1 Comment

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ህብረት(ደምኢህህ)ልዑካን ቡድኖች ወደካፋ ቦንጋ ስገቡ እጅግ ደማቅ የሆነ አቀባበል ተደረገላቸው።


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ህብረት (ደምኢህህ)ልዑካን ቡድኖች ወደካፋ ቦንጋ ስገቡ እጅግ ደማቅ የሆነ አቀባበል ተደረገላቸው።


የድርጅቱ ልዑካኖች ዛሬ ማክሰኞ 6/2/2011 ከአዲስ አባባ ተነስተው ጅማ አየር መንግድ ሲደርሱ ነበር አቀባበሉ የጀመረው፣ በጅማ የምገኙ የድርጅቱ ደጋፊዎችና የደቡብ ምዕራብ ተወላጆች ጅማ አየር ማረፊያ በመምጣት ነበር አቀባብል ያደረጉላቸው። ጉዞዋቸውን ከጅማ በመነሳት ያደረጉት ልዑካን ቡድኖች ጎጀብ ሲደርሱ ልዩና ደመቅ ያለ አቀባበል ነበረ የጠበቃቸው፣ የደርጅቱ አመራሮችም አቀባብል ላደረጉላቸው ህዝብም ሰላምታና ምስጋና አቀርበውላቸዋል። በህዝቡ ታጅበው ጉዞዋቸውን በመቀጠል ጊምቦ ሲደርሱ እንደዚሁ እጅግ ያማረ አቀባበል ነበረ የጠበቃቸው። ከዚያም ቦንጋ ሲደርሱ በሺዎች የምቆጠሩ የካፋ ተዎላጆች, አባቶች, እናቶች, የሃይማኖት ኣባቶች እና ወጣቶች በካፋ ዞን አስተባባርነት እጅግ ውብና ያማረ አቀባበል አደርገውላቸዋል። የካፋ ህዝብ ሁሌም እንደወትሮ እንግዳ ተቀባይነቱንና አክባርነቱን በማሳየት አስመስክሮዋል። የድርጅቱ ልዑካኖች ቦንጋ ከተማ እንደደረሱ የዞኑ አስተዳዳር አቶ ማስረሻ የእንኳን ደህና መጣቹ ንግግር በማድርግ እንግዶቹን የተቀበሉዋቸው ሲሆን የድርጅቱ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ወልደሚካኤልም ንግግር በማድረግ የተቀበሏቸውን ህዝብ በእጅጉ አመስግነው ። በንግግራቸውም ”ከ 17 ዓመት በሀላ ቦንጋን ብረግጥም ረስቻችሁ አላውቅም፡፡ ዛሬም ለዶ/ር አብይና ለለውጡ አቀጣጣይ ወጣቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የቦንጋ ከተማ የንግድ ማዕከል በ 15ኛው ክ/ዘመን የነበረች ነበረች፡፡ ያለመተባበራችን ያለመረዳዳታችን ያለመደራጀታችን ወደ ሀላ አስቀርቶናል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ወጣት አመራር በመኖሩ ታድለናል:: የፖለቲካ አዝማሚያችን ምንም ቢሆን አላማችን ሀገራችን ማሳደግ ነው” በማለት ነበረ የገለፁት::


በዛሬው አቀባበል ላይ ልዩ ምስጋና የሚቸራቸው አካላት
የካፋ ዞን አስተዳደር
የቦንጋ ከተማ አስተዳደር
የቦንጋ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ
የቦንጋ ዩኒቨርስቲ
የቦንጋ ከተማ ትራንስፖርትና ስምሪት
የቦንጋ ከተማ ባህልና ቱሪዝም/ ወ/ሮ አስቴር መኩሪያ/
የቦንጋ ከተማ ባጃጅ ሹፌሮች
የቦንጋ ከተማ ፀጥታ ቢሮ ፖሊስና ትራፊክ ቢሮ
የቦንጋ ወጣቶች
የቦንጋና አከባቢዋ ነዋሪዎች
ቦንጋን በማፅዳት ዘመቻ ደከመኝን የማያውቀውና ዛሬ ኤኔትሬ ይዞ ያጀበውን ታሪኩ/ጎጄ/
ሌሎችም የሚዲያ አባላት በተለይ የአቀባበሉ ኮሚቴ አባላት በሙሉ ምስጋና ይገባችዋል፡፡
የተሻለች እድገትና ዴሞክራሲያዊ ለውጥ ለደቡብ ምዕራብ ህዝብ

One comment on “የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ህብረት(ደምኢህህ)ልዑካን ቡድኖች ወደካፋ ቦንጋ ስገቡ እጅግ ደማቅ የሆነ አቀባበል ተደረገላቸው።

 1. • መልካም ቆይታ ለወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንመኛለን፣ ደስ ብሎናል፡፡
  • የካፋ ህዝብ ገና የለዉጥ ጭላንጭል በማየቱ ብቻ የአሁኑን የዞኑን አስተዳዳሪ ጭምር እያደነቀ እንደሆነ እየተዘገበ ነዉ፡፡
  • የካፋ በተለይም የቦንጋ ህዝብማ እንኳን ልጆቹን ሌሎችንም በክብር ተቀብሎ ማስተናገዱ የታወቀ ነዉ፡፡ ባለጉዳዩ ህዝብ፣ አስታዳዳሪዉና ሌሎችም አቀባበሉን ያደመቁ ሁሉ ሊደነቁና ሊመሰገኑ ይገባል፡፡
  • ችግራችን ብዙና ጥልቅ ስለሆነ፣ ለመፍታትም ረጅም ጊዜና ትዕግሥት ይፈልጋል፡፡ በዚህ ድርጅት መመስረትና ወደ አገር ቤት መግባት የተደሰቱ የካፋ፣ ቤንች ማጂና ሸካ ህዝቦች እንዳሉ እናምናለን፣ ይጠበቃልም፡፡
  • ሆኖም ገና ከአሁኑ ሥጋት የገባቸዉ እንዳሉ፣ በቅርቡ በአርማዉ ላይና በመስራቾቹ ማንነት ላይ በፌስ ቡክ የተፃፈዉን አይቼ አዝኛለሁ፡፡ ግን ከዚህ በላይ ፈተና ሊኖር እንደሚችልና፣ ከሞቀዉ አቀባበል ባልተናነሰ አፍራሽና አሉታዊ ሚና እና ተግባር በግልፅም በሥዉርም እንደሚኖር በመረዳት አመራሮቹ በቁርጠኝነት ለመታገል እንዲዘጋጁ ማሳሰብ እፈልጋለሁ፡፡
  • ዋናዉ ማስተላለፍ የምፈልገዉ ጉዳይ ደግሞ፤ ህዝቡ በቀጣይ የድርጅቱ ጉዞ ላይ በንቃት እንዲሳተፍ፣ በተለይም በአሁኑ ጊዜ ተገፍተዉም ሆነ መርጠዉ በየቦታዉ ተበታትነዉ፣ እንዲሁም በአካባቢዉም እየኖሩ፣ ለዉጡን ከመደገፍ ጀምሮ ሌሎችንም ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች በንቃት እየተከታተሉ ያሉ የአካባቢዉ ወጣቶች ድርጅቱን ማቀፍና መሸከም ለጋራ ህልዉናችን ወሳኝ መሆኑን ተረድተዉ በንቀት ሊሳተፉ ይገባል፡፡

  የተሳካ ቆይታ ይሁን

  ኬቶ ጋዎ

  Liked by 1 person

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: