Leave a comment

ከልብ ካለቀሱ እንባ ኣይገድም


 

ከድህነቱ ከኃላ ቀርነቱ ፍትህና ዲሞክራሲ ከማጣቱም በላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያን ህዝብ ህይወት  እየቀሰፈ በሰው ህይወትና በሀገር ሀብት ላይ በየቀኑ እጅግ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘው የመኪና ኣደጋ ማስቆም ባይቻልም እንኳን መቀነስ ይቻላል::

የመኪና ኣደጋ ዜና መስማትና በሶሻል ሚድያ ላይ መመልከትና ነፍስ ይማር ማለት የተለመደ ጉዳይ ከሆነ ውሎ ኣድራል:: በየእሉቱ በዚያ ኣካባቢ እየደረሰ ያለው የመኪና ኣዱጋ ምናልባትም ትክክለኛ መረጃ ቢሰበስብ ኣይደለም ከኢትዮጲያ ከዓለም  የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ህይወትና ንብረት ጥፋት የመጀመሪያውን ደረጃ ይይዛል ብል ማጋነን ኣይሆንም:: በቡና ምርት ማበርከት ስማችን በዓለም እንደተመዘገበ በመኪና ኣደጋም ታሪክ የመጀመሪያውን ሥፍራ ሳንይዝ ኣንቀርም:: በኣካባቢው ያለው የመንገድ የትራንስፖርት መ/ቤት ዋነኛ ተጠያቂ ሲሆን ለዘመናት ህዝቡ እየሞተ የሀገር ሀብት  ያለኣግባብ እየወደመ መንግሥት ኣስፈላጊውን ሁሉ ማድረግና ይህን የሰው ህይወት እልፈትና የንብረት ውድመት ላይ ቁጥጥር ማድረግ ሲገባው ዳር ቆሞ በመመልከት ዘመናት ተቆጥረዋል:: ይህን ያህል የሰው ህይወት ሲጠፋ የድሀና በችግር ኣሮንቋ ውስጥ የተዘፈቀን ህብረተሰብ ችግር ለመፍታት ምንም ኣይነት ጥረት ሲደረግ ኣይታይም:: በኣካባቢው ምንም ዓይነት መሰረተ ልማት ተጠቃሚ ካለመደረጉም በላይ ብቃትና  ጥራት በጎደላቸው ተሽከርካሪዎች በማሰማራት ልምድና እውቀት በሌላቸው ኣሽከርካሪዎች/ሾፌሮች የመንግሥት ባለሥልጣናት ቸልተኝነት የተሽከርካሪዎች  በቂ ጥገና ማጣት  ጭነት ኣለመመጣጠን በየኬላው ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ኣለማድረግና የትራፊክና ሾፌር ሌባና ፖሊስ ጨዋታ ከሙስና ጋር ተዳምሮ  ችግሩን ኣባብሶታል::

ከዚያም  ባሻግር ለዘመናት የብሶት ድምፁን እንዳያሰማ ኣፉን ተለጉሞ የኖረው  ህዝብ ዛሬም ላይ ዝምታን መርጦ እየተገደል ህዝቡ ኣሜን ብሎ ተቀብሎ ተባባሪነቱን  ቀጥሎበታል ኣንድም ቀን ተቃውሞ ሲያሰማ ኣይሰማም/ኣይታይም:: ባለሥልጣናትም ለችግሩ መፍትሔ በመፈለግብ ፋንታ ጆሮ ዳባ ብለው የችግሩ ኣጋር መሆንን መርጠዋል:: ምክንያቱ ምን ይሆን? የዚህ ኣካባቢ ህዝብ ቁጥር እንዲቀንስ ሆን ተብሎ የተሸረበ ደባ ይመስላል::  ካለፈው የሚኒልክ ወረራ  ወዲህ በጦርነት የህዝቡ ቁጥር  እንዲቀንስ ከተደረገ በኃላ ከትውልድ  መንደሩ በማፈናቀል በማሳደድ ከቤት ንብረቱ በማባረር  ዛሬ ላይ ደግሞ በየእለቱ በተሽከርካሪ  ኣደጋ ህይወቱ ሲያልፍ ንብረቱ ሲወድም በዝምታ መመልከት ዋነኛው የዘር ማጥፋት ድብቅ ሴራ ነው::   መተኪያየ የሌለው ውድ የሰው ልጅ ህይወትና በድህነትና ኃላ ቀርነት ውስጥ ያለ ህዝብ  ሀብትና ንብረት በከንቱ ሲባክን እያየን እስከ መቼ ነው ዝምታ መርጠን ደረት መተን ከንፈር መጠን በሀዘን የምኖረው:;

መፍትሄው እጅግ ቀላል ነው::
1ኛ/ መንገድ ትራንስፖርት መ/ቤት ስምሪቱን በጥብቅ መቆጣጠር

2ኛ የተሽከርካሪዎች ኣመታዊ ምርመራ ቦሎ ኣሰጣጥ  ሥራ ላይ የመዋል ብቃት በኣግባቡ መፈተሽና በጉቦ ቦሎ መስጠት ማቆም

3ኛ/ለሀገርና ለወገን ተቆርቋሪነት ስሜት ያላቸውንና ለቦታው  በቂ ችሎታ ያላቸውን የተሽከርካሪ ፈታሾች በቦታው ላይ መሙደብ

4ኛ/የመንጃ ፈቃድ ኣሰጣጥ በእውቀትና የማሽከርከር ችሎታ ላይ እንዲያተኩር መቆጣጠር በዘሙድ ባዝማድ በጉቦ መንጃ ፈቃድ ኣሉመስጠት
5ኛ/ ጭነትና የተሽከርካሪው የመሸከም ኃይል ማመጣጠን

6ኛ/ በየኬላው ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ
7ኛ/ ሥነ ምግባር ያላቸው በቢራና በቁርጥ የማይደለሉ የትራፊክ ፖሊሶችን መመደብና በልተህ ኣብላኝ ዐይነቱን ኣሰራር ማስወገድ

8ኝ/ ህጋዊ ያያልሆኑ ታሪፎች  መቆጣጠር የደረሰኞችንም በኣንድ ደሩሰኝ ተደጋግሞ የሚደረገውን የገንዘብ ኣሰባሱብ መቆጣጠር

9ኛ ኣጥፊዎችና ህግ ተላላፊዎችን ለፍርድ ማቅረብና ኣስፈላጊውን ቅጣት ማስወሰን

10ኛ/ ባለሐብቶች በየኣመቱ በመኪና ላይ መኪና ለመጨመር የሚያደርጉትን የትርፍ ማጋብስ ሩጫ ትተው በኣግባቡ ህብረተሰቡን ለማገልግል ጥረት እንዲያደርጉ ኣስፈላጊው ቁጥጥር ቢደረግ

ባጠቃላይ የህዝብና የሀገር ሀብት ያለ ኣግባብ እንዳይባክን ከተፈለገ ከላይ የተጠቀሱትንና የመሳሰሉትን እርምጃዎች በመተግበር ጨርሶ ችግሩን ማስወገድ ባይቻልም እንኳን መቀነስ ይቻላል::

በመጨረሻም ዶ/ር ኣቢይ ኣህመድ እንዳሉት “ሰው የሀገር ሀብት ነው” እባካችሁ ሀብታችንን ያለ ኣግባብ ኣናባክነው ሀገር ለመገንባት የሰው ሀይል ወሳኝ መሆኑን ኣንርሳ:: ያለ ኣግባብ የሰው ህይወት እንዲጠፋ የሚሸረበውን ደባ በህብረት እናውግዝ እንዋጋ

ህዝባችንን እግዚአብሔር ይታደግው!!

by: Fantaye Meko

 

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: