Leave a comment

”ካፋና ቡና የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸዉ”፡፡


ውድ የካፋ ልጆች በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ተቃውሟቸውን ለአምባሳደሩ አቀረቡ::

ዛሬ በNovember 21,2018 በዋሽንግተን ዲሲ አከባቢ የሚኖሩ የካፋ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ለተከበሩ አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ካፋ የቡና መገኛ መሆኗ የማይካድ ሃቅ መሆኑን ገልፀው የታሪክ ስርቆትና ዘረፋ በአስቸኳይ እንዲቆም ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል:: ከዚህ በታች የምታዩትንም ደብዳቤ በክቡር አምባሳደሩ በኩል ለሚመለከተው አካላት ሁሉ እንዲደርስ ጠይቀው ደብዳቤውን ለአምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን አስረክበዋል::

ከክቡር አምባሳደሩ ጋር በነበራቸው ውይይት ኢቲቪ የካፋን ሕዝብ ታሪካዊ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይዘግብ በባለሥልጣናት መከልከሉ ከመጠን በላይ ያስቆጣቸው መሆኑን ገልፀው ይህ የሚያመለክተው አንዱ ዘረኛ ቡድን ሲሄድ ሌላኛው ዘረኛ ቡድን በኢቲቪ መሥሪያ ቤት መተካቱ እንዳሳዘናቸው ገልፀው ይህንን ዘረኝነት ከሕዝባቸው ጋር በመሆን እንደሚዋጉ አረጋግጠዋል::
ካፋ ሚድያ kaffamedia

ውድ የካፋ ልጆች በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ተቃውሟቸውን ለአምባሳደሩ አቀረቡ:

ውድ የካፋ ልጆች በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ተቃውሟቸውን ለአምባሳደሩ አቀረቡ:

ቀን : ህዳር 12 , 2011
ለኢትዮጵያ ኤምባሲ
ዋሽንግተን ዲሲ

ጉዳዩ፡- የታሪክ ቅሚያ እንዲቆምልን ስለመጠየቅ ይሆናል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መገለጫ የሆኑ ባህላዊ እሴቶችና ቅርሶች የሚደራጁበት፤ የሚለሙበትና ይበልጥ እየታዋወቁ ጥቅም ላይ የሚዉሉበት ሙዝየሞች በመገንባት እንዲሁም ቅርሶችን በማሰባሰብና በማልማት ከትዉልድ ትዉልድ በማሸጋገር የሕዝብን ተጠቃሚነት እያረጋገጠች ትገኛለች ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በርካታ ቅርሶች በዮኔስኮ የአለም አቀፍ ቅርስነት የተመዘገቡ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ የሀገራችን የማህበራዊና የኢኮኖማዊ የጀርባ አጥንት የሆነዉ ቡና ለመጀመርያ ጊዜ የተገኘዉ በሀገራችን ኢትዮጵያ በደቡብ ክልል በካፋ ዞን በዴቻ ወረዳ በማኪራ ቀበሌ በቡኒ መንድር መሆኑን የተለያዩ መረጃዎች ያረጋግጣሉ፡፡

ነገር ግን ባሳለፍነዉ ሳምንት በምንወዳት በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ሚዲያዎች መከታተል እንደቻልነዉ ያለዉን እዉነታ ያላገናዘበ ፤ ታሪክን ጠንቅቀዉ የማያዉቁ አዋቂነን ባዮች ስለቡና መገኛ ምድር ካፋ መሆኑን ዘንግተዉ የቡና መገኛ ምድር ያልሆነዉን አካባቢ በመጥቀስ የታሪክ ቅሚያ ወይም ነጠቃ በቡናይቱ ምድር በማወጃቸዉ የተነሳ የአካባቢያችን ነዋሪዎች ለተከታታይ 5 ቀናት ሠላማዊ ሠልፍ ከህዳር 1 እስከ 5 2011 ድረስ ማድረጋቸዉን የተለያዩ የመንግስት እና የግል ሚዲያዎች በሰፊዉ ዘግበዋል፡፡

የዚህ የታሪክ ቅሚያ አዋጅ መነሻዉ በቅርቡ የዓለም አቀፍ የቡና ቀን ለመጀመርያ ግዜ በሀገራችን ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቡናና ሻይ ልማት ባለስልጣን መ/ቤት ጋር በመተባበር በዘንድሮ ዓመት የሚከበረዉን ዓለም አቀፍ የቡና ቱርዝም ፕሮግራም ቡና መገኛ በሆነችዉ ካፋ ዞን እንደሚያከብሩ ገልፀዉ ስሰሩ ከመቆየታቸዉም ባሻገር በድህረ ገፃቸዉ ICE Ethiopia is land of origins Ethiopian coffee tour ካፋ ላይ ለመገናኘት መልቀቃቸዉ ይታወቃል ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሳምንት በሃላ የቡናና ሻይ ልማት ባለስልጣን መ/ቤት ሀሳቡን ገልብጦ ጅማ የቡና መገኛ እንገናኝ ብለዉ መልቀቃቸዉን በዚሁ በመደመር ወቅት ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት ሆን ተብሎ ታሪክ ለማጥፋት ወይንም ለመቀማት እንድሁም በህብረተሰብ ዉስጥ ጥርጣሬ ለመፍጠር የተሠራ ሴራ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡

ነገር ግን በአፈ ታርክም ሆነ በጥናት ታግዞ የቀረበዉ የታወቂዉ ካሊዲ( አቶ ካል አዲ) ታርክ መናገር ከጀመረና በመፃሐፍ በትምህርት ከቀረበ አሁን የ1000 አመታት ግዜን ያሳለፍን መሆኑ ይታወቃል፡፡
የካፋ ህዝቦች በተፈጥሮ ጫካ ዉስጥ ጥላን ተመርኩዘዉ ቡናን የማብቀል ዜዴያቸዉ ለረጅም ግዜያት ከሚታዉቁበት እሴቶቻችን አንዱ ነዉ፡፡
እንዲሁም ቡና የሚለዉ ስያሜም ከዝሁ ከቡኒ ምድር የመጣ መሆኑን ቀደምት አባቶቻችን የሚናገሩት እናም በታርክ ተፅፎ እንደሚገኝ የሚታወቃ ሲሆን ኮፊ የሚለዉ የእንግልዘኛ ቃልም ካፋ ከሚለዉ ስም ተያይዞ የተወሰደ እንደመሆኑ የታርክ መዛግብት ይናገራሉ፡፡

በአለማችን ላይ በእጅጉ ጥናት ከተደረገባቸዉ አፅዋት ግንባር ቀደሙ ቡና ሲሆን ሁሉም ጥናቶች በሚያስችል ደረጃ ስለ ቡና መገኛ ምድር የማያሻማ ማስረጃ አቅርበዋል፡፡ የእያንዳንዱ ጥናት መረጃዎች እንደሚያሳዮት ቡና ለመጀመርያ ግዜ የተገኛዉ በኢትዮጵያ በደቡብ ክልል በካፋ ዞን በማኪራ ወረዳ በቡኒ መንድር ነዉ፡፡

የካፋ ዞን ከማንኛዉም ክልል ሆነ ዞን ባልተናነሰ መልኩ በሃገር አቀፍ ደረጃ ከባህር ዳር ቀጥሎ ረጅሙን ባንዲራ በመያዝ የዶ/ር አብይ የመደመር ፅንሰ ሃሳብ ከዳር እስከዳር በመደገፍ ሀገርን ጉድ ያስባለ መሆኑ የቅርብ ግዜ ትዉስታችን ቢሆንም ይህ አይነት የታርክ ቅሚያና ግፍያ ግን የተጀመረዉን የለዉጥ ጎዳና ጥላሸት የሚቀባ እና ለረጅም ግዜ መብቱ ተረግጦ ፤የምጣኔ ሀብቱን ተዘርፎበት እና ማንነቱን ተነጥቆ የኖረዉን ህዝብ በእጅጉ ሊያስቆጣ እንደሚችል ስጋቶችን ከወዲሁ እየገለፅን የካፋና አካባቢዉ ህዝብ ይህን የታሪክ ቅሚያ እንዲቆምላቸዉ የጠየቁት ጥያቄ አግባብ ያለዉና የእኛም ጥያቄ ስለሆነ ለሚመለከተዉ የመንግስት ክፍል የህዝባችን ጥያቄ ላይ የእኛም ጥያቄ ታክሎበት የቡና መገኛ ምድር የሆነችዉ ካፋ ማኪራ መሆኑ ዳግም እንድረጋገጥልን ስንል ጥያቄያችንን እናቀርባለን ፡፡

በተጨማሪም አገራችን በአለም እንድትታወቅ ከሚያደርጉት መገለጫዎች አንዱ የሆነዉን ቡናን ታሪካዊና ልማታዊ ፋይዳዉን የበለጠ ለማጎልበትና ለማስተዋወቅ እንዲቻል በኢትዮጵያ ሚሊንየም ምክር ቤት ዉሳኔ ተሰጥቶበት በካፋ ዞን በቦንጋ ከተማ እንዲገነባ የተወሰነዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ሙዝየም በቀድሞ የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ግርማ ወ/ጊዮርግስ የመሰረት ድንጋይ ሰኔ 21 ቀን 1999 ዓ/ም ተጥሎ በቀድሞ የኢትዮጵያ ፌዲራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚንስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝ አማካኝነት ሚያዚያ 6 2007 የተመረቀዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ሙዝዬም ስራ ሳይጀምር የወፎች መራቢያ መሆን ከጀመረ ዛሬ ላይ ከአራት አመት በላይ ከማስቆጠሩም ባሻገር የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ሙዝዬም በሚንስቴሮች ምክር ቤት ሕጋዊ እዉቅና አግኝቶ እንዲተዳደር በነሐሴ 2009 ዓ/ም ለሚንስቴሮች ምክር ቤት ቀርቦ እስከ አሁን ታፍኖ እልባት አለማግኘቱ ለዚህ ታርካዊ ዝርፋያ/ቅሚያ የዳረገን ስለሆነ በእርሶ በኩል ለሚመለከተዉ የመንግስት መስርያ ቤት ጥያቄያችን ቀርቦ በአፋጣኝ ግዜ ሳይሰጥበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ሙዝዬም ስራ እንድጀምርና የታርክ ቅሚያዉ እንድቆምልን ስንጠይቅ በጎ ምላሹን በእርሶዎ በክቡር አምባሳደር በኩል እንደሚደርሰን በመተማመን ሲሆን እርሶ የሚመሩት ይህ መ/ቤት ይህንን ታሪካዊ ስህተት በማስተካከል እና እዉነታዉን ለዓለም ህብረተሰብ በማስተዋወቅ ሂደት ዉስጥ የራስዎን ሚና እንደሚጫወቱ ተስፋ እያደረግን ለሚያደርጉልን በጎ አድራጎት እና መስርያ ቤቶ ተገኝተን ስሜታችንን እንድንገልፅ እድል ስለሰጡን በእኛ እና በተከበረዉ በጋኪሸረቾ የካፋ ህዝብ ስም ልባዊ ምስጋችንን እናቀርባለን፡፡

➢ ካፋ የቡና መገኛ ምድር ናት፡፡
➢ ታሪክ ይሰራል እንጅ አይሰረቅም፡፡
➢ ካፋና ቡና የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸዉ፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላላም ትኑር !!!

እግዚያብሔር አምላክ ኢትዮጵያና ህዝቦችዋን ይባርክ፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: