1 Comment

ምነውሳ መነፅሩ ሁሉ “የማንነት” ብቻ ሆነ?


by:- Yaroon Kochito

Yaroon Kochito

Yaroon Kochito

አገራችን ውስጥ አንድ አካባቢ ግጭት በተከሰተ ቁጥር ከዘር ጋር ማገናኘት ቀላልና ብዙ ማሰብና ስራ የማይጠይቅ ትኩረት ማግኛ ዘዴ ከሆነ ውሎ አድሯል። ይህ ደግሞ እንደ አገር አይደለም ሰው እንደተሰኘ ክቡር ፍጡር ወዴት እየወሰደን እንደሆነ ስጋት ውስጥ የሚጥል ነው።
ይህንን ሃሳብ እንድፅፍ ያነሳሳኝ እኔ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ስለማውቀው አካባቢ ኅላፊነት በጎደለው መልኩ በአንዳንድ ሚድያዎች፣ማህበረሰብ ተቋማት አንቀሳቃሾች እና አንድ አንድ ግለሰቦች አማካኝነት እየተነገረ ያለ እውነታን ያልተከተለ ዘገባ ነው።

ዜናውም ከከንባታ አካባቢ ወደ ካፋ ዞን መተው እንዲሰፍሩ የተደረጉ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በማንነታቸው ምክንያት እንዲፈናቀሉ የቱደረጉ አድርጎ የምያሳይ ነው። በነገራችን ላይ ከከንባታ ወደ ካፋ ሲመጡ የተቀበላቸውና አቅፎና ደግፎ ያኖራቸው ከንባታ የቀረው ወገናቸው ሳይሆን የካፋ በተለይ ደግሞ የዴቻ ወረዳ ሕዝብ መሆኑን እዚህ ጋር ልናስተውል ይገባል።
እኔ ወደተረዳሁበት እውነታ ከመሻገሬ በፊት ከትውልድ አገሬ ውጭ መብቴ ተከብሮ እንደሚኖር ዜጋ ብቻ ሳይሆን እንደ ሰው በማንኛውም አካባቢ ለሚፈናቀሉ ፍጡራን-አራዊትም ጭምር- ያለኝን ሃዘን ልገልፅ እወዳለሁ።
ሆኖም የክስተቶችን እውነተኛ መንስኤ ግዜ ወስዶ ለመረዳት መጣር ዘላቂ መፍትሄዎቻቸውንም በጋራ በመፈለግ እንደ አንድ ሕዝብ ወደ ፊት ለመራመድ ያስችለናል የሚል እምነት አለኝ።
ነገሩ ወዲህ ነው:-ከወራቶች በፊት የወገኖቻችን መፈናቀል የተከሰተበት አካባቢ ካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ይባላል። ይህ አካባቢ ደግሞ በደቡብ ምዕራቡ የአገራችን አከባቢ የሚገኝ ዞን ሲሆን በስተደቡብ ምዕራብ ከቤንችና ማጂ ዞን፣ በስተሰሜን ምዕራብ ከሸካ ዞን፣ በስተደቡብ ከደቡብ ኦሞና በስተ ስሜንና ሰሜን ምስራቅ ደግሞ ከጅማ ዞን ጋር ይዋሰናል።
በአካባቢው ከ11 በላይ ብሔሮች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም መሃከል “ሜኒቶች”አንዱ ናቸው። “ጥቃቱም”የተፈፀመው ከወራት በፊት በእነዚሁ ሜኒቶች ነው። ይህ ደግሞ ማንንም እንደ ግለሰብ ወይም ዘር፣ ማህበረሰብ፣ ወዘተ ያነጣጠረ አይደለም፤ በጥላቻ ወይም በበቀል ተነሳሽነት የተደረገም አይደለም፤ ምክንያቱም ” ለሜኒቶች” የኛ የማህበረሰብ ክፍፍል ጉዳያቸው አይደለም፤ እነርሱ የሚፈልጉት ከብት ብቻ ነው።
ሜኒቶች ከብት በማርባት በአጠቃላይ በደቡብ ምዕራቡ የአገራችን አካባቢዎች ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የሚኖሩ ሲሆን ባህላቸውን ከምያውቁት እንደተረዳሁት “ዓለም ላይ ያሉ ከብቶች ሁሉ የእነርሱ ናቸው ብለው የምያምኑ ናቸው። ለጋብቻ ጥሎሽም ብዙ ከብቶች ማቅረብ ስለሚጠበቅባቸው ከብት ወዳለበት አካባቢ ተንቀሳቅሰው ይወስዳሉ፤ሊከላለል የሚመጣ ካለም ይገድላል( ምክንያቱም ከብቶቹ የማንም ይሁኑ የማን ባለሙሉ መብቶቹ እነሱ ናቸውና)።
እንደዚህ አይነት ክስተቶች ደግሞ ለዘመናት የዘለቁና የአካባቢውን ማህበረሰብ ያለ ዘር ልዩነት እየተፈታተነ የሚገኝ ጉዳይ ነው።
ሌላው ሊሰመርበትና ዓዕምሮ ያለው ሁሉ ሊገነዘበው የሚገባ ነገር ቢኖር:- ወገኖች ከከንባታ አካባቢ ወደ ካፋ ሄደው ኑሯቸውን ማድረግ የጀመሩት ገና ትላንት አይደለም። ይልቁንም ለብዙ ዓመታት የዘለቀ እንጂ። ብዙዎች እስከዛሬ በአካባቢው ቤተሰብ መስርተው፣ ሃብት ገንብተው በተለያዩ ተቋማት እንደማንኛውም ነዋሪ ተቀጥረው እየኖሩ ይገኛል፤ ወደ ፊትም ይኖራሉ።
የእነሱ አሰፋፈር “በማንነታቸው ተጠቁ” ፋሽን ከመሆኑ በፊት ዘመናትን የዘለቀ መሆኑን ተረድተን፤ ይልቁንም እየተከሰተ ላለው የጋራ ችግር የጋራ ዘላቂ መፍትሔ መሻቱ እውነተኛ ወገናዊ ስሜት መኖሩን ማሳያ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ።
በዚህ መንፈስ ችግሮችን በጋራ እየተጋፈጡ ከሚገኙ ማህበረሰቦች ውስጥ አንዱን ብቻ ተጎጂ ሌላውን እንደ ጎጂ በማቅረብ ስምን ለማጠልሸት መሞከር የስብዕናችንን ልክ እና ለለውጥ ያለንን የቁርጠኝነት ሚዛን ከማሳየት በዘለለ ምንም አይነት አዎንታዊ ጥቅም እንደማያመጣ ተረድተን በተሻለ ግንዛቤ የተሻለ ስራ እንስራ እላለሁ። የመገናኛ ብዙሃንም ቢሆኑ ከተባራሪ ወሬ በተሻለ መንገድ ቢሰሩ ሃላፊነታቸውን ከመወጣት በላይ የሆነ ተግባር ይከውናሉ የሚል ተስፋ አለኝ።

One comment on “ምነውሳ መነፅሩ ሁሉ “የማንነት” ብቻ ሆነ?

 1. የማንነት ጉዳይ መነሳቱ ነዉር ባይሆንም በጠራ መረጃና በዕዉቀት ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይገባል፡፡

  የማንነት ጉዳይ ፋሽን መሆኑ ብቻ ሳይሆን የሚዲያዎቹን ዘጋቢዎች የሚያሳስባቸዉ ይህ ሌላም ቦታ ይደርሳል የሚል ሥጋት ነዉ፡፡ እዉነታዉ ግን እነርሱ ከሚናገሩት በስተጀርባ የሚያሳስባቸዉ የዘር ጉዳይ የሁሉም ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ አለመሆኑ ነዉ፡፡
  ካፋ ዉስጥ ከንጉሡ ጊዜ ጀምሮ በሰፈራ፣ በንግድና በሌላ ሥራ መጥተዉ ኑሮአቸዉን መሥርተዉ ተደላድለዉ የሚኖሩ የሰሜን ሰዎች፣ ኦሮሞዎች፣ ጉራጌዎች፣ ከምባታዎች፣ ወላይታዎች ወዘተ አሉ፡፡ ብሔር ተኮር ጥቃት ቢኖር ኖሮ ከጎጀብ እስከ ጌሻ፣ ከቦንጋ እስከ መንጅዎ በከታማና በገጠር ተሰግስገዉና ተቀላቅለዉ የሚኖሩ እነዚህ ህዝቦች የትቃት ዒላማ ይሆኑ ነበር፡፡ ይልቁንም በፍትህ፣ በዲሞክራሲ ጉዳይ በቅርቡም በለዉጡ የመጡ ጭላንጭሎች ለማስከበርና ለመጠበቅ ካፋ ዉስጥ በተደረጉ እንቅስቃሴዎች በግንባር ቀደምነት የተሰለፉትን ህዝቦች ብሔር ማጤን ይበቃ ነበር፡፡
  ሚዲያ ላይ ለመናገር ዕድሉን ያገኙትን ግለሰቦች የሙያ ብቃትና የሥነ ምግባር ሁኔታ መቆጣጠር የድርጅታቸዉ ሃላፊነት ቢህንም ቢያንስ ከአሜሪካ ድምፅ ኮርስ ቢወስዱ ጥሩ ይሆናል፡፡ ቴፒ ላይ የብሄር ግጭት ተናሳ ብለዉ የዘገቡ ሁሉ፣ የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ከሁሉም አቅጣጫ ጠይቀዉ ቀረቡትን ቢሰሙ ይማሩበት ነበር፡፡
  የሜኢኒትን ጉዳይ በተመለከተ፣ ይህ የመጀመሪያዉ አይደለም፡፡ እኔ እስከማዉቁ ወቅቱን ጠብቆ በጠሎ፣ በጨታና በዴቻ ወረዳዎች ወደ ጥግ በሰፈሩ የካፋ ህዝቦች ላይ ሲፈፀም የነበረ ክስተት ነዉ፡፡ ሕዝቡም አንዳን የጎበዝ አለቆችን ተማምኖ የሚችለዉን ያክል እየመከተ፣ በአብዛኛዉ ሰዉም እየሞተና፣ ከብት እየተዘረፈ ለዘመናት ኖሯል፡፡ የአሁኑን የሚለየዉ በቅርቡ ወደ ዴቻ የመጡ ሰፋሪዎች በቋንቋ አለምግባባት በጊዜ መሸሽ፣ ወይም ለመከላከል አለመዘጋጀታቸዉ፣ የክልሉ መንግሥት ፖሊስና ልዩ ሃይል የሚባለዉም የሥጋት አካባቢዎችን ከመጠበቅ ይልቅ እንደአለቆቻቸዉ ከተማ ዉስጥ ሲያዉደለድሉ በገጠሩ ያለዉን ህዝብ ግን፣ ችላ ማለታቸዉ ነዉ፡፡ ይህ በማጂ አካባቢ ከደቡብ ሱዳን በሚነሱ ዘራፊዎች በየቀኑ የሚፈፀም ግፍ ነዉ፡፡ ይህም ወ/ሮ ሙፈሪያት በመሩት ስብሰባ ዜጎች እያለቀሱ ያቀረቡት፣ እስካሁን ግን መፍትሔ ያልተሰጠዉ ጉዳይ ነዉ፡፡
  በመሆኑም መንግስት የህዝቡን ደህነትና ፀጥታ እንዲያስጠብቅ፤ ሚዲዎችም ነገሮችን ሳያጣሩ ባይዘባርቁ፣ ቢያንስ የአካባቢዉን መስተዳድር ሳያናግሩ ወደ ተራ ተግባር እንዳይገቡ ማሳሰብ እንወዳለን፡፡
  ከሮ ኬቶ

  Liked by 1 person

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: