1 Comment

ለዶ/ር አብይ ጥያቄ አለኝ (By:- meseret mule)


By:- meseret mule

ለዶ/ር አብይ ጥያቄ አለኝ
ከማንኪራ ( ቡኒ መንደር ) እስከ እግዜር ድልድይ (ጉርጉቶ)
አስቤበት አልሄድኩም ፤ በድንገት ጉዞ ወደ ማንኪራ አለ ሲሉኝ ሄድኩ እንጅ ፡፡ እርግጥ ነው ኢትዮጵያዊያን ሁላችንም የቅርብ እሩቆች ነን ፡፡ አካባቢያችንን ከእኛ ይልቅ ሌሎች ጠንቅቀዉ አውቀው የሚነግሩን አይነት ህዝቦች ፡፡
ጠዋት አካባቢ ከ ቦንጋ ከተማ በስተ ደቡብ በኩል ተጓዝን ፡፡ አብዛኛዉ የመንግስት መኪናዎች ናቸው ከሁለቱ ቅጥቅጥ መኪናዎች ውጭ ፡፡ ‘’ኮፊ ኖ ቡኔኔ’’ በሚል ውብ የካፊኛ ሙዚቃ ታጅበን ወደ ማንኪራ ( ቡኒ መንደር ) ተንቀሳቀስን ፡፡ እውነቱን ለመናገር ቦንጋና የቦንጋ ዙሪያን ቀን ማታ ስለምናየው ለምደነው እንጅ መንፈስን የሚይዝ ፣ ቀልብን የሚሰበስብ ፣ ሀሴትን የሚያጭር ፣…በተላይ የተፈጥሮ አድናቂ ለሆነ ሰው የመንፈስ እርካታን የሚያጎናፅፍ ቦታ ስለመሆኑ ምስክር አያሻም ፤ ማየት በቂ በመሆኑ ፡፡ እናም ተፈጥሮን እያደነቅን ጉዞ ወደ ማንኪራ ፡፡
ወደ ማንኪራ በምናደርገው ጉዞ መሃል ገዳም የሚባል ቀበሌ አል ፡፡ የዚህ ቀበሌ ስያሜ በ 1882 ዓ.ም. ከተመሰረተው ባለ 44 መስኮቱ ገዳም መድኃኒያለም ቤተ ክርስቲያን ጋር ተያያዥነት አለው (የኔ ግምት ነው) ፡፡ እርግጥ ይህ ቤተ ክርስቲያን ብቻውን አንድ የቱሪስት መስብ መሆን የሚችል መሆኑን ያየ ይመሰክራል ፡፡
አስፓልቱን ለቀን በስተ ቀኝ ታጥፈን የጠጠር መንገዱን ተያያዝነው ፡፡ ይህ መንገድ የሚያደርሰው እናት ቡና ወዳለችበት ነው ፤ ግን የመንገዱ ሁኔታ እንኳን ወደ እናቷ ቀርቶ ወደ ልጆቿም ለመሄድ የሚመጥን ሆኖ አላገኘሁትምና የዞኑ መንግስት ቢያስብበት ጥሩ ይመስለኛል (በተለይ ድልድዩ)፡፡ ካልሆነ ግን ቦታውን ማየት ለሚፈልጉ ፈታኝ ይሆንና ማየት የፈለገ ሁሉ ምኞቱ ምኞት ብቻ ሆኖ እንዳይቀር እላለሁ ፡፡ ከዚህም ባሻገር ይህን መንገድና ሊሟሉ የሚገባቸውን መሰረተ ልማቶች ያለማሟላት ከልጅ ገንዘብ እየተቀበሉ እናቲቱን መርሳት ይመስለኛል (ኢትዮጵያ በቀዳሚነት ወደ ዉጭ የምትልከውና ዶላር የምታኝበት ቡና መነሻው ከዚህ መሆኑ አይዘንጋ ) ፡፡
መኪና እስከሚገባበት ድረስ በመኪና ከሄድን በኋላ የእግር መንገዱን ተጉዘን እናት ቡናዋ ጋ ደረስን ፡፡ እናቷ ያለችበት ለመድረስ ደኑ ውስጥ 50 ሜ. ያህል መግባት ነበረብን ፡፡ በዚህ ርቀት ውስጥ ግሩም የሆነ የቡና ደን ተመለከትን ፤ ደኑ ያለው ቡና ውስጥ እንጅ ቡናው ደኑ ውስጥ ያለመሆኑን ታዘብን ፡፡ እውነቱን ለመናገር የአካባቢውን ሁኔታ ለመግለፅ ቦታዉ ሂዶ ማየት እንጅ እንዲህ ነው እንደዚያ ነው ብሎ ማስረዳት ይከብዳል ፡፡ ተፈጥሮ ምስክርነት ቆማ ስትናገር ማንኪራ ላይ አይቻለሁ ፡፡
ከማንኪራ መልስ ወደ ኋላ ተመልሰን የእግዜር ድልድይ ን (ጉርጉቶ ) አየነው ፡፡ እዚህ ቦታ ላይ የተሰራ “ የእግዜር ድልድይ” የሚል ቆንጆ ፊልም ተሰርቷልና ያላያችሁ እዩት ፡፡ ተፈጥሮ ጸጥ ባለ ደምፅ በራሷ ቅኔ ምትጮህበት ቦታ ፡፡ ካላይ ትልቅ ክብደት ሊሸከም የሚችል ከስሩ ትልቅ ውኃ የሚያልፋበት ድንቅ ስፍራ የእግዜር ድልድይ ፡፡
ዉሏችንን አጠናቀን ስንመለስ መመለስ ያለባቸው ይያቄዎች ውስጤ ተመላለሱ ፡፡ እናም እንዲመለስልኝ በጥብቅ እሻለሁ ፡፡ ጥያቄዬንም የማቀርበው መልሱንም የምጠብቀዉ ከጠቅላያችን ዶ/ር አብይ ነው ፡፡
ጥያቄ 1 ፡ ዲርዓዝ ብለዉ ብለዉ በብዕር ስም በፃፉት መፃሐፍ ላይ ስለ ከድር ሰተቴ አውርተዉናል ፡፡በ’ኔ እይታ ከድር ሰተቴ ማለት አብዶ ያወቀ ምርጥ የጅማ ሰው መሆኑን በሚገርም አገላለፅ አስረድተውናል ፡፡ እዚሁ በጽሐፍ ገፅ 19 ላይ “…ኢትዮጵያ ለዓለም ገፀ በረከት ያቀረበችው የቡና ፍሬ የመጀመሪያ መገኛ ሥፍራ የሆነዉና ‘ጮጬ’ በሚል ሥያሜ የሚታወቀው ገጠራማ አካባቢ የሚገኘው በዚሁ ዞን ነው…” (ጅማ ለማለት) ይላል ፡፡
እኔ ምጠይቆት …እውነት ይህን ጉዳይ አምነውበት ነው የፃፉት ወይስ የጅማ ሰው ስለሆኑ ? በየትኛዉ ማስረጃዎ ? እንደሚመስለኝ እኔም ሆንኩ ሌሎች ካፋ የቡና መገኛ ነው ተብለን ተማርን እንጅ ጅማ ‘ጮጬ’ የሚል አናውቅም ፡፡ ነው የተሳሳተ ትምህርት ነበር የተማርነው ? ቦንጋ ላይ በብሔራዊ ደረጃ የተቋቋመው የቡና ሙዚየምስ በስህተት ነበር ? ሥራ ያልጀመረው ሙዚየምስ ቀጣይ እጣ ፋንታው ምንድን ነው ?
በዚሁ መጽሐፎ ገፅ 25 ላይ “…እሰከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በመላ አገሪቱ ያለው የተመናመነ የደን ሽፋን አምስት በመቶ መሆኑ በሚገለፅበት ወቅት ከዚያ መሃል 75 በመቶ የሚሆነው የደን ሽፋን በዚህ ዞን (ጅማ) ውስጥ መሆኑ…” ይላል ፡፡ እውነት ዶ/ር ከጅማ ውጭ ስላለዉ ደን በተለይም ካፋ ፣ ሽካ ና ቤንች ማጂ ያለዉን ጥቅጥቅ የተፈጥሮ ደን እረስተውት ነው ወይስ አሁንም ከጅማ ስለተገኙ ለጅማ እያደሉ ነው? እወነትንስ ለመደበቅ ወኜ ከየት አገኙ ?
በመጨረሻ ፡ እኔ የእርሶ እውነተኛ ደጋፊ ነኝ ፡፡ ስደግፎት እንደህዝብ ሆኜ አይደለም ፡፡ ከስሜት ነፃ በሆነ መንገድ ነው እንጅ ፡፡ ስለወደድኮት ፎቶዎን ይዥ አደባባይ የምወጣ ፣ ያልተመችኝ ነገር ሳይቦት ደግሞ ፎቶዎን ለመቅደድ የምሮጥ ሆኜ አይደለም ፡፡ እኔ ስደግፎት የገባኝን አድንቄ ከጎኖ በመሆን ያልገባኝ ሲኖር ደግሞ ልክ እንደዛሬው ማብራሪያ ጠይቄ ነውና እባኮትን መልስ እፈልጋለሁ ፡፡
እርሶም እንደሚሉት ‘ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን እግዚአብሔር ይባርክ’ አሜን !!!

One comment on “ለዶ/ር አብይ ጥያቄ አለኝ (By:- meseret mule)

 1. ደቡብ ምዕራብ ሕዝብ ህብረት (ደምኢሕህ) የሚከተላቸው መሠረታዊ መርሆዎችና ዕሴቶች:-
  ሀ. የግለሰብ ነፃት ፦
  የሰብዓዊና የዲሞክራሲያዊ መብቶችን ያከብራል። ዜጎች ቋንቋቸውን የመጠቀምና የማሳደግ፣ ባህልን የማዳበርና እምነትን፣ ልማድን፣ ሰነስርዓትን ተግባራዊ የማድረግ መብት አላቸው። የቡድን እና የጋራ መብቶችን እንደ የሴቶች፣ የወጣቶች፣ የሙያ ማሕበራትና የመሳሰሉ የስብስብ መብቶችን ያከብራል።
  ለ. ግንኙነቶች:-
  የደቡብ ምዕራብ ሕዝብ ህብረት (ደምኢሕህ) በግለሰቦች መካከል፣ በቡድኖች መካከል፣ በግለሰብና በቡድኖች መካከል ያሉ ግንኙነቶች ተነቃናቂና ተለዋዋጭነታቸውን በመገንዘብ ሚዛናዊና እድገትን አመላካች እንዲሆኑ፣ መብት ከሃላፊነት ጋር መተሳሰር እንዳለበት ያምናል። ታማኝነት፣ ሃቀኝነት፣ ትክክለኝነት፣ ግልጸኝነት፣ ተጠያቂነት፣ ምላሽ ሰጭነት፣ ተቆርቋሪነት፣ መልካም አርአያነት የመሳሰሉ ኃላፊነቶችን መብት ከማስከበር ጋር ትስስርነት እንዳላቸው ይገነዘባል። በተግባር ላይ እንዲውሉም ያለማቋረጥ ጥረት ያደርጋል።
  ሐ. አንድነት በልዩነት:-
  ቋንቋ፤ ሃይማኖትና ባህል የማንኛውም ህብረተሰብ የማንነቱ መገለጫ በመሆኑ፣ ደቡብ ምዕራብ ሕዝብ ህብረት (ደምኢሕህ) እነዚህንና መሰል የማንነት መገለጫዎች ህብረተሰቡ እንዲያሳድግ እና እንዲጠቀም ይታገላል፡፡ አንዱ በሌላው ላይ ተጽዕኖና አድልዎ እንዳያደርግ ይታገላል። ሕብረተሰቡም ጥብቅ በሆነ የአንድነት መሠረት ላይ እንዲቆም ያልተቆጠበ ጥረት ያደርጋል።
  መ. ዴሞክራሲ፡-
  የብዙሃን መንፈስ የተንፅባረቀበት የአስተዳደር ሥርዓት ከሕዝብ፣ በሕዝብ ለሕዝብ የተመረጠ አንደመሆኑ መጠን፣ ማንኛውም ሰው ራሱን በሚነካ ውስኔ ላይ ሃሳብ የመስጠት መበት እንዳለው ደቡብ ምዕራብ ሕዝብ ህብረት (ደምኢሕህ) ያምናል። ግለሰቡ የመምረጥም ሆነ የመመረጥ፣ ሃሣብ የመስጠትና የመተቸት (በመንግስት፣ በሥራ ቦታ፣ በአካባቢና፣ በብሔራዊ ደረጃ) መብቱ የተከበረ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቶ ይታገላል፡፡
  ሠ. አሳታፊነት፣ አሰባሳቢነት:-
  ደቡብ ምዕራብ ሕዝብ ህብረት (ደምኢሕህ) ሕዝቡ በፖለቲካ፣ በምጣኔ ሀብት፣ በማሕበራዊ፣ በዴሞክራሲና በሰብዓዊ ግንዛቤዎች፣ በባለቤትነት መንፈስ ሙሉ ተሳትፎ ያለው ዋነኛ ኃይል መሆን አለበት ብሎ ያምናል።
  ረ. የጋራ ጥቅም :-
  ደቡብ ምዕራብ ሕዝብ ህብረት (ደምኢሕህ) ባንድነት መንፈስ ለጋራ ተጠቃሚነትና የወል እድገት ተቀናጅቶና ተግባብቶ መሥራት አስፈላጊ እንደሆነና ጠቀሜታው የላቀ እንደሆን ያምናል። ለወደፊት ለበሔራዊ ደህንነትና ህልውና ወሳኘነት አንዳለው ስለሚያምን ለተግባራዊነቱ ያልተቆጠበ ጥረት ያደርጋል።
  ሰ. የትግል ስነ ስነርዓት :-
  የግለሰቦችንና የቡድኖችን ተሳትፎ ለማሳደግ፣ ገንቢ ትችቶችን ለመቀበል፣ አሳታፊና አሰባሳቢ ለሆነ ስርዓት፣ ሰላማዊ ትግል ውጤታማ እንዲሆን ደቡብ ምዕራብ ሕዝብ ህብረት (ደምኢሕህ) ያምናል
  ሸ. እኩልነት :-
  ደቡብ ምዕራብ ሕዝብ ህብረት (ደምኢሕህ) አያንዳንዱ ሰው ተፈጥሮዊ አኩልነት ስለአለው በጎሳ፣ በቀለም፣ በትምህርት፣ በሀብት፣ በፆታ፣ በሃይማኖት፣ በአመለካከት ወዘተ ላይ የተመሰረተ አድልዎን አይቀበለውም።
  ቀ. የሕግ የበላይነት :-
  ባለስልጣኖች፣ የመንግስትም ሆነ የግል፣ ሰራተኞች፣ እንዲሁም ማንኛውም ዜጋ በሕግ ፊት እኩልነታቸውን ደቡብ ምዕራብ ሕዝብ ህብረት (ደምኢሕህ) ያምናል። የየትኛውም አካል ይሁን ማንኛውም ግለሰብ ለሕግ የበላይነት ተገዥ ነው።
  እነዚህ እሴቶችና መርሆዎች ከጎሳ ፖለቲካ፣ ከጎጠኛ ፈላጭ ቆራጭነት ሥርዓት ነፃነት በኋላ የሚጠቅሙ ከሶሻል ዲሞክራሲና (የግለሰብ መብት፣ በውድድር ላይ የተመሰረተ የነፃ ገበያ ኤኮኖሚ) ከስምምነት ዲሞክራሲ የተጠናቀሩና ከአገራችን ሁኔታ ጋር የተቀመሩ ናቸው።
  በገጠርና በከተማ በትምህርት፣ በሀብት፣ በኑሮ ሁኔታ ወዘተ ያሉ ልዩነቶችን ለማጥበብ እቅድና ጥረት ያስፈልጋል። አቅሙ ካላቸው ዜጎች የሚሰበሰበውን ታክስና ቀረጥ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በሥራ ላይ በማዋል ኃላፊነትን መወጣት ይቻላል።
  በደቡብ ምዕራብ ሕዝብ ህብረት (ደምኢሕህ) ፓረቲ አምነት የመናገር፣ የመፃፍ፣ ከቦታ ቦታ የመዘዋውር መብት፣ ነፃነት ከተጠበቀ የሕግ የበላይነት ከተከበረ፣ ሕዝቡ በመንግስት ላይ ቁጥጥር የሚያደርግበት ሥርዓት ከተዘረጋ፣ የስልጣን ክፍፍል (ሕግ አውጭ፣ ሕግ ተርጎሚ፣ ሕግ አስፈፃሚ) ሚዛናዊነቱን መቆጣጠር ከተቻለ፤ የግል ሀብት ባለቤትነትና የኤኮኖሚ ነፃነት ከተረጋገጠ፤ ውሃ፣ መብራት፣ የብዙሃን መገናኛ፣ ጤና ጥበቃ፣ ትምህርት፣ ሥራ ለሰው ልጅ አስፈላጊ ነገሮች በመሆናቸው፣ ለተጠቃሚው ዝግጁነታቸው ከተረጋገጠ፣ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች መድረስ ከተቻለ፣ የአገር ድንበርን የሚያስከብር ጠንካራ የመከላከያና ከሕዝቡ ጋር የተስማማ ሰላምና ፀጥታን የሚያስከብር የፖሊስ ኃይል ካለ፤ በችሎታውና በጥረቱ ፈጣን አድገት የሚያሳይ ከራሱ ጋር የታረቀ በአንድነቱ ኮርቶ ደስተኛ የሆነ ህብረተስብ መመስረት አንደሚቻል ደቡብ ምዕራብ ሕዝብ ህብረት (ደምኢሕህ) በጥብቅ ያምናል። ይህንንም ዕውን ለማድረግ ያልተቆጠበ ጥረት ያደርጋል። በዚህ መንገድ የደቡብ ምዕራብ ሕዝብ ህብረት ህልውናውን ያረጋግጣል፡፡
  3. የፖለቲካ መርህ ፦
  የደቡብ ምዕራብ ሕዝብ ህብረት ህዝብ ሁለንተናዊ ማንነት ማስከበር፣ የሌሎችን ህዝቦች ማንነት፣ ባህል፣ እምነትና አስተሳሰብ ማክበር፣ በእኩልነት, ፍትህና መፈቃቅድ ላይ የተመሠረተ ክልላዊና ሃገራዊ የሥልጣንና የሐብት ባለድርሻነትና ተጠቃሚነት እንዲኖር ማድረግ፣ የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከብሩና የመልከዓ-ምድራዊ አሠፋፈርን ታሳቢ ያደረግ የህዝቦች የራስን በራስ ማስተዳደር መብት እንዲከበር መታገል።
  4. የኢኮኖሚና ልማት መርህ ፦
  የደቡብ ምዕራብ ሕዝብ ካለበት ኋዋላ ቀርነትና ድህነት እንዲላቀቅና የኑሮ ሁኔታው እንዲሻሻል ማድረግና ለዚሁም በክልሉ የሚገኙትን ተፈጥሯዊ፣ የሰው ሃይል፣ እውቀትና ሐብት በመጠቀም ፈጣን እድገት እንዲርጋገጥ ማስቻልና ለዚሁም ዓላማና ተግባር ውጤታማነት የክለሉን ተወላጆችና አጋር ወዳጆች በውስጥም በወጭም ሀገራት ማስተባበርና መምራት። እንዲሁም ለብሔራዊ ልማትና የጋራ እድገት ሁለገብ አስተዋጾ ማድረግ።
  5. የማህበራዊ ጉዳይ መርህ ፦
  የደቡብ ምዕራብ ሕዝብ መሠረታዊና ሁለንተናዊ ደህነቱ እንዲጠበቅ ማድረግ፣ በጤናማና ምቹ አካባቢ የመኖር መብቱን በማረጋገጥ፣ የጤና፣ የትምህረት፣ የምግበ፣ የንጹህ ውሀ መጠጥና የመጠለያ ፍላጎቱና አገልግሎቶች እንዲሟሉለት ማድረግ፣ በተመሳሳዩም የስልክ፣ የመንገድ፣ የመብራትና የመገናኛ በዙሃን ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል።
  ከማንም ተጽእኖ ነፃ በሆን መንገድ፣ ህዝቡ በእኩልነት፣ ቋንቋውን፣ ሃይማኖቱንና ባህሉንና ትውፊቶቹን የማጎልበት፣ የፖለቲካ አመለካከቱን ያለተጽእኖ የማራመድ፣ እንዲሁም ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ቅርሶቹን የመንከባከብና የመጠበቅ፣ የማስተዳደር፣ የኪነጥበብ እሴቶቹን የማሳደግ፣ ሳይንስና ቲክኒዮሎጂ ባካባቢው እንዲስፋፋ የማድረግ መብቱ እንዲጠበቅ ማስቻል።
  6. ስባዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ፦
  እንደማንናውም ሰው ሁሉ የደቡብ ምዕራብ ሕዝብ በተፈጥሮው በማንም የማይገሠሥ በህይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነቱ የመከበርና የመጠበቅ ነፃነቱ እንዲረጋገጥለትና በእኩልነት የዜግነት መብቱ ተከብሮለት፣ በፈቀደው ሥፍራ ሠርቶና ሀብት አፍርቶ የመኖርም ሆነ ከቦታ ወደቦታ የመዘዋወር መብቱ እንዲጠበቅለት እና በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል ያለ ምንም ተጽእኖና ባይተዋርነት ፍትሐዊ የህግ ከለላ እንዲኖረው ማስቻል።
  7. የብሔራዊ ደህነትና መከላከያ መርህ፦
  የደቡብ ምዕራብ ሕዝብ ህብረት (ደምኢሕህ) ከሌሎች ደሞክራሳዊ ፓረት ጋሪ ህብረት ፈጥሮ የኢትዮጵያን ሕዝብ የስልጣን ባለቤት ሲያደርግ፡-የሃገሪቱ ብሔራዊ ደህንነትና የመከላከያ ሠራዊት የሁሉንም ህዝብ ተዋጾ ባግባቡ የሚያካትትና ከየትኛውም ዘርና ጎሳ ሆነ ሐይማኖት እንዲሁም የፖልቲካ ወገንተኝነት ፈጽሞ የፀዳ ሆኖ፣ በህዝብ የበላይነት የሚያምንና በህዝብ ይሁንታ ለጸደቀ የሃገሪቱ ህገ-መንግሥት ተገዢ የሆነና በህገ-መንግሥቱ መሠረት ብቻ የሚታዘዝ፣ ለህዝብ ሠላምና ደህንነት፣ ለሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት መከበር እና ለሃገር ሉዓላዊነት ዘብ የሚቆም እንዲሆን አጽኖት ሠጥቶ ይሰራል።
  8. የውጭ ግንኙነት መርህ፡-
  የደቡብ ምዕራብ ሕዝብ ህብረት (ደምኢሕህ) ከሌሎች ደሞክራሳዊ ፓረት ጋሪ ህብረት ፈጥሮ የኢትዮጵያን ሕዝብ የስልጣን ባለቤት ሲያደርግ፡
  ሀ. ከማንኛውም የውጭ መንግሥት ተፅዕኖ ነፃ የሆነ፣ ህዝባዊ አንድነትንና ሃገራዊ ሉዓላዊነትን የሚያከብር፣ የህዝብን ብሔራዊ ጥቅም በቀዳሚነት የሚያስጠብቅ፣ በእኩልነትና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የሚመሠረት መርህና አሠራር ያለው የውጭ ፖሊሲ ይደግፋል።
  ለ. የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ብሔራዊ ጥቅምን እስካልተጋፋና የህዝቧን ጥቅም እስካልተፃረረ ድረስ፣ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ስምምነቶችንና ውሎችን ያከብራል።
  ሐ. የሰው ልጅ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን የማክበር ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን፣ ቻርተሮችንና ስምምነቶችን ያከብራል።
  ሐ. ለዓለም ሠላምና ዲሞክራሲ ከቆሙ አገሮችና ዓለም አቀፍ ተቋሞች ጋር በመተባበር የጋራ ጥቅሞችን የሚያስከበር መርህ ይከተላል።
  መ. በሌላ አገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ባለመግባት፤ የመከባበር፣ የመተሳሰብ፣ የሰላም፣ የትብብርንና የጋራ ዕድገትን የሚያጠናክር እና ችግሮች ሲከሰቱ በሠላም የመፍታት መርህ ይደግፋል።
  ረ.በጋራጥቅምላይ የተመሠረተ የውጪ ንግድ፣ የልማትና ትበበርና ግንኙነቶችንያበረታታል።

  Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: