1 Comment

ምሥጋና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ህብረት (ደምኢሕህ) ልዑካን ቡድን


ምሥጋና

ደምኢህህ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ወልደሚካኤል

ደምኢህህ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ወልደሚካኤል

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ህብረት (ደምኢሕህ) ልዑካን ቡድን ጥቅምት 3 ቀን 2011 ዓ.ም ከሰሜን አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በአዲስ አበባና አካባቢው የሚኖሩ የደቡበ ምዕራብ ተወላጆች አስተባባሪ ኮሚቴዎች አስተባባሪነት በቦሌ አለምአቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለተደረገልን ልዩና ደማቅ አቀባበልና መስተንግዶ በደምኢሕህ ስም ከፍ ያለና ልባዊ ምስጋና ላቀርብላችሁ እወዳለው:: ኮሚቴው በዚህ አስቸጋሪ ወቅት እንደዚህ ያለ የተቀነባበረ ውጤታማ ሥራ በመሥራቱ ኮርተንባችኃል:: ከሁሉም በላይ በህብረትም ሆነ በተናጠል የተደረገልን ግብዣ ያሳያችሁን ልባዊ ፍቅር ከምንም በላይ አስደስቶናል ኩራትም ተሰምቶናል::

አዲስ አበባ ላይ ያገኘነው አቀባበልና እንክብካቤ ጊቤን ስንሻገር ከቦንጋ የተነሳው አስተባባሪ ኮሚቴ በምሁራንና በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወጣቶች የመንግሥት ሰሪተኞች ባጠቃላይ በለውጥ ናፋቂው የአካባቢው ማህበረሰብ ታጅቦ ጎጀብ ድረስ በመምጣት ደማቅ አቀባበል በማድረግ በድምፅ ማጉያ ማንነታችንን እያስተጋባ ጊንቦ ላይ ስንደርስ የጊንቦ ወረዳ ነዋሪዎችም ደማቅ አቀባበል በማድረግ በባህል ጭፈራና ኢትዮጵያውነትን በሚያስተጋባ ሙዚቃ ህዝቡን በማነቃቃት ወደ ቦንጋ ሸኝቶናል::

ልዑካኑ ቦንጋ ስንገባ ቦንጋ አደባባይ ላይ ተሰብስቦ መምጣታችንን ይጠባበቅ የነበረው ማህበረሰብም ከፍተኛ አቀባበል በማድረግ የዞኑ አስተዳዳሪና ባለስልጣኖች ጭምር ድጋፋቸውን በመግለፅ ተባብረን ለምንደርገው የለውጥ እንቅስቃሴ ድጋፋቸው እንደማይለየን አረጋግጠው በደስታ ተቀብለው አስተናግደውናል::

ከአዲስ አበባ ተነስተን ቦንጋ እስክንደርስ የተደረገልንን የፍቅር አቀባበል በማድነቅ ልባችን በጣም ቢነካም ወደ ቤንች ማጅ ዞን ሚዛን ለመሄድ ሻንጣችንን አዘጋጅተን እንዳለን አንድ ያላሰብነው ክስተት ተፈጠረ:: ያረፍንበት አካባቢ በአንድ ጊዜ ተወረረ ከቁጥር በላይ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ትልቅ አውቶቡስ በውስጣቸው የጫኑትን ህዝብ ማራገፍ ጀመሩ ባህላዊ የቤንች ዘፈን አካባቢውን ቀወጠው:: ሽማግሌው አሮጊቱ ሴቱ ወንዱ ወጣቱ ጭር ያለውን የቦንጋ እንግዳ መቀበያ ጫካማ ሜዳ በልዩ ሁኔታ ንፍስ ዘራበት:: ይህ በእንዲህ እንዳለ የቤንች ማጂ ዞን አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ለልዑካን ቡድኑ የአበባና ባህላዊ ስጦታ በማበርከት እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት አቀባበል ካደረጉ በኃላ ጉዞ ወደ ቤንች ማጂ ዞን ሚዛን ከተማ ተጀመረ::

ከቦንጋ ተነስቶ ወደ ሚዛን የተደረገው ጉዞ በሞተር የተመራ ከኃላና ከፊት በዞኑ ፀጥታ ኃይሎች የታጀበ ቁጥራቸውን በትክክል የማላስታውሳቸው ተሽከርካሪዎችና አውቶቡስ ህዝብ የጫነ ሲሆን ሚዛን ስንገባ ዘመናዊና ውብ በሆነው ካሽኒን ሆቴል ጊቢው በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አሸብርቆ መሬቱ ለምለም ሳር ተጎዝጉዞ በቤንች ማጅ ባህላዊና ዘመናዊ የሙዚቃ ባንድ ታጅቦ መግለፅ በማይቻል የአቀባበል ዝግጅት የመስተንግዶ አቀባበል በዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና በልዑካን ቡድኑ አባል ህብረትን በሚገልፅ መልኩ የኬክ መቁረስ ስነሥርአት ከተካሄደ በኃላ ቁጥሩንም ሆነ አይነቱን መግለፅ አስቸጋሪ የሆነ ባህላዊና ዘመናዊ የምግብ ዝግጅት ከላይ በጠቀስኩት የሙዚቃ ባንድ አዝናኚነት እጅግ በጣም ጣፋጭ የሆነ ምግብና ለተደረገልን የራት ግብዣ አቀባበል ከልብ የመነጨ ምሥጋና የልዑካን ቡድኑ ሲያቀርብ ከፍ ያለና ከልብ የመነጭ ፍቅርና አክብሮት ጭምር ሲሆን ለአስተባባሪዎቹና መድረክ መሪዎቹ ያላቸውን ችሎታ እውቀትና ብቃት በማድነቅ ጭምር ነው:: ባጠቃላይ የቤንች ማጅ ዞን ለውጡን ሙሉ በሙሉ የተቀበለና ለመለወጥ ከህብረቱ ጎን የቆመና መሪ በማጣቱ እንጂ አስተዋይ የነቃ ለመብቱ መከራከር የሚችል ልበሙሉ ህብረት ያለው ግልፅና ሰው አክባሪና ፍቅር የሆን ህብረተሰብ መሆኑን በቆይታችን ለመታዘብ ችለናል:: በተጨማሪም ለውጡ እንዳይቀለበስ ለመታገል ቆርጦ የተነሳ መሆኑን በግልፅ አስመስክሯል::

44067959_1532531793515602_5749521592140955648_n

የልዑካን ቡድኑ ወደ ሸካ ዞን ለማድረግ ያቀደውን ጉዞ ከማድረጉ በፊት አንዳንድ ጉዳዮችን ለመፈፀም ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ከአስተባባሪ ኮሚቴው ጋር በመቀናጀት በመስራት ላይ ይገኛል:: በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሸካ ተጉዞ የደምኢሕህ አላማ ከሸከቾ ህብረተሰብ ጋር ውይይት ያደርጋል:: የውይይቱ ዓላማ በህብረትና በአንድነት ላይ ተመስርቶ ለአካባቢያችን እድገትና ብልፅግና ብሎም ክልል የመሆን ጥያቄአች መልስ የሚያገኝበትንና ህዝባችን የበይ ተመልካች ሳይሆን የሀብቱ ተጠቃሚ በመሆን ለጋራ እድገትና ብልፅግና አንድ ሆነን የምንቆምበትን መንገድ በመቀየስ በመካከላችን እየገባ አንድነታችንንና አብሮነታችንን የሚፈታተነውን ኃይል በጋራ በመቋቋም ድል የምናደርግበትን ጠንካራ ተቋም መመሥረት ይጠበቅብናል:: አንድ ነን አንድነታችን ጥንካሬአችን ነው:: ስለዚህ ሸካ ላይ የምናደርገው ውይይት ፍሬ እንዲይፈራ የሁላችንም ተሳትፎ ያስፈልጋል::

ባጠቃላይ የደምኢሕህ ልዑካን የተነሳንበትን ዓላማ ለህዝባችን ግንዛቤ አስጨብጠን የተጀመረው ለውጥ ቀጣይነት እንዲኖረው መሠረት ጥለናል:: የቀረን ተባብረን ግድግዳና ጣሪ121ያ በመስራት የቤታችንን ግንባታ እውን ማድረግ ነው:: ትልቅ ነበርን አሁንም ትልቅ በመሆን ከራሳችን አልፈን ሀገራችንን ኢትዮጵያን እናበለፅጋለን::

ድል ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ህብረት

ሁሉንም ህዝብ በእኩል ዓይን የምታይ አዲሲቲን ኢትዮጵያውያ ለመመስረት ከሚታገል የለውጥ ኃይል ጎን እንቆማለን!!!!

ከደምኢሕሕ ልዑካን አባላት በሙሉ::

One comment on “ምሥጋና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ህብረት (ደምኢሕህ) ልዑካን ቡድን

  1. ለጅምሩ ማማር ድጋፍ ላደረጉ ሁሉ ምሥጋና ይገባቸዋል፡፡ በሸካም የተሳካ ሂደት እንደሚኖር እናምናለን፡፡ በአካባቢዉ ሥም ግልፅ እንቅስቃሴ ማድረግ መቻሉ ራሱ ትልቅ ስኬት ነዉ፡፡ መሥራቾችና መሪዎች የህዝባችን ባለዉለታ ናችሁ፡፡ ከአሁን በሁዋላ ያለዉ ሂደት ቀላል ባይሆንም፣ ወደ ግባችን መድረሳችን ግን የማይቀር ነዉ፣ በርቱ፡፡ የእስካሁኑን ሂደት በመሬት ላይ ያለዉን ለመገንዘብ፣ ቀጣይ ሂደቱን ለመቀየስ እንደመነሻ መዉሰድ ተገቢ ነዉ፡፡

    ’’ Mahee Ceeroon Yeshachee, Yechichino Dufaachee’’

    Liked by 1 person

Leave a Reply to Keto Gawo Cancel reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: