Leave a comment

ቀጥታ መልዕክት ለካፋ ዞን አስተዳዳሪና ለአስተዳዳሪው ጀሌዎች በሙሉ::


ማንም ሰው በሰውነቱ ክቡር ነው፣ የሰውን ልጅ የማንጓጠጥም ሆነ የማሳነስ አላማም ሆነ ፍላጎትም የለንም፣ ምክንያቱም የሰው ልጅ ያጠፋል ደግሞ ይታረማል። ነገር ግን የሰው ልጅ እየተነገረው እና እየተመከረ መታረምና መስተካከል ካልቻለ ምን ማድረግ ይቻላል? በተለይም ስልጣንን ተገን በማድረግ በህዝብ ላይ እኩይ ተግባርን ሲፈጽሙና  ለዚህች ሃገር በቀናነት እየታገሉና እየሰሩ ባሉት ሰዎች ላይ በሚያደርጉት አላስፈላጊና ኢሰብዓዊ በሆነ ድርጊት ላይ ሲሰማሩ እያየን እንዲሁ በምክር ብቻ ልታለፍ የሚገባ ተግባር አይደለም::

ስለሆነም አሁን በስልጣን ላይ ያለኸው አመራር እያደረክ ያለውን ይህንን እኩይ ትግባር ባስቸኳይ በማቆም ለአካባቢው የሚሰሩትንና የሚቆረቆሩትን ወደ ቦታቸው በመመለስ እና እናንተም የካፋ ህዝብ እንደሚፈልገው መስራት ባለመቻላችሁ ህዝቡን በጭራሽ የማትወክሉና የማትመጥኑ በመሆናችሁ ስልጣናችሁን በገዛ ፍቃዳችሁ በመልቀቅ ለሚሰራ ትውልድ እንድታስረክቡ እንላለን።  እኛ የካፋ ተወላጆች ዱሮም ሆነ አሁንም የሚንፈልገው የማንም የፖለቲካ ድርጅት ማለትም እንደ ኢህአዴግ ያሉ ድርጅቶች መፈንጫ እና የትኛውንም የፖለቲካ ድርጅት መስርቶ ካፋን ህዝብ  እወክላለሁ ብሎ የካፋ ህዝብ ባንዳ ሆኖ የሚሽጥና የካፋን ህዝብ የተፈጥሮ ሃብት አሳልፎ ለዘራፊ ኢንቬስተሮች ነን ባዮች የሚሰጥሳይሆን የካፋህዝብ መብቱ ተከብሮ ሃብቱን ተጠቅሞ ራሱን በራሱ ማስተዳደር የሚያስችል ስርዓት እንዲኖረን ነው።

የካፋ ህዝብ ከንጉሱ ስርዓት ከታቶ ጋኪ ሻሬቾ ዘመን በኋላ እንደ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ቢቀላቀልም በዚያን ጊዜ ከነበሩት የኢትዮጵያ ነገስታት ጀምሮ እስከ አሁኗ ዛሬዋ ላይ ድረስ ምንም ዓይነት ለውጥም ሆነ እድገት ሊያሳይ አልቻለም፣ ጭራሽም እንደ ኢትዮጵያዊ እንኳን ልቆጠር አልቻለም፣ ያሁን ይባስ ብሎ ጭራሽ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ ህዝብ ላይ ወታደራዊ አዋጅ  አውጇል።  የሚገርመው  እና የሚያሳዝነው ነገር በዚህ ጉዳይ ላይ የካፋ ባለስልጣናት መተባበራቸውና ህዝቡን አሳልፈው እንደባንዳ መሸጣቸው ነው ። ለነገሩስ እነሱ ሲጀመር  ምን ጭንቅላት አላቸው:: ለሆዳቸውና ለወንበራቸው ይጭነቁ እንጂ።

ይህ ደግሞ የካፋ ህዝብ በሞራልና በልበሙሉነት ለመብቱና ለነፃነቱ በመታገልና ገዢው ፓርቲ ፍፁም አምባገነን እና የራሱን ስልጣን ብቻ ለማቆየት ስል ህዝባችንን እየረገጠ በመግዛት ላይ ያለ አመራር መሆኑን ስለተረዳ መንግስት ሆን ብሎ የህዝቡን መብት ለመርገጥና ህዝቡን ለማሸበር የህዝቡን ስነልቦና ለመቆጣጠር ያወጀው አዋጅ ነው። እስቲ የኢዮጵያ ህዝብ ይመስክር፣ የትኛው የካፋ ህዝብ ነው መሳሪያ ታጥቆ ህዝቡን ሲጎዳ የነበረው? የትኛው የካፋ ህዝብ ነው ባንክ ሲዘርፍ የነበረው? የትኛው የካፋ ህዝብ ነው አመፅ ሲያስነሳና የህዝቡን ንብረት ሲዘርፍ ሲያወድም የነበረው? ነው ወይስ ገና ለገና የካፋ ህዝብ በጋራ በመደራጀቱና ለመብቱ በመታገሉ ተፈርቶ ነው?

ገዢው አንባገንን መንግስት ሆይ በካፋ ህዝብ ላይ ወታደራዊ አዋጅ ከምታውጅ ለምን የካፋን ህዝብ እውነተኛ ስሜቱን ለመረዳት አትሞክርም፣ ለምንድነው የካፋ ህዝብ ጥያቄ ምንድነው ብለህ ለካፋ ህዝብ ለጥያቄያቸው መልስ ለመስጠት የፈራኸው? አሁንም ቢሆን የካፋ ህዝብ ጥያቄውን ከመጠየቅ ወደኋላ አይልም። የካፋን ህዝብ ጥያቄ ላለመመለስ ተብሎ በህዝቡ ላይ ወታደራዊ አዋጅ ማወጅ ፍፁም ፍትሃዊ አይደለም፣ የካፋ ህዝብ ዱሮም አሁንም ወደፊትም ፍፁም ሰላማዊ ህዝብ ነው። የካፋ ህዝብ ህገመንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ደጋግሞ ጥያቄውን እያቀረበ ነው፣ ለዚህ ጥያቄያቸው መንግስት ትክክለኛውን ምላሽ ሊሰጠው ይገባል እንላለን። የታወጀውን ወታደራዊ አዋጅም ከካፋ ህዝብ ላይ እንድያነሳልን እንጠይቃለን::

ኩሩና ጀግናው የካፋ ህዝብ ሆይ ምንም ያህል ሰው ወዳድና ሰው አክባሪቢ ንሆንም አሁን ግን በጋራና በመደራጀት በመነጋገር የሄንን እኩይ ስርዓት ልናስወግደው ይገባናል:: ህዝባችንንም ከዚህ ከተጋረጠበትና ሊያጠፉን ከመጡት ልንታደጋቸውና በጋራ በመሆን ልንጠብቃቸው ይገባናል።

የካፋ ጉርማሾ አሁን ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በተረጋጋና በበሰለ አካሄድ ወደፊት ይምንሄድበት እና መብታችንን አስከብረን ክልላችንን ይምናስመልስበት ጊዜ ስለሆነ ባስቸኳይ እንድንወያይና በጋራ እንድንመካከር አደራ እላለሁ::

ፍትህና ሰላም ነፃነትና እድገት ለህዝባችን!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: