2 Comments

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ህብረት ድርጅት(ደምኢህህ)አመራሮች የመጀመርያውን ስብሰባ በአዲስ አባባ አካሄዱ::


 

1313የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ህብረት ድርጅት (ደምኢህህ) አመራሮች የመጀመርያውን ስብሰባ በአዲስ አባባ አካሄዱ
ስብሰባው ዛሬ 4/2/2011  4ሰዓት የጀመረ ሲሆን በስብሰባው ላይ በርካታ የአከባቢው ተዎላጆች, የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም ምሁራኖች በአደራሹ የሞሉ ሲሆኑ በውይይቱ ላይ በርካታ ሃሳቦች ተነስተዋል።
በስብሰባው መጀመሪያ ላይ አቶ ብርሃኑ ወልደሰንበት ለተሰብሳቢው ጥያቄ በማቅረብ ጀምረዋል:-
”እኛ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ህብረት ድርጅት ሲንመሰርት የህዝቡን ፍቃድ ተቀብለን ሳይሆን ለአካባቢያችን ካለን ተቆርቋርነትና ቁጭት በመነሳት ነው ለዛች አካባቢ እድገር ስንል የተደራጀነው፣ ይሁንና ይህ ድርጅት የህዝብ እውቅና ስለሌው እናንተ እውቅናውን ካልሰጣቹ ህጋው ሆነን መንቀሳቀስ ስለምያስቸግረን የእናንተን ሙሉ ፍላጎት ማወቅ እንፈልጋለን” በማለት ጥያቄያቸውን ለህዝቡ አቅርበዋል፣ በመሆኑም በአደራሹ የምገኙ ታዳምዎች በሙሉ ድምፅ ድጋፋቸውን ገልጸዋል::
በመቀጠልም የድርጅቱ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ወልደሚካኤል እና ለሎች የድርጅቱ አመራሮች ስለድርጅቱ አላማና ፍላጎት በመግለፅ121
በህብረትና በአንድነት ከጮህን እንደመጣለን
ለውጡን ላመጡ ዶ /ር አብይና ቲም ለማ ብሎም ህይወታቸውን ላጡ ወጣቶች ምስጋና አቅርበዋል
ኢትዮጵያዊነትና አንድነትን ማየት የፈለገ ሰው ጎጀብን ተሻግሮ ይመልከት
እኛ በጋራ ከሆንን ህዝባችንንና አካባቢያችን ካለበት ችግር በቀላሉ በማስውጣት የኢኮኖሚና የልማት ተጠቃሚ እንድሆን እናስችላለን
እኛ የአከባቢው ተዎላጆች በጋራ ከሆንን የህዝባችንን ድሞክራሲያዊ መብት ማስጥበቅ እንችላለን
በአካባቢያችን የሚገኙ ሃብቶቻችን ለምሣሌ እንደ ውሽውሽ ሻይ፣ በበቃ ቡና፣ ጎጀብ እርሻ ልማት የአከባቢው ማህበረሰብ ያለማው ሀብት ሆኖ ሳለ ነገር ግን ተጠቃሚዎቹ ለሎች መሆናቸው ፊፁም ኢፍቲኃዊ በመሆኑ ይህንን በጋራ በመሆን ማህበረሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል
እኛ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ካሁን በኋላ የደቡብ ክልል አሸንጉልት መሆን አንፈልግም ራሳችንን ችለን ራሳችንን ማስተዳደር እንፈልጋለን፣ ይሄን ለማድረግ በቂ ምክን ያት ያለንና ህገመንግስቱም ሙሉ በሙሉ ስልምፈቅድልን በጋራ በመሆን ክልላችንን ማስወስንና ህዝባችን ራሱን በራሱ በማስተዳደር የልማቱ ተጠቃሚና የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል
ወጣቱ የመሬት ባለቤትና የስራ ዕድል በመፍጠር ጉልህ ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል
ኢትዮጵያን በመገንባት ደረጃ እና ለዛሬዋ ኢትዮጵያ መመስረት ዋነኛ ምክኛቶች እኛ ነን፣ ምክን ያቱም የካፋው ንጉስ ከሚኒልክ ጋር በነበረው ጦርንርት የእንግሊዝ መንግስት የካፋን ነጉስ መሳሪያ በመስጠት ሊያግዘው ሲፈልግ የካፋው ንጉስ ግን መሳሪያውን አልፈልግም የኛ ጦርነት የውንድማማቾች ጦርነት ነው ሚኒልክ ካሸነፈ ኢትዮጵያን ያስተዳድራል እኔ ካሸነፍኩ ኢትዮጵያን አስተዳድራታለሁ፣ የእናንተ እርዳታ የሚያስፈልገን ወራሪ ጠላት ከውጭ ከመጣ የዛነ ሲያስፈልገን እንጠይቃለን በማለት እንደመለሷቸውና ለዛሬዋ ኢትዮጵያ መመስረት ትልቅ ሚና የነበረው ነው በማለት አውስተዋል
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ህብረት ድርጅት በዋነኝነት የህዝቡን ችግር ፍቺ እና ለህዝቡ ጥቅም የምሰጥ በኢኮኖሚና በለሎች መሰረታዊ ልማቶች ጉልህ አስተዋፅኦ ማበርከት እንዳለበትም ገልፀዋል
በመቀጠልም ለዚህ ሁሉ ለምናስበውና ለምንመኘው ለውጥ በጋራ መደራጀትና የራሳችንን ቤት ራሳችን መስራትና መገንባት እንዳለብን ገልፀዋል።
ሌላው በስብሰባው ላይ ከተገኙት ትላልቅ የመንግስት ባለስልጣናትና ምሁራንም ድርጅቱን ሙሉ በሙሉ እንደምደግፉና እንደምረዱ ቃል ገብተዋል።
በእለቱ ከነበሩ ታዳሚዎች መካከል ወ/ሮ ዘውድቱ በቦንጋ የሚገኘውን የራሳቸውን ቤት ለድርጅቱ ጽ/ቤት እንዲጠቀሙ ፈቅደዋል::
የተሻለች ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያን ለመገንባት በጋራ እንረባረብ

By ቁምላቸው ገብረመስቀል

2 comments on “የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ህብረት ድርጅት(ደምኢህህ)አመራሮች የመጀመርያውን ስብሰባ በአዲስ አባባ አካሄዱ::

 1. መልካም ጅምር ነዉ፡፡
  ድርጅቱ ይዞ የተነሳዉና የቆመለት ዓላማ እንዲሳካ ሁሉም ሊተባበር ይገባል፡፡ በተለይም ክልል ባለመሆናችን እንደሁለተኛ ዜጋ ወደ ጥግ የተገፋነዉ ሁላችንም ነን፡፡ ይህም በኢህአዴግ ዉስጥ ያሉትንም ሆነ በተለያየ ጊዜ በቅንነትና ትጋት አገልግለዉ ያለፉትንም ጭምር ቤተሰባቸዉንና ወገናቸዉን ብቻ ሳይሆን በግል ራሳቸዉንም ያካትታል፡፡ ስለዚህ ይህንን መንገድ መዝጋትና ማደናቀፍ የመጨረሻዉን የህዝባችንን ጥላቻ እንደሚያሳይ አዉቀዉ መተባበር አለባቸዉ፡፡
  ድርጅቱና መሪዎቹ ከ KPDU ዉድቀት መማርና በጥንቃቄ መጓዝ አለባቸዉ፡፡ ለሁሉም የህዝባችንን በደል አይቶ አምላክ ይርዳን፡፡
  ወ/ሮ ዘዉዲቱ ዳምጠዉ ልክ እንደአባታቸዉ ለህዝባቸዉ ክብርና ጥቅም የቆሙ ታላቅ እናት ናቸዉ፡፡ የካፋ ህዝብ ባለዉለታ ነበሩ፣ አሁንም ለልገሣዉ ሊመሰገኑና ሊከበሩ ይገባል፡፡

  ኬቶ ጋዎ

  Liked by 1 person

Leave a Reply to Keto Gawo Cancel reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: