1 Comment

 ለካፋ ሕዝብ እና ለካፋ ወጣቶች በሙሉ, ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ


ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ
ለካፋ ሕዝብ እና ለካፋ ወጣቶች በሙሉ

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በፈሬጆቹ አቆጣጠር Decmber 4 እና 5 2018 እ.ኤ.አ
ዓለም አቀፍ የቡና ኮንፌረንስ በአድስ አበባ እንደሚካሂድና ከጉባኤ በኃላ ለዓለም የቡና መገኛ ወደ ሆነዉ ካፋ ዞን እና ብቸኛዉ የብሔራዊ ቡና ሙዚዬም የሚገኝበት ቦንጋ ከተማ እናት ቡና ወደምትገኝበት ዴቻ ወረዳ ማንኪራ ቀበሌ ቡኒ መንድር ጉብኝት እንደሚደረግ November 2 post ማድረጉ ይታወቃል ፡፡ሆኖም ግን ባለስልጣኑ መ/ቤት 22/02/2011 ዓ.ም ወብ ሳይታቸዉ ላይ የለቀቁትን በመቀየር የአንድ ሕዝብ ታርክ በተዛባ መልኩ መረጃን ማሰራጨት ላይ ይገኛሉ ፡፡ ይህ ደግሞ የአንድ ሕዝብን ታርክ በተሳሳተ መረጃ የሀገራችን ሕዝብ በማሳሳት ሕዝብና ሕዝብን ለማጋጨት የተሰራ ግልፅ አደባባይ ላይ የወጣ ሀገርን የማተራመስና አሁን ሀገራችን የጀመረችዉን ሠላም ፣ልማትና ድሞክራስን የማድፈረስ በይፋ አደባባይ ላይ በካፋ ሕዝብ ላይ ታዉጆብናል ፡፡


የኢፌድሪ መንግስት ይህንን ሀገር የማፍረስ ሥራ የሰራ ተቋማትና በተቋሙ ዉስጥ እንደዚህ አይነት እኩይ ተግባር ላይ የተሰማሩትን በማጣራት በሀገራን ሕገ መንግስት መመሪያዉን በመከተል በሕግ አግባብ እርምጃ እንድወሰድባቸዉ አጠብቀን እንጠይቃለን ፡፡
እንደዚህ አይነተ ተግባሪ ላይ የተሰማራዉ ተቋም በአሁኑ ጊዜ የጀምሪነዉን ለዉጥ የማደፈረስና የሠላም፣ የልማትና የድሞክራሲ እንድሁም የሀገራን አንድነት ሆነ ብሎ ለማፍረስ ዝግጁ በመሆናቸዉ በተግባሪ አሳይተዋሉ ፡፡
የኢፈድሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 39 ንዑስ አንቀፅ 2 እና 3 ላይ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቋንቋቸዉን ፣ታርካቸዉን እና ባህላቸዉን ማስተዋወቅ መጠበቅና ማስጠበቅ ማሳደግ ይችላሉ ብሎ ደግገዋል ፡፡ እኛም የካፋ ብሔር የራሳችን ታርክ ባህልና ቋንቋ የሀገራችን ሕገ መንግስትን መሰረት ባደረገ መልኩ ማስጠበቅ መጠበቅ ማስሳደግ በኢትዮጵያዊ ዜግኔታችን መብት እኩል ተሰቶናል ፡፡
የቀድሞ ጠ/ሚኒስተራችን ኩቡር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ካፋ የቡና መገኛ መሆነዋን የብሔራዊ የቡና ሙዚዬም ምረቃ በዓል ቀን በፊርማቸዉ ያረጋገጡትን ፎቶ አንዱና ዋነኛዉ ማስረጃዎች መካከል አንዱ ነዉ ፡፡


እንድሁም የቀድሞ ግብርና ሚኒስተር 2ተኛ ሀገር አቀፍ የቡና ቀን ስከበር ቡና መገኛ ካፋ በጎበኙበት ወቅት የተወሰዱ ፎቶዎች በራሱ እየመሰከሩ ሀገር የማፍረስ ስራ በእኛ ላይ ተሰርቶብናልና የካፋ ዞን አስተዳደር በአስቸካይ ሀገርን የማዳንና ታርክን የመጠበቅ የማስጠበቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንድደረግ አጥብቀን እንጠይቃለን ፡፡

Birhanu Bibisa

One comment on “ ለካፋ ሕዝብ እና ለካፋ ወጣቶች በሙሉ, ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ

 1. ጥያቄና አስተያት

  ለደምኢሕህ እና ለደቡብ ክልል ምዕራባዊ ዞኖች የኢህአዴግ/ዴኢህዲን ባለሥልጣናት

  የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ ወዴት ያመራል ?

  1. ለደምኢሕህ

  የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ህብረት (ደምኢሕህ)፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለዘመናት የደረሰዉ ግፍና በደል ስለበዛ፣ ከዚህም የተነሳ ቁጭት የወለደዉ፣ በቁርጠኛ የካፋ፣የቤንች ማጂና የሸካ ልጆች የተመሰረተ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህም ለአካባቢዉ ህዝቦች ትልቅ ብሥራት ነዉ፡፡ ለዚህ ድርጅት መመስረት የለፉ፣ የግል ኑሮአቸዉን በድለዉ፣ ጊዜያቸዉን፣ ያላቸዉን ዉስን ገንዘብና ሃብት ሰዉተዉ፣ ለወገንና አገርን የማዳን ዓላማ ለቆሙ ወገኖች ታላቅ ክብር ይገባቸዋል፡፡

  እነርሱም እንደቀደምት ታሪካዊ ወገኖች፣ ስማቸዉን በታሪክ ዉስጥ አስፍረዋልና፣ ሊኮሩ ይገባል፡፡ ከአብዛኛዎቹ መሥራቾችና አመራሮች ማንነት እንደምንረዳዉ የፖለቲካ ልምድና ተሞክሮ (Background)፣ እንዲሁም የትተረፈ ሃብትና ጊዜ ኖሯቸዉ ሳይሆን፣ የወገናቸዉ በደልና ህመም በርትቶ ስለተሰማቸዉ፣ ወደ ፖለቲካ የገቡ፣ “እኛ ካልጀመርን ማን ይጀምራል” በማለት የተነሳሱ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቸዉን እንረዳለን፡፡

  ከእነርሱ በፊትም ከዚሁ አካባቢ የወጡ፣ የህዝብ ልጆች በተለያዩ ወቅቶች የሚችሉትን አድርገዋል፡፡ በተለይም በ1960 ዎቹ በነበረዉ ዉስብስብና ሁኔታ ዉስጥ ጠንካራና በተለያየ ደረጃ የተንቀሳቀሱና የተሳተፉ እንደነበሩ የሚታወቅ ሲሆን፣ ቁጥራቸዉ ቢያነስም ጉልህ ተሳትፎ የነበራቸዉ፣ ምሁራን ነበሩ፤ አሁንም አሉ፡፡

  ከዚያ ዘመን ሰዎች የተወሰኑት መስዋዕት ሲሆኑ፣ የተረፉትም በተለይ በ983 የካፋ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት (KPDU)፣ ሲመሰረት፣ ግንባር ቀደም ተሳትፎ ሊያደርጉ የሚችሉበትን ሁኔታ ህጋዊ ሥርዓቱ ባይፈቅድም፣ ከጀርባ ሆነዉ ከማበረታታትና ከመደገፍ ግን አልቦዘኑም ነበር፡፡ “በእድር ዓይነት መን ገድ ተሰባስበዉና፣ ተረሳን” በሚል ቁጭት ቢሆንም በ KPDU ዙሪያ የተሰባሰቡ የአካባቢዉን ህዝቦች፣ በርካታ ነበሩ፣ አብዛኛዎቹም እስካ አሁንም ድረስ ባለዉ የቁጭት መንፈስ፣ የተሰባሰቡ ቅን የህዝብ ልጆች ነበሩ፡፡

  ምንም እንኳን ገዢዉ ፓርቲ ኢህአዴግ በጠንካራ ክንዱ እየሸረሸረ ማዳከሙ የሚጠበቅ መሆኑ የሚጠበቅ ቢሆንም፤ በተለያየ ምክንያትና ይልቁንም ግን ዉስጥ ሰርገዉ በገቡ ለግል ጥቅማቸዉና ክብራቸዉ በቆሙ ጥቂት፤ ግን መቼም ቢሆን፣ ታሪክ ይቅር የማይላቸዉ ግለሰቦች ሥዉር ሴራና ድጋፍ፣ ኢህአዴግ፣ የካፋ ህዝቦች ዲሞክራሲያ ህብረትንና የተከታዮቹን ተነሳሽነት በቀላሉ አኮላሽቶ፣ ድርጅቱ እንዲበተን ሲያደርግ፣ የህዝባችንም ሞራል በከፍተኛ ደረጃ መጎዳቱ ይታወሳል፡፡ KPDU፣ በ960ዎቹ በነበረዉ ፖለቲካ፣ በተለያየ ደረጃ የፖለቲካ ተሳትፎና ልምድ በነበራቸዉ የአካባቢዉ ምሁራንና ወገኖች ድጋፍ የነበረዉ ቢሆንም በሚገርም ሁኔታ፣ የእነርሱ ልምድ ታክሎበትም እንኳን መቆጣጠር ተስኗቸዉ፣ ድርጅቱ ፈረሰ፣ የግለሰብ መሾሚያ ብቻ ሆኖ አለፈ፡፡ በገዢዉ ድርጅት አማካይነት ተመሳሳይ ጫናና ብተና በብዙ ድርጅቶች፣ በተለይም በደቡብ አካባቢ በተመሰረቱ፣ ልምድና የኢኮኖሚ አቅማቸዉም በተሻለ ደረጃ ላይ በነበሩት ላይ ጭምር የደረሰ ነበር፡፡

  ከብዙዎቹ በወቅቱ ከተንቀሳቀሱት ዉስጥ፣ ቀደም ብሎ ተደራጅቶ በትጥቅ ጭምር ሲታገል የነበረዉ የሲዳማ ሃርነት ንቅናቄ ብቻ እንቅስቃሴዉን ቀጥሎ፣እስከዛሬ በአገር ዉስጥም ጭምር ለሲዳማ ልጆች ተነሳሽነት መሰረት ሆኖ ቀጥሏል፡፡ የሲዳማ ዞን፣ የሚያቀነቅነዉና መሆኑ የሚቀር የማይመስለዉና፣ ለመንግሥትም የጉሮሮ አጥንት ሆኖ የቀጠለዉ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ፣ በተደጋጋሚ መቅረቡም የዚህ ድርጅት አስተምህሮ ዉጤት መሆኑን መካድ አይቻልም፡፡

  ለደምኢሕህ ም፣ የ KPDU እንዲህ ማክተም ልምድ ሊወሰድበት ይገባል፡፡ በተለይም ደምኢሕህም የህዝባችንን ብሶት መቅረፍ ሳይችል እንዳየሽመደመድ፣ ጥረቱ ከተጨናገፈ፤ ይልቁንም ደግሞ እስከወዲያኛ የህዝባችንን ሞራል እንደገና እንዳያዳሽቀዉ እና ዳግም እንዳያንሰራራ ተስፋዉን እንዳያጨልመዉ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል፡፡

  ስለዚህ በመጀመሪያ የፖለቲካ ድርጅትና ዕድር ልዩነቱ ሊታወቅ ይገባል፡፡ በምርጫ ወቅት ሁሉም ደጋፊና፣ ድርጅቱን የተሻለ አማራጭ አድርጎ የወሰደ ሁሉ ሊሳተፍበት ይችላል፤ ግን የድርጅቱ አመራሮች አቅጣጫቸዉንና ግባቸዉን ወስነዉ፣ በዚያዉ መሰረት መምራት ይገባቸዋል፡፡

  ከሁለት ተፎካካሪ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ጋር ተባብረዉ እየሰሩ መረጃና እንቅስቃሴን፣ ከአንዱ ወደ ሌላዉ እያቀበሉ በሁለት ቢላዋ የበሉ፣ እና የሚበሉ ግለሰቦች ሁሌም ይኖራሉ፡፡ ከዚህም አካባቢም ተመሳሳይ ሰዎች እንደነበሩ በተለያየ ጊዜ በነበራቸዉ ተግባር ጭምር ይታወቃል፡፡

  ስለዚህ እነዚህ በቀና መንፈስና በወገን ጥቃት ተቆጭተዉ የተሰባሰቡ ዉድ ልጆች፣ ልምድ ካላቸዉ ቢማሩ፣ እነዚህ በተለያየ የፖለቲካ ሂደት ተሳትፎአቸዉ ልምድ ያዳበሩ እና፣ ጥግ የያዙ ታላላቆች ሃላፊነታቸዉን ቢወጡ ተገቢ ይሆናል የሚል እምነት አለን፡፡ አለበለዚያ ጥግ ይዞ እያዩ፣ ቀና ወገኖች የጀመሩት ዓላማ ሲደናቀፍ ተግባሩን ማጣጣል፣ ማሽሟጠጥ ወይም መቆጨት ትርጉም የለዉም፡፡

  በአሁኑ ጊዜ ያለዉ ትልቁ ጥንካሬ የህዝቡ ብሶት ሥር መስደድ፣ እንዲሁም በርካታ ፈጣንና የበሰሉ ወጣቶች ለመሳተፍና ለመምራት ዝግጁ መሆናቸዉ ነዉ፡፡ ዋናዉ ፈታናና ዉስንነት ደግሞ የህዝቡ ድህነት፣ የልምድና የአቅም ማነስ ናቸዉ፡፡ ያለዉ ዕድል ደግሞ ህጋዊ የሆነ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ የሚያሰችል የመንግሥት አመራር በወቅቱ የማዕከሉን መንግሥት መያዙሩ፣ እና ተቀራርቦ መሥራት ከተቻለም ተጨማሪ አቅም ሊሆን የሚችል የፖለቲካ ድርጅቶች በአገሪቱና በአቅራቢችን መኖር ናቸዉ፡፡ አሥጊና ፈታኝ ሁኔታዎች ደግሞ፣ በዉስጥም በዉጭም ያለና የሚከሰት፣ የሰርጎ ገቦች ሚና እና በተለይም በአካባቢዉ በአንድነት ለመቆም የሚያንገራግሩ አካላት መኖር ነዉ፡፡ ደምኢሕህ እነዚህን ከግምት ቢያስገባ ጠቃሚ ይሆናል፡፡

  ደምኢሕህ ገና በድርጅቱ ፕሮግራም ላይ ማወያየት፣ ማስተዋወቅና ማዳበር አልጀመረም፡፡ ድርጅቱ፣ የፖለቲካ እንደመሆኑ መጠን ለወደፊቱ መጠላለፍ እንዳየመታ አባላቱንና በየደረጃዉ የሚኖሩ መሪዎች በጥንቃቄ የመመልመልና የማደራጀት ተግባር ብዙ ይቀረዋል፡፡ ለምርጫ መዘጋጀት እና ማሸነፍ ባይችል እንኳን ልምድ ሊወሰድበት እንዲቻል መዘጋጀጥና መንቀሳቀስ ይገባል፡፡ ከተሳተፈም እንደምርጫዉ ዉጤት የሚኖረዉን ሁኔታ (Scenarios) ከግምት ያስገባ የአጭር ጊዜና የመካከለኛ ጊዜ መስመርና ግብ መወሰንና፣ ለዚህም መዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡

  2. ለአካባቢዉ የኢህአዴግ/ደኢህዲን ባለሥልጣናት

  • የተፎካካሪ አቀባበል፣ የዞንና የወረዳ ጥያቄና የሰሞኑ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዉሳኔ ምን እንማራለን፣ ከቡና ቀንና ከአየር መንገዳችን ምን መማር ይቻላል ?፡

  የምዕራብ ዞኖቹ የኢህአዴግ/ደኢህዲን ባላሥልጣናት፣ የወቅቱ ፋሺን ስለሆነ ብቻ ወይም ከልባቸዉ አምነዉ እንደሆነ ባይታወቅም የደምኢሐህን አመራሮች ከዉጪ ሲገቡ መቀባላቸዉ ጥሩ ሆኖ፣ የተቀበሉት የገዢዉ መንግሥት ካድሬዎችና ሃላፊዎች፣ ከመጣዉ የደምኢሕህ አመራሮች ጋር በግልፅ መነጋገር አለባቸዉ፡፡ መታወቅ ያለበት ግን ለይሥሙላ የተደረገ አቀባበል ከሆነ፣ መሰረታዊ ችግሮችን የማይፈታ፣ ሆይ ሆይታ በመሆኑ እሳት ከማዳፈን ያለፈ ትርጉም የለዉም፡፡

  ደምኢሕህ በቀጣዩ ምርጫ ከተሳተፈም በቀጣዩ በአካባቢዉ ሌላዉ ዋና ተፎካካሪና አቅም ያለዉ ኢህአዴግ/ደኢህዲን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዉጤቱ ምንም ይሁን ምን ግን እነዚህ ሁለቱም ወገኖች ማወቅ ያለባቸዉ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ችግር በደቡብ ክልል ሥር ሆኖ በምንም መንገድ እንደማይፈታ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል፡፡

  ከሲዳማ የክልልነት ጥያቄም ልምድ ሊወሰድ ይገባል፡፡ የሲዳማን የክልል ጥያቄ በተደጋጋሚ ያቀረበዉ የኢህአዴግ/ደኢህዲን አባላት የሚመሩት የዞኑ መስተዳድር ነዉ፡፡ ሂደቱም ኢህአዴግ ራሱ ከፍተኛ ሥልጣን የሰጣቸዉ ሚኒስትሮችና አምባሳደሮች ጭምር የተሳተፉበት መሆኑን ማስተዋል ይገባል፡፡ ያለዉን ተጨባጭ ችግር ዉስጥ ለመገንዘብ፣ በኢህአዴግ ዉስጥ በተለያየ ደረጃ ተሳትፈዉ ካለፉት በላይ ማንም በቅርበት መረዳት ይችላል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ከህዝቡ በላይ ምንም የመጨረሻ መደበቂያና ተገን እንደማይኖር መገንዘብ ተገቢና መሰረታዊ ጉዳይ ነዉ፡፡ ሲዳማ ክልል ሲጠይቅ፣ የምዕራብ ዞኖች መስቀልንና አንዳንድ አጋጣሚዎችን ጠብቀዉ፣ በመገናኘት በልቶና ጠጥቶ ከመለያየት ያለፈ መጠየቅ ያልቻሉት ለምን እንደሆነ መጠየቅ ወቅታዊ ጉዳይ ነዉ፡፡ ህዝቡና ወጣቱስ ከመሰራተዊዉ ችግርና መፍትሄ ይልቅ በምልክቶችና በጥቃቅን ዉጤቶች ላይ በተበጣጠሰ መንገድ ማተከሩ ለምንድ ነዉ፡፡ በእኔ እምነት እንደጥፋታቸዉ መወገዳቸዉ በማይቀሩት የቀበሌና የወረዳ ካድሬዎች ላይ እየተረባረቡ መቀጠሉ፣ የማስታገሻ ክኒን ከደቡብ ገዢዎች ከማግኘት ያለፈ ዉጤት እንዳላመጣ ማይት ተገቢ ይሆናል፡፡

  ደምኢሕህ ገና ዓላማዉንና ግቡን እንዲያሳዉቅ ይጠበቃል፡፡ የደቡብ ክልል አካል የሆኑ የምዕራብ ዞኖችና ወረዳዎች ባለሥልጣናት ግን የኢህአዴግ/ደኢህዲን አገልጋዮች ሆነዉ፣ አካባቢዉን በደቡብ ክልል ሥር ያስጨፈለቁ ቀጥተኛ ተሳታፊዎችና መሪዎች እንደነበሩ ሊታወቅ ይገባል፡፡ እነዚህ በየዞኑና በወረዳዎች፣ በክልሉ ደረጃም ሆነ በማዕከል ሆነዉ የህዝባቸዉ ሰቆቃ እንዲቀጥል የደገፉ፣ የመሩና የተሳተፉ፣ ወይም በዝምታ ያለፉ የኢህአዴግ አባላት ንሥሐ መግባትና ህዝባቸዉን መካስና ከህዝባቸዉ ጋር መታረቅ ከእነርሱ የሚጠበቅ ነዉ፡፡
  በሰሞኑ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዉሳኔ፣ የጨና ወረዳ ለሁለት ስለተከፈለ፣ ወይም የሸኮ፣ የመዠንግርና፣ የማጂ ጥያቄ ከበረታ ደግሞ በተመሳሳይ በደቡብ ገዢዎቻችን ችሮታ ወረዳ ወይም ዞን መሆን፤ የህዝቡን ጥያቄ ለጊዜዉ ለዘብ ያደርግ ካልሆነ በስተቀር፣ መሰረታዊ ለዉጥ ስለማያመጣ ሌላ የማታለል ተግባር መሆኑን ማረጋገጥ ይችል እንደሆነ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ አይሆንም፡፡

  በኢትዮጵያ ሚሊኒየም የበዓል አከባበር አጋጣሚ ካፋ ዞን የተገነባዉ ብሄራዊ የቡና ሙዚየም ምን ፈየደ? የካፋን ዞን የመንግሥት ሰራተኞች ደመወዝ በተደጋጋሚ ከማስቆረጥና፣ ከዚያም ተጨማሪ ቁዘማ፣ መከፋትና ተስፋ መቁረጥ ካልሆነ በስተቀር ምን አመጣ?
  የሚገርመዉ ዉሳኔዉ በተሰጠበት በዚያ ወቅት በመንግሥት ዉስጥ ከነበረ ዉስጥ አዋቂ ግለሰብ በኢሳት ቲቪ ሲነገር በቅርቡ እንደሰማነዉ፣ ደግሞ ፣ ለካስ ቦታዉ ቦንጋ እንዲሆን የተወሰነዉ በጥቂት የካፋ ልጆች ትግልና፣ ማንበብ የማየሰለቻቸዉና ታሪክ አዋቂዉ የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚ/ር አቶ መለስ ታሪክ አጣቅሰዉ በወሰኑት ዉሳኔ ነዉ አሉ፡፡

  አፈሩ ይቅለላቸዉና ለካፋ ሁለት ወንበር (በርጩማ) በሽግግሩ ጊዜ ተይዞ የቆየልን፣ ለKPDU የተሰጠዉና እስኪደራጅም ተጠብቆ የቆየዉ የካፋን ታሪክ እየጠቀሱ አቶ መለስ በወሰኑት መሰረት ነበር ሲባል ሰምተን ነበር፡፡ መጨረሻዉ ግን የድርጅቱም ጉዳይ ያዉ እንደሙቀጫ ተንደባለለ፣ ወይም ሌላዉ የቤት ሥራችን ሁሉ እንዲሰራልን መጠበቅን አስተምሮ አለፈ እንጂ፡፡
  “የተሰጠ ሥልጣን ደግሞ በተፈለገ ጊዜ ተመልሶ ይወሳዳል” የሚለዉን መገንዘብ ያልቻለዉና ወንበሩ የሞቀዉ የምዕራብ ዞኖች አመራርና ህዝቡም ጭምር ልክ ለKPDU ወንበር የሰጠዉም ሆነ መልሶ ያፈራረሰዉ በግንባር ቀደምትነት ሰጪዉ መሆኑን በማስታወስ፣ የህዝባችንን መፍትሔ ከደቡብ ባለሥልጣናት በችሮታ ለመዉሰድ እየጠበቀ ከሆነ በሬዉን ስትከተል ያመሸችዉንና በማጨረሻ ቤቱ ሲገባ ረግማዉ ጦሟን ያደረችዉን እንዳይሆኑ እንመክራለን፡፡ ሲዳማ ክልል ሲሆን ሲአን ሥልጣን ቢይዝ እንኳን፣ የሲዳማ ዞን የኢህአዴግ/ደኢህዲን አባላትና መሪዎች ዕድልና ቦታቸዉ ይገመታል፣ አብረዉ ተባብረዉ ይሰራሉ፣ ህዝባቸዉንም ያገለግላሉ፡፡

  እንደእዉነቱ ከሆነ ሲዳማ የክልል ጥያቄ በጠየቀበት ወቅት የምዕራብ ዞኖች ቢሆኑ ኖሮ የጠየቁት እስካሁን ምላሽ አያገኝም ነበር ? ስለዚህ ተባብሮ ለመሥራት መዘጋጀትና መጀመር ብልህነት ነዉ፡፡

  ይባስ ተብሎ ሰሞኑን ደግሞ “መደመር፣ የለዉጥ ሃይሉን መደገፍ…… ወዘተ” እየተባለ፣ በሚዘፈንበት ወቅት፣ ድሮዉንም ተሳፍረንበት ወይም ተቀጥረንበት የማናዉቀዉ የባንዲራችን ተሸካሚ ሆነዉ አየር መንገዳችን ”Land of Origins’’ በሚል ስለቡና ሊያስተዋዉቅ፣ በየማስታወቂያዉ ስለ ኢትዮጵያ የቡና መገኛነት የቀሰቀሰበትን የበዓል አከባበር ከካፋ ወደ ጅማ አደረገዉ የሚል ሰማን፡፡

  የሚገርመዉ አየር መንገዱ ቢያንስ በሁለት ዕትም የ”ሰላምታ” መፅሔት ላይ ስለ ካፋ እና ስለ ኢትዮጵያ የቡና መገኛነት በሰፊዉ በመሁራን አስፅፎ ማሳተሙን ረስቶ ነዉ ወይስ፣ እንደሙዚየሙ ሁሉ ባለቤቱ ካልጠየቀ እኔስ ምን አገባኝ ብሎ ይሆን? ሁለቱም መልስ ያስኬዳል፡፡

  ግን ካፋ የቡና መገኛ መሆኑን፣ ይህም የአሁኑ ካፋ ዞን መሆኑን የሚያረጋግጠዉን ማስረጃ ሁሉ ከዓለም ላይ ማጥፋት አይቻልም፡፡ ትርፉ ትዝብት ብቻ ነዉ፡፡ ካፋ የቡና መገኛ ካልሆነ፣ ደግሞ ኢትዮጵያም የቡና መገኛ ስለመሆን መከራከር አትችልም፡፡ ምክንቱም ቡና የተገኘዉ ካፋ፣ የኢትጵያ አካል ከመሆኑ በፊት ብዙ ዓመታት አስቀድሞ ነዉና !!

  እዉነት ነዉ፤ በአንድ ወቅት “ጅማ ” የሚባል አዉራጃ፣ ከፋ በሚባል ጠቅላይ ግዛት ዉስጥ እንደ አንድ አዉራጃ በ1931 ዓ.ም መጠቃለሉንና የጅማ ከተማም፣ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የከፋ ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ እንደተደረገች ይታወቃል፡፡ ግን ደግሞ፤ በዚሁ ጠቅላይ ግዛት ዉስጥ ለጠቅላይ ግዛቱ ሥያሜ ምክንያት የሆነዉ ሌላ“ከፋ ” የሚባል ዋና ከተማዉም ቦንጋ የሆነ አዉራጃ፣ ይህም የካፋ ነገሥታት መቀመጫ የነበረ ከተማ እንደነበር ለመካድና፣ አዲስ ታሪክ ለመፃፍ ጊዜዉ አጭር አይሆንም?

  ካልሆነም አንዱን መምረጥ ካለብንና መስማማት ካለብን ደግሞ አባጅፋርም ካፈቾ ነበሩ፣ አሊያም ለካፋ ንጉሥ የሚገብሩ የኦሮሞ ባለባት ነበሩ ማለት ነዉ፣ ምክንያቱም የካፋ ታሪክና የቡና ታሪክ ረጅም ዕድሜ ያለዉ፣ ይህም በተለይ በዉጭ ምሁራን ተመዝግቦ የሚገኝ፣ የጅማ መንግሥትና የአባ ጅፋር ታሪክ ደግሞ በኦሮሞ ምሁራን ጭምር እንደተረጋገጠዉ ከ19ኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን ያልዘለለ ነዉና፡፡

  ለምሣሌ ሌላዉ ሁሉ ቢቀር ስለ ጅማና ስለግቤ ነገሥታት ታሪክና ዘመን “የገዳ ሜልባ ኦሮሚያ” የተባለዉን በአንድ የኦሮሞ ምሁር የተፃፈዉን መፅሐፍ እና ስለ ካፋ መንግሥት ደግሞ በታለቁ የኦሮሞ ምሁር በአቶ ይልማ ደሬሳ የተፃፈዉን “የ16ኛዉ መቶ ክ/ዘመን ኢትዮጵያ ታሪክ” የተባለዉን መፅሐፍ ማንበብ ብቻ ይበቃል፡፡

  ብቻ፣ እንዲያዉ ይህንን ለምሣሌ ያህል አነሳሁት እንጂ ጉዳያችንስ ከዚህ ሰፋ ያለ ነዉ፡፡
  ይልቅስ የዛሬ 30 እና አርባ አመት አካባቢ የተመሰረቱ ድርጅቶች ዓርማ አገሪቱን ሲያጥለቀልቅ፣ ቢያንስ በታሪክ ለተመዘገቡት ከ600 እና ከዚያ በላይ ዓመታት በተፃፈ ማስረጃ፣ የተመሰከረለት መንግሥታዊ ሥርዓት፣ ዘዉድና የራሱ (ነጭ፣ ሰማያዊና ቀይ) ባንዲራ የነበረዉን ህዝብ ወክለዉ የገቡትን የደምኢሕህን አመራር ወገኖች፣ የራሳችንን ሙሉ በሙሉ ጥለን በአረንጓዴ ቢጫዉ ብቻ መቀበላችን፣ የዋህነትን፣ ሥንፍናን ወይም አሁንም የት ይደርሳሉ የሚል መልዕክትና አስተሳሰብ ከማስተላለፍ በላይ አይመስለንም፡፡
  3. ለሁላችንም

  ስለዚህ ሁላችሁም በፖለቲካ መሪነት ላይ ያላችሁ መስመራችሁን በግልፅ አሳዉቁን፡፡ ካልሆነ ደግሞ ዘፋኙ እንዳለዉ፤

  “እኔስ ከዚህ ወዲያ ሌላ ሰዉ አልወድም፣ በበረደዉ ልቤ እሣት አላነድም” ብሎ አርፎ የተቀመጠዉንና የራሱን ጊዜ እየጠበቀ ያለ ህዝብ ስሜት ማንገጫገጩን ብትተዉ ተገቢ ይሆናል፡፡

  ለምዕራብ ዞኖች ባለሥልጣናት፣ የምመክረዉ ደምሕህን በመቀበል የተደረገዉም መሸነጋገል ብቻ ከሆነ ለማንም አይጠቅምም፡፡ ደምኢሕህ ደግሞ ወደ ህጋዊ ተቋምነት ተሸጋግሮና፣ በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ አደባባይ ይዉጣና እንየዉ፡፡ ይህንን ካልቻላችሁ ደግሞ ህዝባችን ቢያነስ እስካሁን ድረስ በልቶ ማደር አላቃተዉምና፣ ከእጅ ወደ አፍ ኑሮዉን እንዲቀጥል፣ እንደህዝብ ለማደግና ለመበልፀግ የሚያቀርበዉን ጥያቄ ገፍቶ በራሱ ጊዜ እንዲጠብቅ ብትተዉት ይሻላል፡፡
  ይህ ደግሞ በመጨረሻ ዉጤቱ ህዝቡን ለሌላ የደቡብ ክልል መሰል ገዢዎች አሳልፎ መስጠት ወይም ሌላ ሃይል ከደቡብ ምዕራብ አካባቢ እንዲፈጠር መንገድ መጥረግ ይሆናል፡፡

  ዋናዉ ችግር ግን፣ ያኔ ሂደቱም፣ ሆነ ዉጤቱ፣ አንድ ዓይነት ሊሆን አይችልም፡፡

  ኬሮ ኬቶ

  Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: