
አቶ ባርናባስ ኮምታን በዋና ሰብሳቢ
በትናንትናው ዕለት ቅዳሜ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ሕብረት አባላት በሚዛን ከተማ አጠቃላይ ስብሰባ አድርገው ድርጅቱ ተጠናክሮ በኢትዮጵያ መመስረቱን ይፋ አድርገዋል:: በዚህም መሰረት አቶ ባርናባስ ኮምታን በዋና ሰብሳቢነትና ወ/ሮ ተዋበች ተክሌን ምክትል ሰብሳቢ ወጣት መልካሙ ሸገቶን ፀሐፊ አድርገው መርጠዋል:: ባጠቃላይ 21 የድርጅቱ ማከላዊ ኮሚቴዎች በዚሁ ስብሰባ ተመርጠው ሐላፊነቱን ተረክበዋል:: 6 አባላት ያሉበት የቁጥጥር ኮሚቴም ተዋቅሯል:: የቁጥትር ኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ አቶ ጌታሁን ከበደ አና አቶ ተሰማ ናግ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል::

ወ/ሮ ተዋበች ተክሌን ምክትል ሰብሳቢ
ይህ ክስተት ለካፋ ሸካ ቤንችና ማጅ ሕዝብ ትልቅ ድል ነው:: ሁላችንም እንኳን ለዚህ አበቃን!!! ይህንን እንቅስቃሴ ልዩ የሚያደርገው ድርጅቱ ከ3 ዓመት በፊት በካፋ ሸካና ቤንች ማጂ ልጆት በሴሜን አሜሪካ ተመስርቶ አሁን ሃገር ውስጥ በመግባት ድርጅቱ በአከባቢዊ ተቆርቋሪና ቆራጥ ልጆች መመራቱ ነው::

ወጣት መልካሙ ሸገቶን ፀሐፊ
ይህ አከባቢ የራሱ የሆነ ድርጅት ባለመኖሩ ችግር ብሶት በደሉን ፊት ለፊት ቀርቦ ሕዝቡን ወክሎ የሚናገር ባለመኖሩ ሃብቱና መሬቱ ሲዘረፍ እንዲሁም በልማት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት አከባቢዎች በፍፁም ሗላ ቀርና እጅግ የተበደለ ሆኖ ቆይቷል:: ከአሁን በሗላ እንዲህ ዓይነቱ ግፍ ይህ ድርጅት እያለ በፍፁም ልቀጥል አይችልም:: ለዚሁ አጠቃላይ ስብሰባ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ወደ ላይና ታች በመሯሯጥ አስፈላጊ መረጃዎችን በማሰባሰብና አባላቱን ሁሉ አንድ ላይ በማምጣትና ይህንን ታሪካዊ ስብሰባ በመምራት ከፍተኛ መስዋዕት ለከፈሉልን ለአቶ ጎዲ ባይከዳ ጃሹ በሴሜን አሜሪካ የድርጅቱ የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊና ለአቶ ያሮን ቆጭቶ የድርጅቱ ፀሐፊ ምሥጋናችን ከመጠን በላይ ከፍ ያለ ነው::እነዚህ በአባላቱ የተመረጡት አመራሮች በቅርቡ የስብሰባውን ቃለ ጉባኤና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን አሟልተው በመያዝ በቅርብ ቀናት ውስጥ ወደ ምርጫ ቦርድ በመሄድ ድርጅቱን አስመዝግበው ድርጅቱ በሙሉ መብት በሃገር ውስጥ ማንኛውንም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ እንዲችል ሕጋዊ ፍቃድ ይገኛሉ::
አሁን ጨዋታው ተጀምሯል:: ወደ ሗላ ማለት የማይታሰብ ነው:: ይህ ድርጅት በቅርቡ በምርጫ ተወዳድሮ በሕዝቡ ተመርጦ በሕዝቡ ውክልናን አግኝቶ የአከባቢውን መንግሥት እንደሚመሰርት ምንም ዓይነት ጥርጥር የለንም:: ከአሁን በሗላ የሞግዚት መንግሥት በአከባቢያችን አይኖርም ሊኖርም አይገባም::
ደስታችንን እጥፍ ድርብ የሚያደርገው በዚህ ሳምንት የካፋ ዞን የክልልነት ጥያቄ መጠየቁ ሲሆን የሸካና የቤንች ማጂ ዞኖችም የክልልነት ጥያቄ በማቅረብ በመንግሥት ላይ ከባድ ጫና እንደሚፈጥሩ ይጠበቃል:: እነዚህ ዞኖች በሕገ ደንቡ መሰረት የክልልነት ጥያቄ ካቀረቡ በሗላ ሶስቱም ዞኖች አንድ ላይ በመሆን ሶስቱን ዞኖች ወደ አንድ ክልል የማድረግ ሥራን አጠንክረው እንዲሰሩም በጥብቅ እናሳስባለን:: አንድነት ሃይል ነው:: አንድ ከሆንን የማንፈነቅለው ድንጋይ አይኖርም የማንደርስበት ቦታም አይኖርም:: በድጋሚ ሁላችንንም እንኳን ደስ አለን!!!
እግዚአብሔር ሕዝባችንንና ሃገራችን ኢትዮጵያን ይባርክ::
1. ሀ). “የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ሕብረት ”
ነዉ ወይስ
ለ) “የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ሕብረት” ግድፈት ከሆነ ይታረም
2. ሌላዉ በድርጅት አንድ መሆን በፖለቲካ መሪዎች የሚወሰን በመሆኑ ችግር የለዉም፡፡
3. ሌላዉ ሊታወቅ የሚገበዉ፣ የካፋ ዞን የክልል ጥያቄ ያቀረበዉና በዞን ደረጃ ያፀደቀዉ፣ የራሱን መብትና ጥቅም ለማስከበር እንጂ መንግሥት ላይ ጫና ለማድረግ አይደለም፡፡ ሌሎቹም ሁለቱ ዞኖች የክልል ጥያቄ ማቅረብም ሆነ አለማቅረብ መብታቸዉ ነዉ፡፡
4. ቀጣዩና ቢበዛ ከአንድ ዓመት በሁዋላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በመሆን የፌደራል መንግሥቱ አካል የሚሆነዉን ካፋ እና ሌሎቹን (ዞንም ይሁኑ ክልሎች) በአንድ ክልልነት ማዋቀር ግን አሁንም በህጉ መሰረት፣ በሚመሰረተዉ ምክር ቤት ጥያቄና በሚከተለዉ ህዝብ ዉሳኔ ዉቴት የሚወሰንና የሚፈፀም ነዉ፡፡
5. ክልል፣ ህዝብንና ድርጅቱን በተመለከተ ግን አንድም ሦስትም ሆነዉ፣ ግን ደግሞ ድርጅቱ በአንድነት መታገል፣ መወዳደርና እንደዉጤቱም ማስተዳደር ወይም መደገፍ ይችላል፡፡ ህጉም ሥርዓቱም ይህ ነዉ፡፡
6. በእነዚህ አካባቢዎች ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ድርጅቶች (ኢህአዴግም ሆነ ሌሎች አገር አቀፍ ፓርቲዎች) ) ጭምር ሊወዳደሩ፣ ካሸነፉ ሊመሩ፣ በከፊልም ካሸነፉ በጋራ ማስተዳደር እንደሚችሉ እንዳይረሳ፡፡
LikeLiked by 1 person