Leave a comment

ፊተኞች ኃለኞች


ፊተኞች ኃለኞች

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረት (ደምኢሕህ) ኣስፈላጊነት

ቦንጋ በ1560ዎቹ የተቆረቆረች ስትሆን የከተማው ምሥራቃዊ ጫፍ ኣካባቢ ያለው ከፍተኛ ሥፍራም”ቦንጌ ሻምበቶ” በመባል ይታወቃል:: ከቦንጋ ጋር ኣንድራቻና ባርታ ሌሎችም የነገሥታት መናገሻዎች እንደነበሩ ይታወቃል::: ፊተኞች ኃለኞች

ከኦሮሞ መስፋፋት በፊት በሰሜን በኩል ካፋን ያዋስን የነበረው የሂናሪያ መ ንግሥት ነበር:: ከ18ኛው ምዕተ ኣመት እስከ 1840ዎቹ ድረስ ወደ ኣካባቢው በተስፋፋው የሜጫ ኦሮሞ የመስፋፋት ሂደት የተነሳና በየጊዜው በተለያየ ጊዜና በተለይም የ1897ቱን የምኒልክን የመስፋፋት ወረራ ተከትሎ በኣካባቢው ህዝብ የደረሰበትና ዛሬም ላይ እየደረሰበት ያለው ግፍና በደል ተዘርዝሮ የማያልቅ ሲሆን ግፍና በደል ህዝብ ጆሮ ባለመድረሱ ትውልዱ የታሪክ ደሀ ተደርጎ በመቀረፁ የበታችነት ቢሰማው ምን ይደንቃል??

ባጠቃላይ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚኖረው ምንም እንካን ጀግናና ታላቅ ህዝብ ተፈጥሮ ያደለው ሀብታም ህዝብ የኣኩሪ ታሪክ ባለቤት ቢሆንም ወደፊት እንዳይራመድ ሲሰማ ያደገው ጀግንነቱን ሳይሆን ፈሪነቱን ነፃነቱን ሳይሆን ባርነቱን ታላቅነቱን ሳይሆን ኣናሳነቱን ባለሀብት መሆኑን ሳይሆን ድህነቱን ጉብዝናውን ሳይሆን ስንፍናውን ኣዋቂነቱን ሳይሆን ኃላ ቀርነቱን ነበር:: ይህም ሆን ተብሎ በህዝቡ ኣእምሮ ውስጥ ሰርፆ እንዲገባና ከትውልድ ትውልድ
እንዲተላለፍ በየጊዜው በተነሱ የማእከላዊው መንግሥትም ሆነ ተወካዮች ህዝቡ ላይ በተደጋጋሚ ጫና ሲደረግበት ዛሬ ላይ ደርሷል::

ከላይ የተዘረዘረው ግፍና በደል ከኣሁን በኃላ እንዳይቀጥል በጋራ ተባብሮ ጉልበትን ኣጠናክሮ መታገል ኣማራጭ የሌለው ምርጫ በመሆኑ ካፈቾ ሸከቾ ቤንች ማጅ በህብረት መቆም ብርታትና ጥንካሬ ይሰጣል ተብሎ ስለታመነበት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረት (ደምኢሕህ) መመሥረት ኣስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ጠቢቡ ሰሎሞን ለሁሉም ጊዜ ኣለው እንዳለው የኛም ጊዜ ኣሁን በመሆኑ ነገ ወይም ተነገ ወዲያ ሳንል ኣያቶቻችን ዘመናዊ እውቀት ሳይኖራቸው ጅግንነታቸውን ኣወረሱን:: ዘመናዊ የፅሑፍ ችሎታ ስላልነበራቸው ታሪካቸውን በፅሑፍ ማስተላለፍ ባይችሉም ብዙዎች ለልጆቻቸውና ለልጅ ልጆቻቸው በማስተላለፋቸው እንደ ወንድወሰን ግዛው ያሉ የመብት ተሟጋቾች ሌሎችም የደምኢሕህ ኣባላት ከቤተሰባቸው የሰሙትን ያልተፃፈ ታሪካችንን በማሳወቅ እንዲሁም ታሪክ ፀሐፊዎች እንደ አቶ በቀለ ወ/ማርያም ኣዴሎና የመሳሰሉት ከዘገቡት በተጨማሪ ኣደባባይ ኣውጥተው በማካፈል ግንዛቤ እንድናገኝና ኣንገታችንን ቀና ኣድርገን በማንነታችንና በባህላችንና በኣንድነታችን እንድንኮራ መንገድ እየጠረጉ ይገኛሉ::

የደቡብ ቶሌቪዥን መሥራት ያለበትን ባለመሥራት ሃላፊነቱን በኣግባቡ ባለመወጣቱና ወገናዊነቱን ባለማሳየቱ በታሪክ በጥቁር ቀለም ሲመዘገብ ካፋ ሚድያና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሚድያ በወርቅ ቀለም ታሪክ ይመዘግባቸዋል:: እኛም ከወዲሁ ምሥጋና እንቸራቸዋለን::ወጣቱም ሆነ ህብረተሰቡ ባጠቃላይ ወደ ኣንድነት በመምጣት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረት (ደምኢሕህ) ጎን በመቆም የመጣውን ለውጥ በመደገፍ ሀገር እንዳትበታተን ህዝባችንም ወደቀደመው ታላቅነቱ ተመልሶ በነፃነትና በወንድማማችነት ኣብሮ የመኖር ባህሉን ጠብቆ የኣካባቢውን ሰላም ኣስጠብቆ በዘር በቋንቋ በሀይማኖት ኣንዱ በሌላው ላይ ተፅዕኖ ሳይፈጥር በመቻቻል የምንኖርባትን ኢትዮጵያ መገንባት ይኖርብናል::

ተባብረን ኢትዮጵያን እንታደጋት
ፍትህ እኩልኑት ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ!!!
ፋንታዬ መኮ
ካፋ ሚድያ kaffamedia

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: