Leave a comment

የካፋ አከባቢ ክልልነት ጥያቄ የፋሽን ጉዳይ ወይስ መሰረታዊነት ያለው?


Samuel Tamiru Amade

Samuel Tamiru Amade

Samuel Tamiru Amade

የወቅቱ የክልልነት ጥያቄዎች በተለይም ቀድሞ ደቡብ ተብሎ በሚጠራው የአገራችን አከባቢ መሰረታዊ በሆነ መልኩ በአብዛኛው እየተጠየቀ ያለ ሲሆን ሁሉም አከባቢዎች የየራሳቸው መነሻና ምክንያት እንዳላቸው እውን ነው፡፡ ለነዚህም ጥያቄዎች መንግስት እየሰጠ ያለው ትኩረትና ምላሽ ከህዝቡ ጥያቄ አንፃር ምን ደረጃ ላይ እንዳለና ምን ያህል ህጋዊነትን የተከተለ እንደሆነ ለቀባሪ ማርዳት ነው የሚሆነው፡፡
ከእነዚህ የክልልነት ጥያቄዎች መካከል ዋንኛው ትኩረቴ በካፋ አካባቢ ህዝቦች ክልል የመሆን ጥያቄ ፋይዳዎችንና መሰረታዊ መነሻዎችን ለመዳሰስ ነው፡፡
እንደሚታወቀው በአገራችን ታሪክ ውስጥ በዘመነ መሳፍንትና ከዚያም በመከተል የተፈጠሩ መንግስታት ያሳለፏቸው ታሪኮች ናቸው፡፡ በእነዚህ የታሪክ ዳራዎች በዋናነት አንዲት ኢትዮጵያን ለመመስረት ጥረቶች የተደረጉበትና እያንዳንዱ ንጉስ ለቀጣዩ ተተኪ በኢትዮጵያ አንድነት ዙሪያ የዱላ ቅብብል እያደረጉ የመጡ መሆኑን ያሳያል፡፡ በተለይም ታላቋ ኢትዮጵያን በመመስረት ሂደት የመጨረሻው ንጉስ አፄ ሚኒሊክ 2ኛ እንደሆኑ ታሪክ የሚያስረዳ ሲሆን በዚህ ሂደት ውስጥም መጨረሻ ላይ ታላቋ ኢትዮጵያን የተቀላቀለችው አገር ካፋ እንዲሁም ንግሱ ንጉስ ጪኒቶ ጋሊቶ ነው፡፡ የታሪክ መዛግብትም እንደሚያስረዱት የመጨረሻው የአንዲት ኢትዮጵያ ምስረታ ከፍተኛ የሆነ ትግል የተደረገበትና የኃይል ሚዛን ልዩነት እንዲፈጠር የአድዋን ጦርነት ጨምሮ በርካታ አጋጣሚዎች የተፈጠሩና የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉስ አፄ ሚኒሊክ 2ኛ አቅማቸውን አጠናክረው ካፋን በመውረር በመጨረሻ ታላቋ እትዮጵያን መመስረት ችለዋል፡፡ ከዚህም በላይ የታሪክ አዋቂዎች መጨመር ይችላሉ፡፡
ከክልል ጥያቄዎች አንፃር የካፋ አከባቢ ቀድሞ በዘመነ መሳፍንት ሂደት ውስጥ አገር የነበረና ለዘመናዊው የኢትዮጵያ መንግስት አወቃቀር መነሻ የሚሆን አደረጃጀት የነበረው በመሆኑ፣ ከዚያም በኋላ በነበሩ አደረጃጀቶች (ቅድመ 1987) ጠቅላይ ግዛት፣ ክፍለ ሀገርና ራስ ገዝ በመባል ተጠሪነቱ ለፌደራል መንግስት እንደነበርና ራሱን በራሱ ሲያስተዳድር የነበረ አከባቢ ነበር፡፡ ነገር ግን አቅጣጫን እንጂ ታሪካዊ ዳራን መሰረት ያላደረገው የኢህአዴግ አደረጃጀት ወደ ደቡብ ክልል ፈቃደኝነትንና ታሪክን ሳያገናዝብ መጠርነፉ በረካታ ተግዳሮቶችንና አለመግባባትን መፍጠሩ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ ስለሆነም ዋናው መሪ ህዝብ ነውና የህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
ከታሪካዊ ዳራው በተጨማሪ የካፋ አከባቢ ከመላው የኢትዮጵያ አካባቢዎች በጋራ መኖርንና ማህበራዊ ትስስርን መሰረት አድረገው ለመኖር የሚመጡ ዜጎችን ቤታቸውን፣ ሀብታቸውንና ሌሎች ያሏቸውን ሁሉ በማካፈል አብሮ ለመኖር ዝግጁ የሆኑ ናቸው፡፡ ካፋ ቤት የእግዜር ነው ብሎ በምንም መንገድ ባይተዋርነት እንዳይሰማው በማድረግ የሚያኖር ህዝብ ያለበት ነው፡፡ ህዝቡም ባለው አደረጃጀት የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችንና እንቅስቃሴዎችን ለመጠየቅና ለመተግበር እጅግ ረዥም የሆነ ጉዞና የሀብት ብክነት የሚስከትልባቸው መሆኑ እሙን ነው፡፡ አሁንም የክልልነት ጥያቄው ከማህበራዊ ፋይዳው አንፃር በአከባቢው የሚኖሩ ሁሉም ዜጎች ደግፈውትና አምነው የሚንቀሳቀሱበት በመሆኑ የሁሉም ነዋሪዎች ጥያቄ ነው፡፡
እንደሚታወቀው ከታሪካዊ ዳራ፣ ከማህበራዊ ትስስርና ከፈቃደኝነት ውጭ የተዋቀረው የደቡቡ ክልል ለካፋ አካባቢ ያበረከተው ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦ ማየት ያስፈልጋል፡፡ እንደሚታወቀው የአንድ አከባቢ ኢኮኖሚ ከሚመሰረትባቸው መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል ለከተሞችና ለንግድ ማዕከሎች ያለቸው ቅርበት ተጠቃሽ ነው፡፡ የመንግስት መዋቅራዊ ሀብቶችና እንቅስቃሴዎችም በዋናነት የኢኮኖሚው መዘውር ከሚባሉ አቅሞች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ የደቡቡ ክልል መቀመጫ ከካፋ አከባቢ በከፍተኛ ደረጃ የሚርቅ በመሆኑና ትኩረት በየደረጃው ያልተሰጠው በመሆኑ የአከባቢው ኢኮኖሚ እንዲቀዛቀዝ የራሱ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ስለሆነም አስተዳደራዊው አደረጃጀትን ለነዋሪዎች ቅርብ በማድረግ ኢኮኖሚው እንዲነቃቃ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከትና ጥብቅ ክትትል ማድረግ አለበት፡፡ ነገር ግን ለኢኮኖሚው መነቃቃትና ለልማቱ ትልቅ አስተዋፅኦ የሚኖረው የአከባቢውን ሀብት በተገቢው መጠቀም አለበት፡፡

ታዲያ የካፋ አካባቢ የክልልነት ጥያቄ ምኑ ላይ ነው ፋሽንነቱ? ምኑስ ላይ ነው የሌላውን አካባቢ ጥያቄ መነሻ አድርጎ የተጠየቀው?

ነገር ግን የክልልነት ጥያቄው ከኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ፋይዳው አንፃር የተጠየቀና ለአገራዊው እድገት ከአሁኑ በተሻለ መንገድ ለማበርከት እንዲቻልና እየተስተዋለ ያለውን የሀብት ብክነት በተገቢው ለመቆጣጠር የሚያስችል ነው፡፡ ይህም አገራችን እየተከተለች ያለውን የአንድነት እንቅስቃሴ የሚያጠናክር አደረጃጀት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ካስፈለገም ፖለቲካዊ ዳራውን ማየት ያስፈልጋል!!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: