን ሁለቱን ህዝቦች ለማጋጨትና፣ ለማናቆር ብዙ ጥረት በተደራጀ መንገድ ሲካሄድ ነበር፡፡ የቅስቀሳዉን ዓላማና ምንጭ ያልተረዱ ሁሉ የዚህ ሰለባ ሲሆኑ፣ ካፋና ሸካ እንደገና ተመልሰዉ፣ ሁለት ዞኖች በመሆናቸዉ የየዞኑ ሃላፊ ለመሆንና ከዚህች የምትገኘዉን ጥቅም ቅድሚያ የሰጡ ካድሬዎችም በዚህ የመናቆር ሂደት ላይ ነዳጅ ከማርከፍከፍ ጀምሮ፣ ዉስጥ ዉስጡንና በግልጽም በመቀስቀስ ተስትፋዋል፣ መርተዋል፡፡ ቢቻልማ ኖሮ የአስተዳደር መዋቅር ማብዛት፣ ለመንገድ፣ ለዉሃ፣ ለት/ት ቤት ወዘተ ሥራ ሊዉል የሚገባዉን ዉስን በጀት ከመፍጀት ያለፈ የሚያመጣዉን ጥቅም መረዳት ይከብዳል፡፡ ያለዉን የተማረ የሰዉ ሃይልም በማቀናጀት የተሻለ ሥራ መሥራት ባስቻለ ነበር፡፡ ቢሆንም ያለዝግጅትና ያለህዝብ ዉይይት በቀጭን ትዕዛዝ የተደረገ በመሆኑ፣ ህዝቡም ሆነ ካድሬዎቹ ራሳቸዉ ያልተዘጋጁቡትና ያልተቀበሉት በመሆኑ፣ አንድነቱ ያልተዋጠላቸዉ ወገኖች ደግሞ በበኩላቸዉ ያደረጉት ቀስቀሳ ታክሎበት በተናጠል ለደቡብ ገዢዎቻቸዉ ያጎበደዱ፣ ሁለት አስተዳዳሪዎች፣ የመምሪያ ሃላፊዎችና፣ እጥፍ ቁጥር ያለዉ የመንግሥት ሰራተኛ ያሏቸዉ ሁለት ዞኖች ሆኑ፡፡ በዚህ መቀጠሉ እንዳለ ሆኖ፣ የህዝቡን አንድነት ለትዉልድ ለማስተላለፍ፣ በአንዳንድ ምሁራን አነሳሽነት፣ የጎንጋ ህዝቦች ቋሚ የግንኙነት መድረክ ተጀምሮ ነበር፡፡ ይህም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከስሟል፡፡ አሁን ደግሞ በቴፒ አካባቢ አብሮ በኖረዉ ህዝብ መካከል የህዝብ ለህዝብ ግጭት እንዴት ተጀመረ፣ ይልቁንም፣ ካፈቾንና ሸካቾን ለማቃቃር የተደረገዉ ለምን ዓላማና በማን ነዉ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነዉ፡፡ አንዳንድ ምልክቶች ግን ከሁዋላ አንድ ሃይል ይኖር ይሆን የሚያሰኙ ሲሆን፣ በስሜት ከመነዳት መራቅ እንደሚያስፈልግ፣ ሁሉንም በጥንቃቄ ማስተዋል፣ ስለህዝብ ከመናገር፣ ህዝብን ከመፈረጅ እና ዘላቂነት የሌለዉ እርምጃ ዉስጥ ከመሳተፍ እንድንቆጠብ ያሳያሉ፡፡ በመሆኑም፣ በህዝብ ላይ ከመነሳትና፣ እንደህዝብ ከመተቻቸት በፊት ማጣራቱ ይበጃል፡፡ ካፈቾና ሸካቾም ሆነ፣ ሸካቾና አማራ የሚጣላበት ምክንያት የለዉም፡፡ ጊዜ ዕዉነቱን እሲያወጣ መታገሥ ተገቢ ሲሆን፣ በግልፅና በአደባባይ መወያየቱ ግን ሊቀጥልና ዕዉነቱን ሊያወጣ ይችላል፡፡

    ኬቶ

    Liked by 1 person

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: