2 Comments

ታሪክ ይሰራል እንጅ አይፈጠርም፡፡ የቡና ታሪክ የካፋ ታሪክ ነው፡፡


ሁሉም ነገር ገደብ አለው፣ ሁሉም ነገር ልክ አለው፣ በማንነትና በታሪክ ሲመጡብን ግን ነገሮች ከልክ ያለፉ ይሆና!!!!!!!!!!

45447375_290422645145955_5720262617063227392_n

http://edition.cnn.com/travel/article/ethiopia-coffee-origins-bonga/index.htmlhhvj.png

2 comments on “ታሪክ ይሰራል እንጅ አይፈጠርም፡፡ የቡና ታሪክ የካፋ ታሪክ ነው፡፡

 1. ቡና የካፋ ካልሆነ፣ ኢትጵያም የቡና መገኛ አይደለችም ማለት ነዉ፡፡

  በኢትዮጵያ ሚሊኒየም የበዓል አከባበር አጋጣሚ ካፋ ዞን የተገነባዉ ብሄራዊ የቡና ሙዚየም ዉሳኔ በተሰጠበት በዚያ ወቅት በመንግሥት ዉስጥ ከነበረ ዉስጥ አዋቂ ግለሰብ በኢሳት ቲቪ ሲነገር በቅርቡ እንደሰማነዉ፣ ደግሞ ፣ ለካስ ቦታዉ ቦንጋ እንዲሆን የተወሰነዉ በጥቂት የካፋ ልጆች ትግልና፣ ማንበብ የማይሰለቻቸዉና ታሪክ አዋቂዉ የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚ/ር አቶ መለስ ታሪክ አጣቅሰዉ በወሰኑት ዉሳኔ ነዉ አሉ፡፡

  አፈሩ ይቅለላቸዉና ለካፋ ሁለት ወንበር (በርጩማ) በሽግግሩ ጊዜ ተይዞ የቆየልን፣ ለKPDU የተሰጠዉና እስኪደራጅም ተጠብቆ የቆየዉ የካፋን ታሪክ እየጠቀሱ አቶ መለስ በወሰኑት መሰረት ነበር ሲባልም ሰምተን ነበር፡፡

  አሁን ደግሞ “መደመር፣ የለዉጥ ሃይሉን መደገፍ…… ወዘተ” እየተባለ፣ በሚዘፈንበት ወቅት፣ ድሮዉንም ተሳፍረንበት ወይም ተቀጥረንበት የማናዉቀዉ የባንዲራችን ተሸካሚ ሆነዉ አየር መንገዳችን ”Land of Origins’’ በሚል ስለቡና ሊያስተዋዉቅ፣ በየማስታወቂያዉ ስለ ኢትዮጵያ የቡና መገኛነት የቀሰቀሰበትን የበዓል አከባበር ከካፋ ወደ ጅማ አደረገዉ የሚል ሰማን፡፡

  የሚገርመዉ አየር መንገዱ ቢያንስ በሁለት ዕትም የ”ሰላምታ” መፅሔት ላይ ስለ ካፋ እና ስለ ኢትዮጵያ የቡና መገኛነት በሰፊዉ በመሁራን አስፅፎ ማሳተሙን ረስቶ ነዉ ወይስ፣ እንደሙዚየሙ ሁሉ ባለቤቱ ካልጠየቀ እኔስ ምን አገባኝ ብሎ ይሆን? ሁለቱም መልስ ያስኬዳል፡፡

  ግን ካፋ የቡና መገኛ መሆኑን፣ ይህም የአሁኑ ካፋ ዞን መሆኑን የሚያረጋግጠዉን ማስረጃ ሁሉ ከዓለም ላይ ማጥፋት አይቻልም፡፡ ትርፉ ትዝብት ብቻ ነዉ፡፡ ካፋ የቡና መገኛ ካልሆነ፣ ደግሞ ኢትዮጵያም የቡና መገኛ ስለመሆን መከራከር አትችልም፡፡ ምክንቱም ቡና የተገኘዉ ካፋ፣ የኢትጵያ አካል ከመሆኑ በፊት ብዙ ዓመታት አስቀድሞ ነዉና !!

  እዉነት ነዉ፤ በአንድ ወቅት “ጅማ ” የሚባል አዉራጃ፣ ከፋ በሚባል ጠቅላይ ግዛት ዉስጥ እንደ አንድ አዉራጃ በ1931 ዓ.ም መጠቃለሉንና የጅማ ከተማም፣ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የከፋ ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ እንደተደረገች ይታወቃል፡፡ ግን ደግሞ፤ በዚሁ ጠቅላይ ግዛት ዉስጥ ለጠቅላይ ግዛቱ ሥያሜ ምክንያት የሆነዉ ሌላ“ከፋ ” የሚባል ዋና ከተማዉም ቦንጋ የሆነ አዉራጃ፣ ይህም የካፋ ነገሥታት መቀመጫ የነበረ ከተማ እንደነበር ለመካድና፣ አዲስ ታሪክ ለመፃፍ ጊዜዉ አጭር አይሆንም?

  ካልሆነም አንዱን መምረጥ ካለብንና መስማማት ካለብን ደግሞ አባጅፋርም ካፈቾ ነበሩ፣ አሊያም ለካፋ ንጉሥ የሚገብሩ የኦሮሞ ባለባት ነበሩ ማለት ነዉ፣ ምክንያቱም የካፋ ታሪክና የቡና ታሪክ ረጅም ዕድሜ ያለዉ፣ ይህም በተለይ በዉጭ ምሁራን ተመዝግቦ የሚገኝ፣ የጅማ መንግሥትና የአባ ጅፋር ታሪክ ደግሞ በኦሮሞ ምሁራን ጭምር እንደተረጋገጠዉ ከ19ኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን ያልዘለለ ነዉና፡፡

  ሌላዉ ሁሉ ቢቀር ስለ ጅማና ስለግቤ ነገሥታት ታሪክና ዘመን “የገዳ ሜልባ ኦሮሚያ” የተባለዉን በአንድ የኦሮሞ ምሁር የተፃፈዉን መፅሐፍ እና ስለ ካፋ መንግሥት ደግሞ በታላቁ የኦሮሞ ምሁር በአቶ ይልማ ደሬሳ የተፃፈዉን “የ16ኛዉ መቶ ክ/ዘመን ኢትዮጵያ ታሪክ” የተባለዉን መፅሐፍ ማንበብ ብቻ ይበቃል፡፡

  ኬሮ ኬቶ

  Liked by 1 person

 2. በገዛ እግር ላይ መተኮስ፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ፡ አልተጀመረም !

  “Ethiopa; Land of Orgins’’ ተብሎ ፣

  “የቡና መገኛ ጅማ ነዉ”

  ከተባለ ቀጣዩ ተረት ደግሞ፣

  “የጥቁር አባይ መነሻዉ ካርቱም ወይም ካይሮ ነዉ” ማለትን ይሆናል፡፡

  ቡና ከካፋ፣ ከኢትዮጵያ ምድር ስለመገኘቱ መከራከር ትርፉ ጉንጭ ማልፋት ብቻ ነዉ፡፡ ባይሆን በዕዉቀት ለመጓዝ እና ለመምራት የተዘጋጀ ካለ፣ ይህንን ለማለት እፈልጋለሁ፡፡
  1. “ዶ/ር አቢይ የጅማን የኢንዱስትሪ ዞን በጎበኙበት ዕለት የካፋን የጫካ ቡና ጎበኙ” የተባለዉ ዜና ለምን ተዳፈነ ?
  2. የዶ/ር አቢይ የጅማ ጉዞ የተደረገዉ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድና የቱሪዝም ጉዳይን የሚመለከተዉ መሥሪያ ቤት (ባለሥልጣን ተብሎ ሳናጣጥም፣ ኮሚሽን ስለሚባል፣ እሱንም ሳናላምጥ ደግሞ ተመልሶ ሚኒስትር ስለሚባል፣ ግራ እንዳላገባ ነዉ)፣ በትብብር ‘’The land of Origins’’ ተብሎ የተጀመረዉን እንቅስቃሴ፣ ኢትዮጵያ የቡና መገኛ፣ በሚል መሪ ቃል ሊጀምር ነዉ፣ ከተባለ በሁዋላ ነበር፡፡ ታዲያ ክቡር ሆይ፣ የጉዞዉ ዓላማ ገና ሥራ ያልጀመረዉን ፓርክ ለመጎብኘት ወይስ፣ የቡና መገኛ ጉዳይ ዬት ይከበር የሚለዉን ለመወሰን ነበር?
  3. ጥቃቅን እና አሰልቺ ዜናዎችን የሚዘግቡትና የሆነ ጠቃሚ ነገር ይገኝ እንደሆነ ብለን ስናፈጥ፣ ቀኑን ሙሉ ምንነቱ ያለታወቀ ዝባዝንኬ የማንንም ባህል የማይወክል ዉዝዋዜና ዳንስ፣ እና መልዕክቱ ምን እንደ ሆነ ያልታወቀ ዘፈን አይሉት ንግግር ነገር ላይ ጊዜያችንንና ገንዘባችን የሚፈጁት ሚዲዎች ሁሉ ለምን ዝም አሉ?
  4. ጠ/ሚራችንም ልክ እንደቀደምት መሪዎቻችን ካፋ በድብቅ ደርሰዉ እንዴት ተመለሱ? በርግጥ የዚያን ጊዜዉ መሪያችን እንኳን አዳራቸዉን ያደረጉት እንዲሁ ያዉ ካፋ ዞን ዉሽዉሽ ስለነበረና፣ ግርግር እንዳይበዛ አድርገዉ በሦስት መኪና ብቻ በመጓዝ ሊደበቁ ቢሞክሩም አካባቢዉን መቃኘትን፣ በፍቃዱ መከወን ተደራቢና በፍቃደኝነት የሚሰራዉ ተግባሩ የሆነዉ ወዛደሩ ግን ስላያቸዉ መረጃዉ ወጣ፡፡ የአሁኑ የጫካ ቡና ጠባቂም እኮ ያዉ ከዚያዉ የወጣ አስተዋይ ታዛቢ ነዉ፡፡
  5. ታዲያ ይህንን የቀድሞ መሪያችንን ጉዞ ተከትሎም የዉሽዉሽ ሻይ ልማት ተሸጠ ተባለ፣ ቀጥሎም ሽያጩ የተደረገዉ የመንግሥት ባለሙያዎችና የተቀጠረዉ አማካሪ ድርጅት ከገመተዉ ዋጋ በጣም በወረደ ዋጋ ነዉ ተባለ፣ ቀጥሎም ባለቤቱ ህወሃት ነዉ፣ አይደለም ኢፈርት ነዉ፣ አይደለም የወ/ሮ አዜብ ናት፣ የለም የአላሙዲን ነዉ……… ማለቂያ የሌለዉ አስተያየት ቀጥሏል፡፡ ለዚህ መልስ የሚሰጥ መሪ መጣ ስንል ደግሞ፣ ሌላ ጥያቄ የሚያስከትል ጉብኝትና ዜና መስማት ጀመርን፡፡ እባካችሁ አሁን እንኳን ጊዜችንን ሳትበሉ ጉዳዩን አጥሩት፡፡
  6. ታዲያ ይህ ምኑም የማይገባኝ፣ አንዳንዴ ግን ለአጭር ጊዜም ቢሆን በወንበርና በጠመንጃ የሚታዘዝ፣ ታሪክ የሚባል ነገር ራሱን ደገመ? ግጥምጥሞሹ ግን አይገርምም? ፖቲካ ኢኮኖሚን ሲገዛ?
  7. ለተከበርከዉና፣ ገናናዉ፣ የባንዲራችን ተሸካሚ፣ መኩሪያችን…… የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት ጥያቄ አለኝ፣ 4.1. ከዚህ በፊት በምርምር የተደገፈ የምሁራን ፅሁፍ በ”ሰላምታ” መፅሔት ከሁለት በላይ እትሞች ላይ በጥልቀት ሥታትሙ ማንም አያነበዉም ብላችሁ ነበር? እኛ ግን በምሁራንና በተለይም በጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረተን ዕዉቀት እንወዳለንና መዝግበነዋል፣ ብዙዎችም አንብበዉታል፡፡ 4.2. በዓሉን ጅማ የምታከብሩት ታዛችሁ ነዉ ወይስ፣ ወደ ካፋ በአየር መድረስ ሥለማይቻል? በመኪና ደርሶ ለመመለስ እኮ እስከነዝግጅቱ ከሁለት እስከ ሥስት ሰዓት በላይ አይፈጅባችሁም ነበር እኮ፡፡ ያዉም መዘግየትና ጊዜ ብርቁ ላልሆነለትና መታወቂዉ ለሆነ አየር መንገድ ሦስት ሰዓት ለትልቅ ዓላማ ምን አላት?
  • ብቻ ሁሉም ነገር በገዛ ራሳችሁ እግር ላይ መተኮስ አይሆንም?፣ ያዉም በከፊል ለሽያጭ ለተዘጋጀ ድርጅት ይህ ተግባርና የፈፀማችሁት ዉዥንብር ትርፍ ያስገኝ ይሆን?
  • ባይሆንተስፋ እናደርጋለን፤ “ቡና የተገኘዉ ከጅማ ነዉ” ባላችሁበት አፍ፣ ቢያንስ መዳረሻዎቻችሁንና አገራችሁን በማስታወቅ በተከበራችሁበት በ “ሰላምታ መፅሔት”፣ ላይ ነገ ደግሞ “የጥቁር አባይ መገኛ የሆነችዉ ካርቱም ወይም ካይሮን ጎብኙ” ስትሉ እናገኝ ይሆናል፣ በዚህም ‘’Consistent approach and service ’’ በመባል ሌላ ገፅታ ትገነባላችሁ፣ ታተርፋላችሁም ብየ አስባለሁ፡፡

  8. በመረጃ ለምታምኑና ለሚመለከታችሁ ሁሉ ወገኖች ግን፣ ስለዚህ ዉዝግብና ዉዥንብር የህይወት ታሪክ የማዉቁን ላካፍላችሁና በራሳችሁ መንገድ አጣሩት፡፡
  ሀ. Oxfam የተባለ ግብረ-ሰናይ ድርጅት በዓለም ላይ ከቡና ምርት አምራቹ ደሃ ገበሬ ተጠቃሚ ባለመሆኑ ዓለም አቀፍ ዘመቻ በ1996 አካባቢ ከፈተ፡፡ ለዘመቻዉም ኢትዮጵያንና ካፋን የቡና መገኛ በመሆናቸዉ መንደርደሪያዉ አደረገ፡፡ በዘመቻዉ መጀመሪያና ማብሰሪያ የቀድሞዉ ጠ/ሚ/ር መለስ ተገኝተዉ ነበር፡፡
  ለ. በዚያ ወቅት Oxfam US ዉስጥ ይሰራ የነበረ “ዶ/ር” ነኝ የሚል ስሙም “አበራ” የተባለ፣ የጅማ አካባቢ ሰዉ ድርሰት ፅፎ ብቅ አለ፡፡ ይህንን ተረት፣ ተረት ድርሰት ደግሞ ስሙን “Research report” ብሎ አሰራጨዉ፡፡ ልክ እንደ አየር መንገዳችን እግሩ ላይ ያዉም በተደጋጋሚ ተኮሰ እንጂ አላተረፈም፡፡ ምክንያቱም፤ ሰዉየዉ ዶ/ር ከሆነ ቢያነስ ለሁለተኛና ለዶክተሬት ድግሪዉ ምርምር አድርጎ አሳትሟልና፣ የተረት ተረት ድርሰቱን የምርምር ሪፖርት ነዉ ማለቱ፣ ወይ ሰዉየዉ ድግሪዉን ገዝቶታል፣ ወይ በዚያች የትምህርት ዘርፍ ወቅት ተኝቶ ነበር፡፡ ይህ ካልሆነ በትልቅ ዓለት ላይ የተፃፈዉን የካፋን እና የቡናን ታሪክ ለመነቅነቅ በመሞከሩ የዋህነቱን አስነብቦ አልፎአል፡፡

  ሐ. ጉዳዩ ግን ቀጠለ፡፡ ይህ ወኔዉ አስከ አፍንጫዉ የሆነዉ ግለሰብ ደግሞ የዋህ ግን ተከታዮች አላጣም፡፡ በዚያዉ ዓመት፣ ምግባር ሰናይ ደርጅቱ ዘመቻ ሲጀምር፣ እርሱም በወቅቱ የግብርና ሚ/ር የነበሩትን የቅርቡን የቀድሞዉን ፕሬዝዳነታችንን ዶ/ር ተሾመ ሙላቱን፣ እንዲሁም አባ ዱላ ገመዳን ሁሉ ሳይቀር አንከርፍፎ ወደ ጅማ ወስዶ፣ “ይህ ነዉ እናት ቡና፣ እናም የቡና መገኛ ጅማ/ኦሮሚያ ነዉ” ተብሎ ተገባበዙ፣ በዜናም ብዙ ድርሰት ተነበበ፡፡ ሌላ ዉሸት፣ ያዉም አገራዊ ሃላፊነት የነበራቸዉን ዜጎች ያሳተፈ፡፡
  መ. ሚሊየነሙ ሲከበር ደግሞ ሌላ ጉድ ወጣ፡፡ ታሪክ አዋቂዉ አቶ መለስ ዜናዊ የሚወስኑበት ሰዓት ደረሰ፡፡ ቡና የተገኘዉ ካፋ፣ ወቅቱም ከበርካታ ዓመታት በፊት፣ የካፋ መንግስት ራሱን ችሎ ለብቻዉ በሚተዳደርበት ዘመንና ወቀት ነዉ፣ ቡና ‘’ coffee, café, cave…. ወዘተ) የሚለዉን ስም ያገኘዉም ከካፋ ነዉ፣ ስለዚህ ሚዚየሙን ቦንጋ ላይ ሥሩና ስሙንም “ብሔራዊ የኢትዮጵያ የቡና ሙዚየም” ይባል አሉ፡፡

  ይህንን ተከትሎ ደግሞ በወቅቱ የነበሩትም ፐሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ወደ ቦንጋ ተጉዘዉ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡

  ሲጠናቀቅ ደግሞ የቀድሞዉ ጠ/ሚ/ር ሃይለማሪም ደሳለኝ ደግሞ መርቀዉ ከፈቱና በዚያዉም የምርጫ ቅስቀሳ አድርገዉ ተመለሱ፡፡

  ሰ. ግን አሁንም ዉዥንብሩና ዉዝግቡ ቀጠለ፡፡ ቢታይ ቢታይ ሙዚየሙ ሥራ አይጀመርም፡፡ አንድ ነገረኛ ጋዜጠኛ ደግሞ አምና ነገሩን እንደገና ቆሰቆሰዉ፡፡

  ሙዚየሙን ጎብኝቶ፣ ለዓመታት ሥራ አለመጀመሩን ሲዘግብ፣ ዜና አንባቢዉ ደግሞ ከአዲስ አበባ ስቱዴዉ ሆኖ፣ ለማብራሪያ የጋበዛቸዉ አንድ አቶ አበራን የመሰሉ የባህልና ቱሪዝም ሚ/ር፣ የህግ ባለሙያ ተጠይቀዉ፣ ሌላ ዉሸት ደገሙ፡፡ እንዲህም አሉ፡ “ሙዚየሙ በዞኑ ተነሳሽነት ነበር የተገነባዉ”፣ ሆኖም ዉይይት እየተደረገበት ነዉ አሉ፡፡ ከዚህ መሥሪያ ቤት በላይ ማን ነዉ የሚሊኒየሙን አከባበር ሰነዶችና ታሪኩን የተረከበና የሚያዉቅ? ለምንስ ይዋሻል፣ የእዉቀት ማነስ ወይስ አሁንም ጭፍን የታሪክ ሥርቆትና ክህደት?

  እንግዲህ ከላይ የተጠቀሰዉ የቡና ቀን በዓል ጉዳይ ተከተለ፡፡ ነገም ሌላ ነገር ይከተላል፡፡
  ለአሁኑ ግን ስሰሰለቸኝ፣ ለጊዜዉ በዚሁ ላብቃ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ማለት ስለሚቻል እሰቲ ሌሎቻችሁም ሞክሩትና፣ ወይ እንደመር፣ አልያም በእግራችሁ ላይ ተኩሱ!!

  በገዛ እግር ላይ መተኮስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አልተጀመረምና !

  ከ.ኬ.ጋዎ

  Liked by 1 person

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: