Leave a comment

ለዶ/ር አብይ ጥያቄ አለኝ (By:- meseret mule)


By:- meseret mule

ለዶ/ር አብይ ጥያቄ አለኝ
ከማንኪራ ( ቡኒ መንደር ) እስከ እግዜር ድልድይ (ጉርጉቶ)
አስቤበት አልሄድኩም ፤ በድንገት ጉዞ ወደ ማንኪራ አለ ሲሉኝ ሄድኩ እንጅ ፡፡ እርግጥ ነው ኢትዮጵያዊያን ሁላችንም የቅርብ እሩቆች ነን ፡፡ አካባቢያችንን ከእኛ ይልቅ ሌሎች ጠንቅቀዉ አውቀው የሚነግሩን አይነት ህዝቦች ፡፡
ጠዋት አካባቢ ከ ቦንጋ ከተማ በስተ ደቡብ በኩል ተጓዝን ፡፡ አብዛኛዉ የመንግስት መኪናዎች ናቸው ከሁለቱ ቅጥቅጥ መኪናዎች ውጭ ፡፡ ‘’ኮፊ ኖ ቡኔኔ’’ በሚል ውብ የካፊኛ ሙዚቃ ታጅበን ወደ ማንኪራ ( ቡኒ መንደር ) ተንቀሳቀስን ፡፡ እውነቱን ለመናገር ቦንጋና የቦንጋ ዙሪያን ቀን ማታ ስለምናየው ለምደነው እንጅ መንፈስን የሚይዝ ፣ ቀልብን የሚሰበስብ ፣ ሀሴትን የሚያጭር ፣…በተላይ የተፈጥሮ አድናቂ ለሆነ ሰው የመንፈስ እርካታን የሚያጎናፅፍ ቦታ ስለመሆኑ ምስክር አያሻም ፤ ማየት በቂ በመሆኑ ፡፡ እናም ተፈጥሮን እያደነቅን ጉዞ ወደ ማንኪራ ፡፡
ወደ ማንኪራ በምናደርገው ጉዞ መሃል ገዳም የሚባል ቀበሌ አል ፡፡ የዚህ ቀበሌ ስያሜ በ 1882 ዓ.ም. ከተመሰረተው ባለ 44 መስኮቱ ገዳም መድኃኒያለም ቤተ ክርስቲያን ጋር ተያያዥነት አለው (የኔ ግምት ነው) ፡፡ እርግጥ ይህ ቤተ ክርስቲያን ብቻውን አንድ የቱሪስት መስብ መሆን የሚችል መሆኑን ያየ ይመሰክራል ፡፡
አስፓልቱን ለቀን በስተ ቀኝ ታጥፈን የጠጠር መንገዱን ተያያዝነው ፡፡ ይህ መንገድ የሚያደርሰው እናት ቡና ወዳለችበት ነው ፤ ግን የመንገዱ ሁኔታ እንኳን ወደ እናቷ ቀርቶ ወደ ልጆቿም ለመሄድ የሚመጥን ሆኖ አላገኘሁትምና የዞኑ መንግስት ቢያስብበት ጥሩ ይመስለኛል (በተለይ ድልድዩ)፡፡ ካልሆነ ግን ቦታውን ማየት ለሚፈልጉ ፈታኝ ይሆንና ማየት የፈለገ ሁሉ ምኞቱ ምኞት ብቻ ሆኖ እንዳይቀር እላለሁ ፡፡ ከዚህም ባሻገር ይህን መንገድና ሊሟሉ የሚገባቸውን መሰረተ ልማቶች ያለማሟላት ከልጅ ገንዘብ እየተቀበሉ እናቲቱን መርሳት ይመስለኛል (ኢትዮጵያ በቀዳሚነት ወደ ዉጭ የምትልከውና ዶላር የምታኝበት ቡና መነሻው ከዚህ መሆኑ አይዘንጋ ) ፡፡
መኪና እስከሚገባበት ድረስ በመኪና ከሄድን በኋላ የእግር መንገዱን ተጉዘን እናት ቡናዋ ጋ ደረስን ፡፡ እናቷ ያለችበት ለመድረስ ደኑ ውስጥ 50 ሜ. ያህል መግባት ነበረብን ፡፡ በዚህ ርቀት ውስጥ ግሩም የሆነ የቡና ደን ተመለከትን ፤ ደኑ ያለው ቡና ውስጥ እንጅ ቡናው ደኑ ውስጥ ያለመሆኑን ታዘብን ፡፡ እውነቱን ለመናገር የአካባቢውን ሁኔታ ለመግለፅ ቦታዉ ሂዶ ማየት እንጅ እንዲህ ነው እንደዚያ ነው ብሎ ማስረዳት ይከብዳል ፡፡ ተፈጥሮ ምስክርነት ቆማ ስትናገር ማንኪራ ላይ አይቻለሁ ፡፡
ከማንኪራ መልስ ወደ ኋላ ተመልሰን የእግዜር ድልድይ ን (ጉርጉቶ ) አየነው ፡፡ እዚህ ቦታ ላይ የተሰራ “ የእግዜር ድልድይ” የሚል ቆንጆ ፊልም ተሰርቷልና ያላያችሁ እዩት ፡፡ ተፈጥሮ ጸጥ ባለ ደምፅ በራሷ ቅኔ ምትጮህበት ቦታ ፡፡ ካላይ ትልቅ ክብደት ሊሸከም የሚችል ከስሩ ትልቅ ውኃ የሚያልፋበት ድንቅ ስፍራ የእግዜር ድልድይ ፡፡
ዉሏችንን አጠናቀን ስንመለስ መመለስ ያለባቸው ይያቄዎች ውስጤ ተመላለሱ ፡፡ እናም እንዲመለስልኝ በጥብቅ እሻለሁ ፡፡ ጥያቄዬንም የማቀርበው መልሱንም የምጠብቀዉ ከጠቅላያችን ዶ/ር አብይ ነው ፡፡
ጥያቄ 1 ፡ ዲርዓዝ ብለዉ ብለዉ በብዕር ስም በፃፉት መፃሐፍ ላይ ስለ ከድር ሰተቴ አውርተዉናል ፡፡በ’ኔ እይታ ከድር ሰተቴ ማለት አብዶ ያወቀ ምርጥ የጅማ ሰው መሆኑን በሚገርም አገላለፅ አስረድተውናል ፡፡ እዚሁ በጽሐፍ ገፅ 19 ላይ “…ኢትዮጵያ ለዓለም ገፀ በረከት ያቀረበችው የቡና ፍሬ የመጀመሪያ መገኛ ሥፍራ የሆነዉና ‘ጮጬ’ በሚል ሥያሜ የሚታወቀው ገጠራማ አካባቢ የሚገኘው በዚሁ ዞን ነው…” (ጅማ ለማለት) ይላል ፡፡
እኔ ምጠይቆት …እውነት ይህን ጉዳይ አምነውበት ነው የፃፉት ወይስ የጅማ ሰው ስለሆኑ ? በየትኛዉ ማስረጃዎ ? እንደሚመስለኝ እኔም ሆንኩ ሌሎች ካፋ የቡና መገኛ ነው ተብለን ተማርን እንጅ ጅማ ‘ጮጬ’ የሚል አናውቅም ፡፡ ነው የተሳሳተ ትምህርት ነበር የተማርነው ? ቦንጋ ላይ በብሔራዊ ደረጃ የተቋቋመው የቡና ሙዚየምስ በስህተት ነበር ? ሥራ ያልጀመረው ሙዚየምስ ቀጣይ እጣ ፋንታው ምንድን ነው ?
በዚሁ መጽሐፎ ገፅ 25 ላይ “…እሰከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በመላ አገሪቱ ያለው የተመናመነ የደን ሽፋን አምስት በመቶ መሆኑ በሚገለፅበት ወቅት ከዚያ መሃል 75 በመቶ የሚሆነው የደን ሽፋን በዚህ ዞን (ጅማ) ውስጥ መሆኑ…” ይላል ፡፡ እውነት ዶ/ር ከጅማ ውጭ ስላለዉ ደን በተለይም ካፋ ፣ ሽካ ና ቤንች ማጂ ያለዉን ጥቅጥቅ የተፈጥሮ ደን እረስተውት ነው ወይስ አሁንም ከጅማ ስለተገኙ ለጅማ እያደሉ ነው? እወነትንስ ለመደበቅ ወኜ ከየት አገኙ ?
በመጨረሻ ፡ እኔ የእርሶ እውነተኛ ደጋፊ ነኝ ፡፡ ስደግፎት እንደህዝብ ሆኜ አይደለም ፡፡ ከስሜት ነፃ በሆነ መንገድ ነው እንጅ ፡፡ ስለወደድኮት ፎቶዎን ይዥ አደባባይ የምወጣ ፣ ያልተመችኝ ነገር ሳይቦት ደግሞ ፎቶዎን ለመቅደድ የምሮጥ ሆኜ አይደለም ፡፡ እኔ ስደግፎት የገባኝን አድንቄ ከጎኖ በመሆን ያልገባኝ ሲኖር ደግሞ ልክ እንደዛሬው ማብራሪያ ጠይቄ ነውና እባኮትን መልስ እፈልጋለሁ ፡፡
እርሶም እንደሚሉት ‘ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን እግዚአብሔር ይባርክ’ አሜን !!!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: