Leave a comment

ሰበር ዜና:- እንኳን ደስ ያላችሁ የካፋ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ነዋሪዎች በሙሉ


Asaye Alemayehu

ሰበር ዜና
እንኳን ደስ ያላችሁ የካፋ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ነዋሪዎች በሙሉ
የተከበረው የካፋ ዞን ምክር ቤት ህዳር 6/03/2011 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ለበርካታ ዓመታት ከዞኑ ኅብረተሰብ ስቀርብና ብዙዎች መስዋዕትነት የከፈሉበትን ራስን በራስ የማስተዳደር ወይም ክልል የመሆን ጥያቄን በአጀንዳነት ይዞ ያለምንም ልዩነት በሙሉ ድምፅ ማፅደቁ ይታወቃል::
ሆኖም ይህ ውሳኔ መተላለፉ የእግር እሳት የሆነበት ዴኢህዴን አመራር ላይ ያሉ የካፋ ተወላጆችን እንደለመደው ከማስፈራራት ባለፈ ከድርጅት አቅጣጫ ውጪ ነው የሚል መግለጫ በመስጠቱ በዞኑ ውስጥ ያሉ የድርጅቱ አባላት ሳይቀሩ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ያለፈው ሳምንት ትልቁ ጉዳያችንና ጉዳችንም ነበር:: ወትሮውንም የድርጅት አቅጣጫን ሳይሆን የሚመራበትን የሀገሪቱን ህገ መንግስት ጠንቅቆ የሚያውቅና ጨዋው የካፋ ህዝብ በህገ መንግስቱ መሰረት ያለምንም ሁከት’ንብረት ማውደምና የሰው ህይወት ማጥፋት በፀዳ መልኩ ያስተላለፈውን ውሳኔ በጀግናው የካፋ ዞን ምክር ቤት ም/ል አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ግርማ አማካይነት ክልል ምክር ቤት ዛሬ ገቢ አድርጓል:: ይህን ደብዳቤ መጨረሻ ቦታው ላይ ለማድረስ መፈረም ያለባቸውን ካፋን የወከሉ ክልል ምክር ቤት አባላት ያሉበት ቦታ እንደ ተሿሚ ሳይሆን እንደ ተላላኪ የተሰቃየህ ለስልጣንህ ሳይሆን ለህዝብህ የወገንከው ኩራታችን የሆንከው ልጃችን አቶ ግርማ ሁሌም የካፋ ህዝብ ስያዘክርህ ይኖራልና ክብር ይገባሃል:: ይህ ሁሉ ነገር ብሰራም እጅ አወጥታችሁ ባታፀድቁ የህዝቡ ልፋት ሁሉ ከንቱ ይሆን ነበርና የተከበራችሁ ካፋ ዞን ምክር ቤት ጉባኤ አባላት በሙሉ’በሁሉም ወረዳዎችና በተለያዩ አካባቢዎች የሚትገኙ አካላት በሙሉ’ሁሉም ጉርማሾዎች እና በተላይ በስተመጨረሻ ክልል መግባት ያለበት ቅጽ ላይ ወሳኝ ፊርማችሁን ያሳረፋችሁ አድስ አበባ’አዋሳና ቦንጋ የሚትገኙ አመራሮች ክብር ይገባችኋል:: ያልፈረማችሁ ካላችሁም/ያልፈረመ ይኖራል ብዬ ባልገምትም/ የካፋ ህዝብ አሁንም ይቅር ባይ ነውና በቀጣዙ ሂደትም ተስተካክላችሁ ለህዝቡ እንደምትወግኑ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ::
አሁን ጥያቄው የቀረበው በህገ መንግስቱ መሰረት በመሆኑ ክልሉ የድርጅት አቅጣጫ ምናምን ሳይል የህጎች ሁሉ በላይ የሆነውን ህገመንግስቱን መሰረት በማድረግ የተከበረውን የክልሉን ምክር ቤት አባላት ጉባኤ በመጥራት ጥያቄያችንን በማስወሰን ህዝቤ ውሳኔ እንዲያስፈፅም ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንድፅፍ ሳንታክት መስራት ያስፈልገናል::
ማስጠንቀቂያ:በብቃታችሁ ወይም ባመጣችሁት ለውጥ ሳይሆን በሰንሰለትና በማቃጠር ብቃታችሁ ከቦንጋ ውጪ በሹመትም ይሁን በትምህርት ከሄዳችሁ በኋላ የክልል ጥያቄ ሂደቱን አልጠበቀም እያላችሁ የምታሽቃብጡ ጡት ነካሾች ራሳችሁን አስተካክሉ::
ከመቸውም ጊዜ በላይ አንድ መሆን ያለብን ወቅት አሁን ነውና በተለመደው የይቅር ባይነት የካፋ ባህላችን ይቅር ተባብለን በትንንሽ ነገሮን መነቋቆርን ትተን በመተራረምና በውስጥ በመመካከር ለማንነታችን መስራት ያስፈልገናል የሚል እምነት አለኝ::
አሁን ቦንጋ የክልሉ ርዕሰ ከተማ ስለምትሆን ሁላችንም ተናበን ለክልል ከተማነት የምትመጥን ከተማን ቶሎ መፍጠር ስላለብን ወደ ስራ ፊታችንን ማዞር አለብን

https://www.facebook.com/Diggootuneba?__tn__=%2CdlC-RH-R-R&eid=ARCBMMzGys6NbTvAiUkyrbm2abANh-Fhi7PuqEuxm9oeCXE2SUGwVkzWy_-CzCjLgytvhfno-ek485j5&hc_ref=ARSKIHkPPTkKKe6Rfrbhuzh2QPdUYQsIiSTt_jDRB7JDtLVC87rHubNctIIjevC9Z0w

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: