የተከበራችሁ የጎንጋ ዝርያዎች በያላችሁበት
የካፋ ንጉሠ ነገሥት የጋኪ ሻሮቺ ማሽቃሬ ባሮ እንኳን ኣደረሳችሁ!!!
ላይኛው ቤት ሆኜ በኣፀደ ነፍስ
በሥጋ ባልኖርም ኣለሁ በመንፈስ
ስታከብሩ ኣይቼ ቦንጋ ላይ ማሽቃሮ
ሞቅ ደመቅ ኣርጋችሁ ከኣምና ዘንድሮ
ጠብና ጥላቻ ከመሀላችሁ ጠፍቶ
ደስታ ሰፍኖበት በቦንጌ ሻንበቶ
ኣየሁኝ ልጆቼን ክንዴን ተንተርሼ
ርቄ ሄጃለሁ ኣልመጣ ተመልሼ
ስትበሉ ስትጠጡ ስትጎራረሱ
የጠብን ግድግዳ ስታፈራርሱ
ሠንጋው ተጥሎ ቡናውም ተፈልቶ
ተከበረ ማሽቀሬ ባሮ በቦንጊ ሻንበቶ
ተረስቼ ኖሬ ከመቶ ኣመት በላይ
ልጆቼ ኣስታወሱኝ ማሽቃሮ በኣል ላይ
እናቆማለን ኣሉ የጋኪን ሐውልት
ጀመረ ውዱ ልጅሽ ገንዘብ ማዋጣት
እጅ ለጅ ተያይዘው ልጆችሽ እንደነብር
ጥምረት መሰረቱ ኣንድ ሆነው በፍቅር
ተባብረው ሊሰሩ ሊያሳድጉ ሀገር
መሐላ ፈፀሙ ቆመው በኣንድነት
ከእንግዲህ ዳግመኛ ላይለያቸው ሞት
እጥፍ ድርብ ሆኖ እኔም ደስታየ
ተመልሼ ሄድኩኝ ወደ መኖሪያየ
እመጣለሁና ዳግም ለመጪው ኣመት
ጎበኛችኃለሁ ብቅ ብየ ድንገት
ምኞታችሁ ሰምሮ ሐውልቴን ኣቁማችሁ
ሰላምና ፍቅር ሰፍኖ መሐላችሁ
በትንሽ በትልቅ መናቆር ትታችሁ
ለፍትህ ለኩልንት በጋራ ሆናችሁ
ጥንት እንደነበረ ስሜን ኣድሳችሁ
ኣልበገር ብዬ የተዋደኩለት
እጄን ያሳሰርኩት በወርቅ ሰንሰለት
ለናንተ ብዬ ነው ዋጋ የከፈልኩት
ህይወቴን ገብሬ መስዋዕት የሆንኩት
ካገሬ ወጥቼ በዚያው የቀረሁት
ለህዝቤ ነፃነት ለሀገሬ ኣንድነት
የሀገሬን ዳር ድንበር ተግታችሁ ጠብቁ
በዘመናዊ ተኩላ እንዳትነጠቁ
ይብቃችሁ መኝታ ካሁን ጀምራችሁ
እንዳትሸወዱ እኔ ልምከራችሁ
እንዳይቀለበስ የመጣው ለውጣችሁ
ኣቢይን ኣግዙት ከጎኑ ቆሜችሁ
እንዳትበታተን ኢትዮጵያ ሀገራችሁ
ፍቅርና ኣንድነትን ሰላምን ይስጣችሁ
ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን እግዚአብሔር ከታቀደው መከራና ከተሸረበው ሴራ ይጠብቅልን!!!
ፋንታዬ መኮ
ካፋ ሚድያ kaffamedia