Leave a comment

የካፋ ትንሳኤ ለኢትዮጵያ ህልውና መሰረት ነው


~የካፋ ትንሳኤ ለኢትዮጵያ ህልውና መሰረት ነው~
ኢትዩጵያችንና ሕዝቧ ለዘመናት የዘለቀውን የፖለቲካ ሽኩቻና አለመረጋጋት በማስቀረት የተረጋጋና ለጋራ ዕድገትና ብልፅግና የሚተጋ አንድ ፖለቲካዊና ኤኮኖምያዊ ማህበረሰብ ለመፍጠር የምያስችል የተስፋ ጭላንጭል እየፈነጠቀ ነው። ይህንንም ተስፋ ከግብ ለማድረስ እኔ ከማለት እኛ የሚሉ፤ በየአከባቢው የሚነሱ ጥያቄዎችን የዘውግ የዘር የጎሳ እያሉ ታርጋ ከመለጠፍና ከማንቋሸሽ ይልቅ እውነተኛ የዜጎች ጥያቄ መሆናቸውን አምኖና ተቀብሎ በጋራ ተገቢ የሆኑ ፖሊሲዎችን መቅረፅ የሚችሉ፤ እያንዳንዱ ማህበረሰብ የራሱ የሆነ ባህላዊና ታሪካዊ ማንነት እንዳለው ተቀብሎና ይህም ማንነቱና ባህሉ ለምንፈጥራቸው ተቋማቶች መተክያ የሌላቸው ግብዓቶች መሆናቸውን ከልብ ተቀብሎ ማስተናገድ የሚችሉ መሪዎች የምትሻበት ወቅት ላይ እንገኛለን። በእርግጥ በተለምዶ የለማ ቡድን(team lema) እና ጠሚ አብይ ኢትዮጵያና ሕዝቧ በዘመኗ አይተው የማያውቁትን የለውጥ አስተሳሰብ በማራመድ ትልቅ አገራዊ መነቃቃትንና የዜግነት ክብርና ለማምጣት እየተጉ ይገኛል፤ ነገር ግን ይህ የለውጥ አስተሳሰብ በተቋማት በመታገዝ እስከ እስከ ትንሿ ቀበሌ እስካልዘለቀ ድረስ የታሰበውን ለውጥ ማሳካት እንደምያዳግት በየጊዜው የሚነሱ አሰቃቂ ግጭቶች በግልፅ ያመላክታሉ።
ይህንን ርዕስ ለማንሳት የመረጥኩት ካለፈው ታሪካችን ምን እንማራለን የትኛውን ወስደን የትኛውን በማሻሻል በየጊዜው እየጎለበተ የሕዝባችንን ሕይወት የሚቀይርና ለትውልድ የሚሻገር ስርዓት ልንገነባ እንችላለን የሚል የአንድ ግለሰብ ጥቅል እይታየን ለማስቀመጥ ያክል ነው(በእርግጥ ወደፊት በሚፈጠሩ መድረኮች የምሁራንና የመላው ሕዝብ እይታ ታክሎበት የሚዳብር ይሆናል የሚል እምነት አለኝ)።
ወደ ርዕሱ ከመግባቴ በፊት እንደ አገር የሚነሱ አጠቃላይ ጥያቄዎች ምን ይመስላሉ የሚለውን በቅድምያማየቱ አስፈላጊ ይሆናል።
እነሱም፡-
1. እራስን በራስ የማተዳደር
2. የመሬትና የሃብት ባለቤትና ተጠቃሚ መሆን
3. የራስን ባህልና ቋንቋ የመጠቀም፣የማሳደግና የመጠበቅ
4. አገራዊ አንድነትንና ሉአላዊነትን የማስጠበቅና የዜግነት ክብርን ማስፈን
ናቸው
ታድያ እነዚህ ጥያቄዎች ከርዕሱ ጋር ያገናኛቸዋል ትሉ ይሆናል። እንግድያውስ ወደዝያው ልመለስ።
አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ካፋን በቡና መገኛነቷና ክ/ሃገርነቷ ያውቃታል በተወሰነ መልኩም የካፋ ግዛት (Kafa Kingdom) ታሪክ ጭምር። የእኔም ትኩረተ Kafa Kingdom ምስረታ አሁን ለምናልመው አገራዊ ተቋም ወይም ስርዓት ምስረታ ምን አስተዋፅኦ ይኖረዋል የሚለው ነው።
Kafa Kingdom የዘር ማሳያ ሳይሆን ከመካከለኛው ክ/ዘመን አንስቶ በየግዜው እያደገና እየጠነከረ ንጉሳዊ አስተዳደር ሆኖ በሚኒስተሮች የሚመሩ ተቋማት የነበሩት ጠንካራ አገር ነበር። ካፋ ማለት ትርጓሜውም ወደ አዲስ ህይወት መሸጋገር መለወጥ እንደማለት ነው። የካፋ ዘር ሃረግ የሆኑትም በመላው አገራችን ይገኛሉ። እነሱም ሽናሻ፣አንፊሎ፣ እናሪያ እን ሻካ ይገኙበታል። ግዛቱም በየጊዜው እየስፋና እየጠበበ እስከ ወሊሶ ከምባታ እና ሱዳን ይደርስ እንደነበር የታሪክ መዛግብትና ትውፊቶች ያስረዳሉ። በመጨረሻም ከረዥም ጊዜ እልህ አስጨራሽና የብዙዎችን ሕይወትና ተቋማቶቹን ከቀጠፈና ካወደመ በኋላ 1897 እ.ኤ.አ ወደ አሁኗ ኢትዮጵያ አካል እንዲጠቃለል ተደረገ። (ያሁኗ ለማለት የተፈለገው ቀድሞም ቢሆን እስከ ሶማሌ ትዘል የነበረችው ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ አካል እንደነበር ለመግለፅ ተፈልጎ ነው)።
ታድያ የካፋ ንጉሳዊ አስተዳደር ምን ይመስል ነበር? እንዲደመሰስ ባይደረግ ኖሮ የዛሬይቷ ኢትዮጵያ የተሻለ ስርዓይ ይኖራት ነበር?
1.እራስን በራስ ማስተዳደርን በተመለከተ፡ የካፋ ግዛት ትናንሽ ግዛቶች ህልውናቸውን እንደጠበቁና በራሳቸው ነገስታት እየተመሩ በአንድ ንጉሰ ነገስት ሥር የሚስተዳደር አንድ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ማህበረሰብ እየፈጠረ የመጣ የአስተዳደር ርዕዮተ ዓለም ነበር። እንደማንኛውም ስርዓቶች በዚህ ሂደት ውስጥ የስልጣ ሽኩቻዎች እንደነበሩና ሂደቱን ለማስቀጠል ፈታኝ እንደነበር ይታመናል። በአጠቃላይ ግን እንደ ስርዓት የሌሎችን መብትና ማንነት ከግምት ያስገባና ያልጨፈለቀ ዘመናዊና ጠንካራ መንግስታዊ ስርዓት እንደነበር ታሪካዊ ሃቅ ነው።
2. የመሬትና የሃብት ተጠቃሚ ስለመሆን: በይጊዜው ወደ ግዛቱ የሚተሙ ጎሳዎችን ንጉሱ በመቀበል መሬት በመስጠትና የራሳቸውን መሪ እንዲመርጡ በማድረግ የተረጋጋ ኤኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስር እንዲጎለብት ያደርጉ ነበር።
3.የማህበረሰብን ባህልና ቋንቋ መጠበቅን በተመለከተ:- በግዛቱ ስር የነበሩ አካባቢዎችን ብንመለከት ባንድ ቋንቋ፣ባህልና እምነት በንጉሳዊው ስርዓት ወቅት እንዲወድቅ የተደረገ አካባቢ አልነበረም። ለምሳሌ ዳውሮን፣ወሊሶን፣ ካምባታን እንዲሁም እስከ ሱዳን ዘልቀን ማየት እንችላለን።
4. አገራዊ አንድነትንና ሉዐላዊነትን በተመለከተ፡- በክፋ ንጉሳዊ ስርዓት ወቅት ኢትዮጵያዊነት መሬት፣ሃብት፣ወይም ድንበር አልነበረም። ይልቁንም ከምንም በላይ የድል የወንድማማችነትና የአብሮነት ልባዊ መገለጫ እንጂ። ይህም በተግባር የተፈተነ ካፋንም እስከዛሬ ለደረሰበት ታላቅ መከራ ያበቃው መስዋዕትነት የተከፈለበትም ጭምር ነው። ክስተቱም እንዲህ ነው፦በ1897 ንጉስ ምኒሊክ ሁሉንም ግዛቶች አስገብረውና ከጣልያን የማረኩትን ዘመናዊ መሳሪያ ይዘው በተከታታይ ድል ነስቷቸው አልበገር ያለውን የካፋ ግዛት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስገበት የጦርነት ነጋሪት ጎሰሙ። በዚህን ጊዜ ግዛቱም ከውጭ መንግስታት ጋር ይገናኝ የነበረ ሉዓላዊ መንግስት ነበርና በሱዳን የነበረው የእንግሊዝ ጦር ንጉሡ ጋር ቀርቦ ምኒሊክ ሊወጋህ እየተሰናዳ ነውና መሳርያ ሰጥተንህ ተዋጋ ቢሉት “ እኔ የምዋጋው ከወንድሜ ጋር ነው፤ እኔ ባሸንፍ አገሩን ሁሉ እኔ እገዛለሁ እርሱ ብያሸንፍ እሱ ይገዛል የእናንተን እገዛ የምፈልገው ከባዕድ ጋር ስዋጋ ነው” ብሎ በመመለስ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው የጥቁር ሕዝቦች ኩራትና አንድነት ተምሳሌት በመሆን ተሰዋ። ሕዝቡም እስከመጨረሻዋ ሰዓት ድረስ ከጎኑ በመሆን ታላቅ መስዋዕትነት ከፈለ፤ እስከ 14 የሚሆኑ ቤተ-መንግስቶችና ቅርሳ ቅርሶች ወደሙ የቀረውም ሕዝብ ለጭቆና ተዳረገ። ማንነቱ የተከበረለት አንድ ምጣኔ-ሃብታዊና ፖለቲካዊ ማህበረሰብ መራበትና ራዕይ ተገቶ በምትኩም ይኽው እስከ ዛሬ የምያራኩተን የመጨፍለቅና የመበዝበዝ ስርዓት ተተካ።
መልዕክቴም በመደማመጥ፣በመማማርና በመተጋገዝ ሁላችንም ልንመራበትና ልንተዳደርበት የምንችልበትን ስርዓት እንፍጠር፤ ለሁላችን የምትበቃ አገር አለችንና አብረን እየኖርን አብረን እንዳልኖርን አይነት አንሁን። የጋራ አገርና ተቋማት በመገንባት አዲስ ምዕራፍ እንጀምር።
ያሮን ቆጭቶ
በበረራ ላይ የተፃፈ
Oct.03, 2018

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: