Leave a comment

“Majority rule, minority right” የሚባል ነገር አለ፡፡ !!


Menwuyelet Melaku

Menwuyelet Melaku

By: Menwuyelet Melaku

ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያስቸገረው ጉዳይ ቢኖር ሕገወጥነት ፡ አለመደማመጥ፡ የሕግ የበላይነት ያለመከበር፡ ሰብአዊነትን ማጣት የመሳሰሉት ናቸው፡፡
በይበልጥ እየጎዱን ያሉት ያለመደማመጥ /በራስ መንገድ ማድመጥ/ እና የሕግ የበላይነት መታጣት ሲሆኑ እነዚህ ኩነቶች በይበልጥ እየተስተዋሉ የሚገኙት ልሂቃን ተብለው በሚፈረጁና ከተሜ በሆኑት መሆኑ ሁኔታውን እንዲከፋ ያደርጉታል፡፡
ማንኛውም አካል በሰከነና ሕግን በጠበቀ መልኩ ጥያቄዎችን መጠየቅ ይችላል፡፡ ጥያቄዎቹ ተገቢም ይሁን ተገቢ ላይሆኑ ይችላሉ ግን መልስ የሚያገኙት በሀገሪቱ ብሎም በአለም አቀፍ ሕግጋት መሠረት ነውና ምላሹ ምንም ይሁን ምን ሕጋዊ እስከሆነ ድረስ የመቀበል ግዴታ በጠያቂውም ሆነ በሌላው የሚመለከተው አካል ዘንድ ይኖራል፡፡
ምላሾች መቼም ቢሆን ሁለትና ከዛ በላይ የሆኑ አካላትን አስደስተው አያውቁም እንዲያስደስቱም አይጠበቅም፡፡ ሽንፈትን በፀጋ መቀበል ከአንድ የሰለጠነ ማህበረሰብ የሚጠበቅ ይሆናል፡፡
አንድ ሕገወጥ ተግባርን ለመመከት ሌላ ሕገወጥ አካሄድን መጠቀም ማለት ከእጅ አይሻል ዶማነትን ያስከትላል፡፡ ሕገወጥ ተግባር በሕጋዊ አካሄድ ብቻ ነው ሊስተካከል የሚገባው፡፡ የብሽሽቅ ፖለቲካ ለማናችንም አይበጅም፡፡ ለኢትዮጵያ ካሰብን ሰከን ማለት ይበጀናል፡፡
ሌላውና አስቸጋሪው ጉዳይ የሚሆነው መንግስት ሕግን ለማስከበር ያለው ቁርጠኝነት የደከመ መሆኑ ነው፡፡ በተገቢው ቦታና ጊዜ ሕግን ማስከበር የግድ አስፈላጊ ነው ልጅ እንኳን ሲያጠፋ ካልተቀጣ ጥፋቱ ትክክለኛ ተግባር እየመሠለው ደጋግሞ ያጠፋል፡፡ ወይም አንድ የዕግር ኳስ ዳኛ ጥፋቶች ሲፈጠሩ በቃል ተግሳፅ በቢጫና ቀይ የማይቀጣ ከሆነ ከዚህም ከዚያም ወገን ጥፋቶች እየተፈፀሙ ጨዋታው በአግባቡ እንዳይሄድ ያደርጋል፡፡ ይባስ ብሎም የተጨዋቾቹ ተግባር ወደ ደጋፊው ተዛውሮ መላው ስታዲየም ይበጠበጣል፡፡
አንድ መንግስት ዴሞክራሲያዊ የሚያሰኘው የራሱ የሆኑ የተለዩ ባህርያት አሉ፡፡ ሕግን አለማስከበር ግን በፍፁም የዴሞክራሲያዊ መንግስት መገለጫ ሊሆን አይችልም፡፡ አይደለምም፡፡ የምንወስደው እርምጃ በሁሉም ቦታዎችና ጊዜያት ተመሣሣይነት ያላቸውና ወጥ ከሆኑ በፍፁም ለትችት መፍራት የለብንም፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ችግር አንድ ግለሰብ ወደ ስልጣን ሲወጣ ዘሩንም አብሮ ይዞ ስለሚወጣ ነው፡፡ በዚህ ረገድ እስካሁንም ሀገራችንን እየበጠበጡ ያሉት በቁጥር በርከት ያሉ ብሄረሰቦች ናቸው በዋነኛነትም ትግሬ፡ አማራና ኦሮሞ ሲሆኑ እነዚህን ለመቀላቀል እየተንደረደረ ያለው ሲዳማም ለኢትዮጵያ ቀጣይ ስጋት ይሆናል፡፡
አነዚህ ብሄሮች ኢትዮጵያን ተፈራርቀው መርተዋል እየመሩም ነው፡፡ በአንዳቸውም ግዜ ግን ኢትዮጵያ ከድህነት አረንቋ ወጥታ አታቅም፡፡ ይህንን አሳፋሪ ሪከርድ ይዘው የእኔ ዘር ያንተ ዘር ሲሉ ጥቂት አለማፈራቸው በጣም ያሳዝናል፡፡ ሌሎች በቁጥር ያነሱ ብሄረሰቦች ግን ማንም ዞር ብሎ አያያቸውም ድምፃቸውም አይሰማም ነገር ግን በግጭቶች መሀል ሲጎዱ ይስተዋላል፡፡ ወትሮስ የዝሆኖቹ ጥል ጉዳቱ ለሳሩ ነው ይባል የለ?
እስኪ ከተራ መበሻሸቅና የዘር ፖለቲካ ወጥታችሁ ሀገሪቷን ከሌሎች ሀገራት ተርታ አሰልፏት፡፡ ረሀብ ሞት ስደትና መፈናቀልን አስቁሙ የዛኔ ስለእናንተ ዘር ትልቅነት እኛ እንመሠክራለን፡፡
አንድ ነገር ልብ በሉ
ሀገራችንን እግዚአብሔር ይጠብቃት ፡፡ አበቃሁ፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: