2 Comments

ሰሚ ያጣው እና ባለቤት አልባው ህዝብ!!


By: Coffee Kaffa

መንግስት የማያቀው የደቡብ ምዕራብህዝብ!!
ቦንጋ፣ ሚዛን፣ ቴፒ….

– በዚህ ቀጠና እንደትላንቱ ሁሉ ዛሬም፤ በፈጣሪ ዘንድ ክብር ያላት ነብስ ያለርህራሄ በግፍ የረገፈች ነው። በካፋ ዴቻ፣ በቴፒ፣ እና በሌሎችም።
– በሶስቱም ዞኖች ላይ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች፤ ዛሬም እንደትላንቱ ከማያቀንእና ከማይወክለን ደኢህዴን ከሚባል ድርጅት ጋር መሞዳመዱን ቀጥለውበታል።

እነዚህን ሁሉ የህዝቡን ብሶት እና ለቅሶ ወደጎን በመተው፤ የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግስት ተገቢውን መልስ ከመስጠት ይልቅ፤ ቸልታን መርጠው በቁጥር ደረጃ ብዙ ለሆኑ ህዝቦች ብቻ መቆማቸውን ባገኙት መድረክ ላይ ያሳዩን ነው።

ለዚህ ማሳያ ደግሞ ባሳለፍነው ሳምንት፤ ጠቅላይ ሚኒስተራችን በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርበው ከሰጡት መግለጫዎች ይህን ማየት በቂ ነው።
” ‘የደቡብ ክልል’ ዞኖችን የክልል ጥያቄ መመለስ መፍትሔ አይሆንም። ሕገ መንግስታዊ ጥያቄ ቢሆንም መፍትሔ አይደለም። ስለሆነ የወሰንና የአስተዳደር ጉዳዮች ኮሚሽን በሚያቀርበው ጥናት መሰረት መልስ ያገኛል። በጥናቱ ኢትዮጵያ 20 ክልሎች ያስፈልጋታል ከተባለ በዚያ መልክ የሚታይ ይሆናል። ከዚህ ውጭ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ጥያቄ ላቀረቡ 10 ዞኖች መልስ መስጠት አይቻልም።”

በሌላ በኩል ደግሞ በዛሬው እለት የሰላም ሚኒስተሯ የሰጡትን መግለጫ እንይ፤ “ከህብረተሰቡ ጋር በተቀናጀ ተግባር 1 ሚሊየን 20 ሺህ ያህል ዜጎችን ወደ ቀያቸው መመለስ መቻሉን በእምባ የታጀበ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አሁን ቁምነገሩ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው ለምን ተመለሱ አይደለም። እሰይ እንኳን ተመለሱ ጥሩ ተግባር ነው።

ግን የመንግስት ረፓርት የሚቀርበው፤ በጎ ተግባሩን እና ለመመለስ የሚመቻቸውን ብቻ ነው? ይህማ እኮ ድሮ በህወሓት ዘመንም ነበር።

ሰላም በሌለባት አገር የሰላም ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የተቋማቸውን የ6 ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ለህዝብ ተወካች ምክር ቤት ለውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ስያቀርቡ ሶፍት ከእጃቸው አልተለየም ነበር፡፡

ስለዚህ ወገኔ ሆይ፤ ቦንጋ፣ ሚዛን፣ ቴፒ እና አካባቢዋ ያላችሁ፤ ለራሳችን ስንል ከትላንቱ በይበልጥ ልንደራጅ፣ ልንመካከር ይገባል።

Advertisements

2 comments on “ሰሚ ያጣው እና ባለቤት አልባው ህዝብ!!

 1. ሃሳቡ ተገቢና በብዙዎች አዕምሮ የሚጉላላ ጉዳይ ነዉ፡፡ ታዲያ ማን ያደራጅ፤ ማን ያስተባብር?
  በእዚያን ሰሞን እነዚህን ህዝቦች አደራጃለሁ፣ እመራለሁ ያለዉ ድርጅት እንኳን በዚህ ጉዳይ ላይ ለመንግሥትም ሆነ ለሚዲያ ድምፁን አላሰማም፡፡

  አንድ የካፋ ዘፈን ትዝ ይለኛል

  ” ሃኖ ጫኖቾ፣ ጫኖቾ ከሹኤ ገታ ሹቃቻ ከቃየ ጋታ ቃጀነ፤ ሃኖ ኩሮቾ ኩሮቾ ኮ ቢተ ገታ ቢታቻ ኮቃየ ገታ ቃጀነ ዬሮ ሄቺቤ መቀቃ፤ ………. ይቀጥላል” ፡፡
  በላቲን የበለጠ መረዳት ይቻላል፡

  ” Haano Cannoocho Cannoocho Ko’Shuu’e Geta Shuuqqaacha Ko’Qaye Getaa Qajeene, Haano Kuroocho Kuroocho Ko’beete geta biittaach ko;qaye geta Qajeene; Yeroo Hechibee Meqqeeqa…………..”

  Liked by 1 person

  • በርግጥ እውነት ነው፣ ህዝቡ መሪ ይፈልጋል፣ ምሰበስበውን ይፈልጋል፣ ይሁንእንጂ እነሱ ከተባበሩና በጋራ ከተስማሙ ምመራቸውን መፈለግ ቀላል ነው፣ ምክን ያቱም ህዝቡ ሁሉን ነገር ያውቃልና፣
   ዘፈኑን በጣም አውቀዋለሁ፣ ስንቶቹ ይህ ዘፌን ግብቷቸው ራሳቸውን ይጥይቃሉ፣

   Liked by 1 person

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: