1 Comment

ደቡብ ምዕራብን ኮማንድ ፖስቱ ተቆጣጥሮታል:: አብን ቢሮ በሚዛን ከተማ ከፍቷል::


Kaffamedia 23622481_136233960477549_6603229457377281274_n

ደቡብ ምዕራብን ኮማንድ ፖስቱ ተቆጣጥሮታል:: አብን ቢሮ በሚዛን ከተማ ከፍቷል::

ምነው ሁሉም የራሱን ማንም አይድረስብኝ ብሎ ሸሽጎና ሰሲቶ የግሉ ካደረገ በሗላ የሚስኪኑን የየዋሁን የካፋን የሸካን የቤንችንና የማጂን አከባቢ እንደ ሥጋ ቅርጫ ለመቀራመት የሚሯሯጠው?

የገረመኝ የመንግሥት በፀጥታ ስም ኮማንድ ፖስት እያለ የክርስትና ስም እየሰጠ ሰላማዊዉን አከባቢ የጦር ቀጠና ይመስል በወታደርና በክላሽ ጋጋታ ውዥምብር መፍጠሩ ነው::

ሲጀመር እስከምናውቀው በአከባቢው የታጠቀ ይሁን የተደራጀ ሃይል እንደሌለ ነው:: ጦርነት ለማወጅ ሆነ ውዥምብር ለመፍጠር ያለመ ወይም የተዘጋጀ ቡድን ሆነ ግለሰብ በአከባቢው እንደሌለ ግልፅ ነው:: እርግጥ ነው በሸካ ዞን በቴፒ ከተማ ዘጠኝ ወር ያስቆጠረ ውንብድና ሕዝብ አፈናቅሏል:: በቤንች ዞን ከሸኮ ወረዳ የሕዝብ መፈናቀል አለ:: ማጂ ላይ ውጥረት ሰፍኖ ይገኛል::

ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው በታጠቀ ሃይል ወይም በአከባቢው ሰላምን ለማደፍረስ ከአከባቢው በተደራጁ ቡድኖች ወይም ግለሰብ አለመሆኑ ግልፅ ነው::

ይህ ሁሉ ውዥምብርና ሁካታ የተፈጠረው በራሱ በመንግሥት ደህንነት አካላትና ከአከባቢው በተሾሙ የካፋ ሸካ ቤንች ማጂ ዞን አስተዳደር ነን በሚሉት የሲዳማ ባለስልጣናት ተላላኪዎች ካልሆነ በስተቀር ማንም ሊያደርገው ሊሞክረውና ሊያስበውም አይችልም:: ተደራጅቶ የሚንቀሳቀስ አካል ካለ በግልፅ ይነገረንና እኛም እንወቅ::

የእነዚህ አከባቢዎች ሁከት በራሱ በመንግሥት ሴራ የተቀናጀ እንጂ በፍፁም በሌላ አካል ሊከወን እንደማይችል ሳይታለም የተፈታ ነው:: የአከባቢው ሕዝብ የዋህ ተንኮልን የማያውቅ ንፁህ ሁሉንም የሚወድና የሚያቅፍ ያለውን በሙሉ ለሌላ ሰጥቶ ባዶ እጁን የሚቀር ገራገር ሕዝብ ነው::

ታዲያ ለእንዲህ ዓይነቱ የዋህ ሕዝብ ኮማንድ ፖስትና የወታደር ጋጋታ ለምን አስፈለገ? ወይስ ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ አሏት ነው ነገሩ? መንግሥት ነኝ ባዩ የሚፈልገውን በግልፅ ተናግሮ ቢለይለት ይሻል ነበር:: ዙሪያ ጥምጥም መሄድ ለምን አስፈለገ ? ምስኪን ማሰብ የማይችሉትን ወጣቶች በማደራጀት የክፋትን ሴራ የሚጠነስስ ከመንግሥት ወይም ከመንግሥት ካድሬና ደህንነት ክፍል ውጭ በዚያ አከባቢ ሁከት መፍጠር የሚችል ብቁ የሆነ አካል ሊኖር አይችልም የለምም:: ይሄ ለሁሉም ግልፅ እንዲሆን ያስፈልጋል::

በዚያ አከባቢ አንድ የታቀደ ሴራ እንዳለ ግልፅ ሆኖ እየታየ ነው:: መንግሥት እውነት ለእነዚህ አከባቢዎች ከልቡ የሚቆረቆር ቢሆን እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሃገራችን አሳቢ ቢሆን ኖሮ ትልቁና ዋንኛው የችግሩ ፈዋሽ መድሃኒት መሆን የሚገባው በሦስቱም ዞን ያሉትን አስተዳዳሪዎችንና ካድሬዎችን ጠራርጎ ሙሉ በሙሉ ማባረርና አከባቢውን ከሲዳማ ባለስልጣናትና ተላላኪዎቻቸው ነፃ ማውጣት መሆን ነበረበት:: ታዲያ ይህን የመሰለ ያፈጠጠ እውነት እያለ አከባቢውን የጦር ቀጠና ማድረግ ምን የሚሉት ብልጣ ብልጥነት ነው?

ለነገሩስ ምን ይደረግ:: ከሞኝ ደጆፍ ሞፈር ይቆረጣል ይሉ የለ:: የአከባቢው ሕዝብ ኢትዮጵያ ሃገሩን ከልቡ ስለሚወድ አረንጏዴ ቢጫ ቀዩን ባንዲራ ይዞ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ ልክ እብድ እንዳባረረው ወደ ላይና ታች መሮጥ እንጂ መች ለራሱ አወቀበት:: ራሱ ሳይጠነክር ሌላኛውን ለማጠንከር በከንቱ የሚባክን ሕዝብ ነው:: ኢትዮጵያ እንድትጠነክር ከፈለክ መጀመሪያ አንተ ራስህ መጠንከር አለብህ:: ያንተ ያለመጠንከርና ደካማ መሆን ሃገሪቱን ኢትዮጵያን ደካና ዝልፍልፍ ያደርጋታል:: ኢትዮጵያ ጠንካራ ሃገር እንድትሆን አንተ መጀመሪያ ጠንክርህ በእግርህ ቁም:: ያኔ ለምትወዳት ሃገርህ የብረት ምሰሶ ሆነት ትታደጋታለህ:: ምስጢሩ ይሄ ነው ካፋ ሸካ ቤንች ማጂ እወቅበት::

አብን ሆይ ከኢህአዴግ; ከሲዳማ ባለስልጣናትና ከተላላኪዎቻቸው የተለኮሰ እሳት በደቡብ ምዕራብ አከባቢ እየነደደ ስለሆነ አብን ነኝ ብለህ መጥተህ እሳቱ ላይ ቤንዚን ከምታርከፈክፍ በጊዜ ውልቅ ብትል ለሁላችንም ይበጃል:: በአከባቢያችን በቂ የሚፋጅ እሳት አለ:: መቼም ሃገርህ ነውና የትም ተንቀሳቅሰህ መስራት እንዳለብህ ብናምንም ጊዜው አሁን አይደለም:: እሳቱን እንደተቆጣጠርን ብቅ ካልክ አንቀየምህም ውዱ አብን ሆይ:: ነገር ግን አንተ አማራን እወክላለሁ ብለህ ነው የተደራጀሄው:: ይህ አከባቢ የካፋ ክፍለሃገር እንጂ የአማራ ክልል አይደለም:: ታዲያ ሚዛን ምን ልትሰራ ነው የመጣሄው:: አማራ ነኝ ካልክ እዚያው በአማራ ክልልህ ጨፍር:: ይልቁንም ከእኛ ጋር ተዋልደው ተጋብተው ለሚኖሩት ከአማራ አከባቢ ለመጡት ኢትዮጵያዊያን ችግር ባትፈጥር ይሻላል:: ምናልባት ወደ አማራ ክልል ልታጏጉዛቸው አውቶቢስ ይዘህ መጥተህ ከሆነ እነሱን ተዋቸው እነሱ እዚህ ከመጠን በላይ ተመችቷቸዋል:: እነሱ ግን አብንን እንፈልጋለን ይምጣልን ብለው ጥሪ አድርገው ከሆነ እሱ ሌላ ጉዳይ ነው::

ቸር ይግጠመን
ካፋ ሚድያ kaffamedia

One comment on “ደቡብ ምዕራብን ኮማንድ ፖስቱ ተቆጣጥሮታል:: አብን ቢሮ በሚዛን ከተማ ከፍቷል::

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: