Leave a comment

እዉን ካፋን ያገለለ ፖሌቲካ ለኢትዮጵያ ዋስትና ይሆናልን?


by Tekle’ab Bullo 

እዉን ካፋን ያገለለ ፖሌቲካ ለኢትዮጵያ ዋስትና ይሆናልን?
ዉድ አምባቢያን ሰሞኑን እየታዩና እየተንጸባረቁ ባሉ የካፋ ህዝብ ላይ በተቃጡ የማግለል ፖሌቲካና ታሪክ ሽምያ ላይ እይታየን ለማንፀባረቅ እገደዳለሁና እነሆ…….
በመጀመሪያ ሁላችንም እንደሰዉም ሆነ እንደ ኢትዮጵያዊ ልንረዳ የሚገባን ጉዳይ ቢኖር ወንድሙን ገድለዉና አግልለዉ በሰላም የኖረም ይሁን የከበረ የለም ለወደፊትም በፍፁም ልኖር አየችልም፡፡ ታድያ ይህ እዉነታ እንዳለ ሁኖ ሰሞኑን ካፋን ገድለንና አግልለን እንክበር ዘመቻ ከአንድ ወንድምም ሆነ ወገን የማይጠበቅና ዉጤቱም የከፋ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም፡፡
በሃገራችን ከቅርብ ጊዜ ወድህ የማይገባንና ጥሩ የሆነዉን ሁሉ የኔ ነዉ የኛ ነዉ የሚሉ ዘመቻዎች የተለመዱ ቢሆኑም ካፋ ላይ የተቃጣዉ አሳፋሪና ለሰሚም ፈገግ የሚያሰኝ ነዉ- የታሪክ ሽምያ በሉት ቅምያ እና ማንነት የመጨፍለቅ ፖሌቲካ፡፡
ካፋ የገዛ ስሙን በነጮች /ዉጮች/ቋንቋ ለቡና መጠርያ ካዋሰም ሆነ ቡን የምትባለዉን ትንሿ መንደሩን ለኢትዮጵያዊያን ቡና ብላችሁ ጥሩበት ብሎ ለቡና መጠርያ ካዋሰ እነሆ በ4ኛዉ ክ/ዘመን መሆኑን ፍሊፕ ብርወሲ ኢትዮጵያ በሚል መፃሐፍ ፍንትዉ አድርጐ አሥቀምጦታል፡፡ ይህን እዉነታ የካዱ የካፋንና የቡናን እናትና ልጅነት ዝምድና አምኖ መቀበል ያልቻሉ የለላን ታሪክ የራሣቸዉ ለማድረግና ለመቀማት የቋመጡ አብሮ የኖረን ማህበረሰብ ለማባላት ቆርጦ የተነሱ አካላት የተወሰኑት በጅማሬያቸዉ የተቀጩ ሲሆን አድስ የተቀላቀሉትም ወንድሙን የገዳ መጨረሻዉ አያምርምና ተቆጠቡ፡፡
ማሳያ 1/ ከአመታት በፍት በሰራዊት ፍቅረና በሸዋፈራዉ ደሣለናኝ የተመራዉ የዉሸት ማሥታወቂያ ቡድን ከዚህ ቀደም በነበረዉ ፅሁፍ ታሥተዉሉ ይሆናል መጨረሻዉ ሣያምር ካፋ ላይ በሰነዘረ እጅ እራሱን በራሱ አጥፍቶ ከነ ድምፁ መጥፋቱ የቅርብ ጊዘ ትዉሥታችን ነዉ፡፡
2/ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስተር በህግ አገልግሎት ዳይረክተር አቶ በላቸዉ ድሪባ አማካኝነት በካፋ የቡና መገኛነት የተዛባ መግለጫ የሰጠቢሆንም ከዚህ ቀደም በነበረዉ ፁሑፍ ታሥተዉሉ ይሆናል መግልጫዉ በህዝቡ የተወገዘ የተሳለቁበት ከመሆኑም በላይ ይህ ከተከሰተ አንድ አመት ባልሞላ ግዘ ዉስጥ ሚኒሥተር መስርያ በቱ ሰዉ አልበረክት ብሎት 4ኛ ሰዉ መቀየሩ ጉድ የምያሠኝ ነዉ፡፡ የቦንጋ ቢሄራዊ ቡና ሙዝየምም ከተጠናቀቀ 4 ዓመት ብሞላም ሥራ አልጀመረም፡፡
3/ ዛሬ ላይ ደግም የቡናና ሻይ ባለሥልጣን የአለም ቡና ቀንን(ህዳር 25 እና 26) በ ኢትዮጵያ ለማክበር በምያደርገዉ ዝግጅቱ ላይ በፈሥ ቡክ ገፁ በሰራዉ ማሥታወቅያ ከቡና ኮንፍረንሥ በኃላ የቡና መገኛ ወደ ሆነችዉ ጅማ ዞን የምደረግ ጉብኝት እንዳያመልጥዎ ካሁኑኑ ይመዝገቡ በሚል የበረ ወለደ ታሪክ ማሥታወቂያ መሥራቱ አንድም ለማህበረሰቡ ያለዉን ንቃት ያሳየበት በለላም በኩል ህዝብን ከህዝብ ጋር ለማባላት የጠነሰሰዉ ሰራ ፍንትዉ አድርጎ የ ምያሳይ ሃቅ ነዉ፡፡
4 / እጅግ በጣም የሚገርመዉ ይህ ሁሉ ጉድ ሲደረግ ሃይ ባይና ሥርዓት ያዙ የሚልም ሆነ ካፋን እንደ ህዝብ የሚቆጥር የመንግሥት አካል ያለመኖሩ እዉነት ካፋን ያገለለና የገደለ የኢትዮጵያ የነገ እጣ ፈንታ ያምር ይሆን የሚል ጥያቀ ይፈጥርብኛ ምክንያቱም የካፋ ህዝብ ጥንትም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር ቀድሞ የተደመረ ግን አሁን ባለዉ ስርአት ግን የተረፈዉ ከመደመር ይልቅ መጨፍለቅ ከመታቀፍ ይልቅ መገለሉ እጅግ ያሣዝናል፡፡
5/ ካፋ በታርክ ገናና ባለፉት ስርአቶች በክፍለ ሃገርና በጠቅላይ ግዛት ደረጃ ለማከላዊ መንግስት ታሪኩ ጠፍቶ እራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ ተነፍጎ ሃብት ንብረቱ ተዘርፎ የበይ ተመልካች ከመሆን አልፎ ጉዳዩን ለማሥፈፀም ሃገር አቋርጦ ክልል የሚፈልግ ማህበረ ሰብና ክልል ፍለጋ ከ750 -1200ኪ/ሜ የምጓዝ መሆኑ እዉን ይህ መንግሥት ለዚህ ህዝብ ክብር አለዉ ወይ ያሥብላል
እናም ከዚህ ትዝብት በመነሣት
ሀ/ የካፋ ህዝብን የወከላችሁ ፖሌቲከኞች፤ አመራሮችና የመንግሥት አካላት ሁሉ እመኑኝ የናንተ ስልጣን ያለ ህዝባችሁ ጤዛ ነዉ፤ የናንተ ክብር አሣድጎ ካከበራችሁ ህዝብ ዉጭ ህልም ነዉ፤ የናንተ ሃይል ያለ ህዝብ ፍቃድ ቅዠት ነዉና ህዝባችሁን አሥከብራችሁ ተከበሩ፤ ታሪኩን አሥጠብቃችሁ በታሪክ መዝገብ ዉሥጥ ኑሩ፤ ለህዝብ ክብርና ድምፅ መኖርን ከሲዳማ ባለስልጣናት ተማሩና የካፋን ህዝብ ታሪክ አስጠብቃችሁ እራሱን በራሱ የማስሥተዳደር መብቱን አሥጠብቃችሁ ከህዝባችሁ ጋር አብሮ መክበርን አሣዩን ፡፡
ለ/ ከካፋ አብራክ የወጣችሁ ምሁራን የምሁርነት መገለጫዉ የህዝብ ድምፅ መሆኑን ተገንዝባችሁ የተደበቀዉን እዉነታ ቆፍራችሁ አዉጥታችሁ የህዝብን ንቃተ ህሊና ቀሥቅሣችሁ ለራሱ መብት እራሱ እንድታገል በማስቻል የካፋን ህዝብ ታሪክ በማደስ ዳግም ለማዕከላዊ/ፈደራል/ መንግስት ተጠሪ የሆነ ካፋን በመፍጠር የታሪክ አካል ሁኑ
ሐ/ ወጣቶችና ሁሉ ም የህዝብ አካላት ሁኑ ለህዝባችሁ ኑሩ የራሣችሁን መብት በራሣችሁ ድምፅ አስከብሩ፤ ማንንም አትጠብቁ፤ ፈርዶብን በእኛ ሀገር ያላላለቀሰ ህፃን አይጠባም የሚል ብህል ይሰራል፡፡ ዝም ማለት ጎድቶናል፤ አስንቆናልና ያለንን ሀብት ንብረት ሳናወድም ወንድም እህት ኢትዮጵያዊያንን ሳንጎዳና ሳናስከፋ ኩሩ ባህላችንን ጠብቀን በሰላማዊ መንገድ ድምፃችንን የምናሰማበት ተከታታይ የአንድ ሳምንት ሰላማዊ ሰልፍ በሁሉም የካፋ አካባቢዎች እንዲጠራና እዲካሄድ በአከብሮት እጠይቃለሁ፡፡
መ/ ሌሎች የኢትዮጵያ ወንድም እህቶቻችን ሁሉ ከዚህ ከተገፋና ከተገለለ ካፋ ህዝብ ጎን በመሆን የዘወትር አብሮነታችሁን እንድታሳዩን አደራ እላለሁ፡፡
ሠ/ የፈደራል መንግስትና የሚድያ አካላት የዚህን የካፋ ህዝብ ጥያቄ መልስ ችላ ከማለት አስቸኳይ መልስ የምገኝበትን መንገድ በመቀየስ እንድታግዙ እያልኩ በተለይ የለዉጡ መሃንድስ የሆኑ ጠቅላይ ሚንስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ከ2 ወር በፊት አኔዚህ ጥያቄዎች በወጣቶች አማካኝነት ሰነድ ተዘጋጅቶ የደረሰሎት መሆኑን እያስታወስኩኝ የርሶ መንግስትም ዛሬም ይህ ህዝብ በረሶ ተስፋ አልቆረጠምና ይህን የካፋ ህዝብ ብሶትና ጥያቄ መልስ እንድያስገኙልንና ህዝቡን እንዲክሱ አደራ እላለሁ፡፡
ረ/ በአጠቃላይ በሁሉም አካላት ትብብር የቡና መገኛዋ ፤ የአለማችን አረንጓዴ ሳንባ፤ የብዙ እንቨስትመንቶች መዳረሻና የአብሮነት ተምሳሌት የሆነችዉ ካፋ እራሷን በራሷ የማስተዳደር መብት እንዲረጋገጥላትና የቡና ባለቤትነት ታሪክ ላይ የሚነሱ ልበወለድና የተሳሳቱ አስተያየቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲቆም ላሳስብም አደራ ለማለትም እወዳለሁ፡፡
ሉሲን ከአፋር ቡናን ከካፋ የፈጠረዉ ፈጣሪ እንደመሆኑ ባለቤትነቱን ከወሰደም ፈጣሪ እንጂ ሰዉ አይሞክረዉም!
ካፋ ታሪኩን ለማደስና ለማዕከላዊ መንግስት ተጠሪ ለመሆን እራሱን በራሱ እንጂ ማንንም አይለምንም! መደምርን ወይም መጨፍለቅን በተግባር የምናይበት ጊዜ ላይ ደርሰናል!
…………..ሰላም!……….

ተክለአብ ነኝ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: