Leave a comment

የካፋ ጉርማሾ ፓርቲውን እንድቀላቀል ደምኢህሕ ጥሪ አቀረበ


38023561_282102385890705_1514103197361242112_n

ደምኢህሕ ጥሪውን ያስተላለፈው በቀን 15/07/2011 በሻተራሻ ገሮ አደራሽ ከቦንጋ ነዋሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ነው ።
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ህብረት ከ4አመት በፊት በሀገሬ አሜሪካ ተመስርቶ በቅርቡ መንግስት ባስተላለፈው ጥሪ መሠረት ሀገር ቤት ገብቶ ባለፈው ህዳር ወር ላይ በሚዛን ከተማ የምስረታ ጉባኤ አካሄዷል።
ይህን ተከትሎ ደምኢህሕ በሀገርቱ በምርጫ ቦርድ እውቅና ከተሠጣቸው 107 ለፓርቲዎች አንዱ ሆኗል ።

የደምኢህሕ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዋና አስተባባሪ አቶ በርባናስ ኮምታ በወቅታዊና በተያያዥ ጉዳዮች ለነዋሪዎች ባሠሙት ንግግር የካፋ ጉርማሾ ታሪካዊ ማንነቱንና የአከባቢውን ተጠቃሚነት ለማስከበር እያከናወነ ያለውን ተግባራት ደምኢህሕ ያደንቃል ብለዋል ።
የካፋ ጉርማሾ ከቡና መገኛ ማንነት ጋር ተያይዞ የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ለተከታታይ አምስት ቀን ስካሄድ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ አንዳች ጉዳት ሳያደርስ መጠናቀቁ ምስጥር ከወጣቶቹ አስተዋይነትና ብልህነት የመነጨ ነው ብለዋል ።
በቅርቡ ቴፒ አከባቢ የተፈናቀሉ ወገኖች ጉርማሾ ያደረጉት ሰበአዊ እርዳታን ይህም የጉርማሾ ጥንካሬ መሆኑን ደምኢህሕ ተረድቷል። ።
ለዚህ ሁሉ በድርጅቱ ስም አቶ በርናባስ ምስጋናና አቀርቧል ።
ጉርማሾ ከዚህም በላይ የማድረግ አቅሙም ሆነ ብቃቱ ጉርማሾ እንዳለው ደምኢህሕ ጠንቅቆ ያውቃል ያሉት አስተባባሪው ጉሪማሾ ፓርቲውን እንድደግፉ ጠይቋል ።
ነዋሪውም ሆነ ጉርማሾ ፓሪቲውን ተቀላቅሎ ሠላማዊ ትግል በማድረግ አከባቢውን ተጠቃሚ እንድያደርግ ጥሪ አቅርበዋል ።
የፓርቲው ምክትል አስተባባሪ መምህርት ተዋበች ተክሌ በበኩላችው ፓርቲው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም ብሔረሠቦችን በማቀፍ በኢትያዊነት ላይ ጠንክሮ ይሰራል ብለዋል ።
የሴቶችና የወጣቶች ተሳትፎ የፓርቲው ትኩረት ነው ብለዋል ።
ይንን ለማድረግ ደምኢህሕ በቦንጋ ከተማ ቢሮ ከፍቶ በህጋዊ መንገድ የአባላት ምዝገባ መጀመሩን አስታውቀዋል ።
የአከባቢው ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል ሁሉ ቀርቦ አባል በመሆን ትግሉን መቀላቀል ይችላሉ ብለዋል ።

የፓርቲዉ ማዕከላዊው ኮሚቴ አባል የሆኑት መምህር ክፍሌ መሸሻ ለታዳሚዎቹ እንደገለጹት ደምኢህሕ የይምሰል ወይም የፌክ ኢትዮጽያዊነትን ያወግዛል ብለዋል ።

የአከባቢው ተጠቃሚነት ኢትዮጵያዊነትን የሚቃረን አይደለም ብለዋል ።በፓርቲው ዋና ጸሀፊና የአከባቢው እውቁ የሰብአዊዊ መብት ተማጋች በሚል በብዙዎች የሚሞካሸው ወጣት መልካሙ ሺገቶ የፓርቲዉን የአስካሁን ሂደት ለታዳሚዎቹ አብራርተዋል።

ከታዳሚቹም ማዳበሪያ አስተያየትና ጥያቄዎች ተነስቶ ሰፊ ዉይይት ተደርጎባቸዋል።
ስመ ጥሩዎቹ የጉርማሾ አስተባባሪዎችና ሌሎችም ታዳሚ ነበሩ።
በሀገረ አሜሪካ ለስድስትሆነው ደምኢህህን ከመሰረቱት አንጋፋዋ ወይዘሮ ፋንታዬ ገብሬ ለወጣቶቹ ምክር አዘል የትግል አቅጣጫ አመላክተዋል።
እኛ እዚህ አድርሰናል በቀሪውም ከጎናችሁ ነን ጨዋታዉ በግብ የሚጠናቀቀዉ በእናንተ ብርታት ነው በማለት ወጣቱን አስደምመዋል።
ብዙዎች የወይዘሮዋን መልእክት በቁጭት እንደተረዱት ዘጋቢዎቹ እኝስ ልንገነዘብ ችለናል።
በስተመጨረሻም በአዲስ አበባ የደምኢህህ አስተባባሪ አቶ ታደሰ ተፈራ ለቀጣይ ትግል ጠቃሚ ግብአቶችን ከውይይቱ መገኘቱን አስረድተዋል።
ውይይቱም ባለ አምስት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ባማረ ሁኔታ ተጠናቋል ከስር ይቀርባል።
1. የካፋ ህዝብ ለዘመናት ሲጠይቀው የነበረው ራስን በራስ የማስተዳደር መብት መገለጫ የሆነው ክልል የመሆን ጥያቄ ህገ መንግስታዊ በመሆኑ ያለ ምንም ቅድሜ ሁኔታ ተፈጻሚ እንድሆን እንጠይቃለን ።

2.በተለያዩ የሀገሪቱና በክልሉ እየተካሄደ ያለው መፈናቀልንና ዘርን መሠረት ያደረገ ጥቃት ቆሞ ህግና ስርአት እንድከበርና በተለይ በቴፒና ማሻ ላይ የተፈናቀሉት ወገኖቻችን ልክ እንደ ሌላው ኢትጽያዊያን ሰባዊ ዲጋፍና ትኩረት መንግስት እንድሰጣቸው ደምኢሕህ ጠይቋል ።
3 .እኛ የካፋና አከባቢዋ ህዝቦች ከነግስታት የስልጣን ዘመን ጀምሮ ወደ ጎን በመገፋታችን ከሀገርቱ ኢኮኖሚም ሆነ ፖለትካዊ ተሳትፎ ሳንወከል ሳንጠቀም ዛሬ ድረስ ቆይተናል ።በዚህም ምክንያት በልማት ኃላ ቀርተናል ስለሆነም መንግስት የረጅም ዘመን በደል አድሎና ጭቆናን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንደ ህዝብ የምንጠቀምበትንና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ለማምጣት የሚረዱ እርምጃዎችን በመውስድ እንደ እርምጃዎች በመውሰድ እንደ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ላይ ያለ አንዳች አስተዋጽኦና የሚመዘብሩ እርምጃ እንድወስድና ማስተካከያ እንዲያደርግ እንጠይቃለን።

4.በደቡብ ክልል ከላይ እስከ ታች ድረስ ድረስ ለውጡን የሚመጥኑ ብቃት ያላቸውን አመራሮችን በመመደብ ከተላላኪነት ወደ ተሳታፊነትና በመሻገር ህዝባችንን እንድክስ እንጠይቃለን ።

5.አለም አቀፍ ቅርስ አካል የሆነው አሬንጓደው ወርቅ ቡና መገኛው ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ካፋ ማኪራ መሆኑ በአለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀር በመታመኑ መንግስት ብሔራዊ የቡና ሙዝዬም በቦንጋ ከተማ መገንባቱ ይታወሳል ።ይሁንና በጊዜ ሂደት ስልጣን ላይ የሚወጡ አካላት ይህንን ብሔራዊና አለም አቀፍ የሆነውን እውነት ለማደብዘዝ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ በመሆኑም መንግስት ቡና የተገኘው ካፋ መሆኑን በማስረገጥ ለመገለጫው የተገነባው ሙዝዪም በአስችኳይ ስራ እንድጀምር እንጠይቃለን።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: