Leave a comment

ሁሉም ያልፋል ሼሁ ግን ዳግም በህይወት የኢትዮጵያን ምድር ኣይረግጧትም በተለይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያን ምድር::


 

ኢትዮጵያን ከኣየርዋ እስከ ከርሰ ምድሯ ጠንቀው የሚያውቋት ሼህ ኣላሙዳን ከእስር ተፈተው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ቀን ነገሩ እንደዚህ ግልብጥብጥ ብሎ ሲጠብቃቸው ምን ይሉ ይሆን??? የሚል ቪድዮ ኣዳመጥኩና የመጣልኝን ሀሳብ በተለይ ሀብቱን ሙጥጥ ኣድርገው ባዶ ያስቀሩት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ትዝ ኣለኝ ተፈተው ቢመጡ እናንተ ምን ትላላችሁ እኔ የምለውን ኣልኩ

 

ሁሉም ያልፋል ሼሁ ግን ዳግም በህይወት የኢትዮጵያን ምድር ኣይረግጧትም በተለይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያን ምድር ለምን ቢባል ህዝብ ከተኛበት በድምገት ባነነ:: ኣይገርምም???

 

ሼሁ ከዘሩኛነታቸው የተነሳ ከደቡብ ምዕራብ ዘርፈው ወልድያ ላይ ሄደው የትውልድ መንደሬ ብለው የተንጣለለ ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት ማዘውተሪያ ስታድየም ሲሰሩለት (ኣኝከህ ኣኝከህ ወደ ወገንህ ዋጥ) ለታዋቂ ግለሰቦችና ኣርቲስቶች በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ኣፍሰው ሲሰጡ ከኢትዮጵያ ኣልፈው ለክሊንተን ፋውንዴሽን (Clinton Foundation) 20 ሚላዮን ዶላር ሲረዱ (Hilary Clinton campaign) የበበቃን ቡና የውሽውሽ ሻይ ልማት ኢንቬስተር ስም የህዝቡን መሬቱን ብቻ ኣይደለም ደሙን ሲመጡ ለ27 ኣመት ቁጭ ብለን ኣየናቸው:: ኣንድ ትንሽየ የጨርቅ ኳስ መጫወቻ ሜዳ ስልሰሩለትም ሌላው ቢቀር ውሽውሽ የተንጣለለ ሜዳ ትንሽ ቦታ እንኳ ወስደው ትንሽየ የድፖርት ማዘውተሪያ ስሩልን ልማልት ድፍረቱም ኣልነበረንም:: መንገድ ት/ቤት ክሊኒክ ፋርማሲ ሆስፒታል ጤና ጣቢያ ማን ደፍሮ ጠይቆ በኣካባቢው ህዝብ ይኑር ኣይኑር ሼሁ የሚያውቁት ነገር የለም ሰውን ጫካ ውጦታል ሰውማ ቢኖር ሌላው ቢቀር ከላይ የተጠቀሱት መሠረተ ልማቶች በቱሱሩ ነበር:: ትንሽየ ለሠራተኛ የስፖርት ማዙውተሪያ እንኳን ድርጅቱ ጊቢ ማቋቋም ማንን ገደለ?? የሚገርመው የካፋ ባለሥልጣናት ኣርቲስቱና ሴቱ ብር ሲዝቅ ይህ ሀብት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ መሆኑ ኣንድ ቀንም ትዝ ብሏቸው ኣያውቅም ኣይናቸው ታውሮ እጅ እግራቸው ተጠፍሮ ያካባቢው ሀብት በተሳቢ 24 ሰኣት በሸታ ተጭኖ ሲወጣ የሚወጣው ምን እንደሆነ እንኳን የሚያውቁ ኣይመስለኝም:: ከኣዲስ ኣበባ ሚዛን የተሰራው ኣስፋልት ለህዝቡ ታስቦ ሳይሆን ሁብቱን ለመዝረፍ ታስቦ ነው:: የሚገርመኝ 27 ኣመት በዚህ ኣይነት ሲጋዝ ሀብቱ ኣለማለቁ::

 

እግዚአብሔር እውነተኛ ፈራጅ ነው:: ኣይቶ ኣይቶ ፅዋው ሲሞላ ከሀገር ኣስወጥቶ ዘብጥያ ኣወረዳቸው እድሜ ይሥስጣቸው የሳውዲው ልዑል የሚገርመው ከኢትዮጲያ ሲወጡ በድንገት ሀገር ኣማን ነው ብለው ኑዛዜ እንኳን ኣልተናዘዙም ለፍቅረኛችው የኑዛዜ እድል ኣግኝተው ቢሆን ኖሮ የውሽውሽ ሻይ ልማት ለሙሽራዋ የበበቃ ቡና ለኣዜብ በሆነ ነበር ግን ምን ያደርጋል ፍርድ የእግዚአብሔር ነው ደግሞ በምህረት ስም ዶ/ር ኣቢይ ወደ ሥልጣን በመጡ ማግስት በይቅርታ ተፈተው እናያቸው ነበር ለነገሩ ዶ/ር ኣቢይ ዩሳውዲን ልኣዑል እንዲፈቷቹው ተማፅነው ኑበር ግን ፍርድ የእግዚአብሔር ሆነና ኣልተሳካም:: ኣንዳንድ የጥቅም ተካፋይ የሆኑ ግለሰቦች ስይናቸውን በጨእ ኣጥበው የደሀ ኣባት ናቸው ይፈቱልን እያሉ ጡዋት ማታ ያቀነቅናሉ ያልተነካ ግልግል ያውቃል ኣሉ ከሙስናውና ከዘረፋው ባሻገር ሚሊኒየም ኣዳራሽ ሲሰራ ቦታው ላይ ተኝተው የነበሩ ጎዴና ተዳዳሪዎችን ከኣፈር ጋር እንዲቀላቀሉ ኣድርገዋል ተብለው ይታማሉ እውኑቱን እግዚአብሔር ይወቀው ይህ ከተፈፀመ እግዚአብሔር ይቅር የማይለው ዉንጀል ነው

 

ሼሁ የዛሬ 27 ኣመት ኢትዮጵያ ሲሙጡ ማሊየነር ነበሩ የኛን ሀብት ዘርፉው ቢሊየነር ሆኑ ይገርማል

 

ለሙሆኑ እነዚህ ድርጅቶች ኣሁን የማን ናቸው?? የህዝቡ ወይስ?? ባለቤት ኣልባ

 

ይዘገያል እንጂ ሁሉም የእጁን ያገኛል

W/ro Fantaye

Posted by: Kumilachew Ambo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: