Leave a comment

በካፋ ሕዝብ ማለትም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አከባቢ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ደባ!!


በካፋ ሕዝብ ማለትም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አከባቢ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ደባ

ሕዝቡን ለማፈን ቀና እንዳይል ራሱን በራሱ እንዳያስተዳድር የመሬቱና የሃብቱ ባሌቤት እንዳይሆን ሁሌም የበይ ተመልካች ሆኖ እንዲኖር ትልቅ የሴራ ድግስ የትዘጋጀለት ይመስላል::

ይህንንም ሴራ እውን ለማድረግ በደንብ ታስቦና ታቅዶ በቴያትር መልክ ቀርቦ የተሳካ ስራ እየተሰራ ይገኛል:: ይህ ሴራ እርምጃውን በደንብ ጠብቆ ከላይ ወደ ታች ድረስ ያለ ምንም እክል ወጤታማ እንዲሆን ዘንድ:-
1. የካፋን ሕዝብ ከካንባታ ለሰፈራ የመጡትን ወገኖች አባሯል በሚል ሰበብ የደቡብ ልሣን በሚባል ጋዜጣ ዘልፎ እርቃኑን ማስቀረትና ባልሰራው ስራና ባላጠፋው ጥፋት ሕዝቡን ወንጅሎ ሞራሉን መግደል
2. የተደራጀና የታጠቀ ሃይል እንዲያውም ፀረ ሰላም ሆኖ አንድ ጠጠር የሚወረውር ድርጅት ወይም ግለሰብ በሌለበት አከባቢ የመከላከያ ሰራዊት ጋብዞ በሕዝቡ ላይ ፍርሃት በመልቀቅና የመከላከያውን ጋጋታ በመጠቀም አስፈራርቶ የሕዝቡን ድምፅ ለማፈን በአከባቢው አለአስፈላጊ ኮማንድ ፖስት ማቋቋም:: የእውነት እንነጋገር ከተባለ ማነው ካፋ አከባቢ ሁከት ፈጣሪ? ካለኢህአዴግ በስተቀር እኛ እስከምናውቀው የታጠቀ ወይም የአከባቢውን ሰላም ለማደፍረስ የተደራጀ አካል እንደሌለ ግልፅ ነው:: በአከባቢው በተለይም በሸካ ዞን በቴፒ ከተማ ዘጠኝ ወር ያስቆጠረ ብጥብጥ መፈናቀልና ሞት እስካሁን ድረስ እልባት አላገኘም:: በዚህም ብጥብጥ አብዛኛዎቹ ሰለባ የሆኑት በዘራቸው አንድ የሆኑ አንድ ቋንቋ የሚናገሩ አንድ ዓይነት ባህል ያላቸው የአንድ እናትና አባት ልጆች የሆኑት የካፋና የሸኮ ብሔረሰቦች ናቸው:: እንዲሁም በቤንች ዞን በሸኮ ወረዳም ብጥብጥና የዘጎች መፈናቀል ተከስቷል:: ይህን ሁሉ ሁከትና ብጥብጥ ሊያቅድ ሊያስፈፅም ወይም ሊተገብር የሚችል ሃይል በአከባቢው ከኢህአደግ በስተቀር በጭራሽ የለም:: ግፈኛውም ተንኮለኛውም ሕዝብን ከሕዝብ የሚያፋጅ ሃይል ከኢህአዴግ በስተቀር ከየትም ሊመጣ አይችልም:: ራሱ ኢህአዴግ ብቻ ነው በአከባቢው ካድሬውንና የደህንነት ክፍሉን ተጠቅሞ እንዲህ ዓይነቱን የእርስ በእርስ ብጥብጥና ሁከት መፍጠር የሚችለው:: ሌላ ሃይል ካለ መንግሥት በይፋ ለሕዝቡ ማሳወቅ ግዴታው ነው:: ስለዚህ ለደረሰው ሞት መፈናቀልና የንብረት መውደም ሁሉ ከኢህአደግ ሌላ ተጠያቂ አካል ሊኖር አይችልም:: ኢህአዴግ ይህ ቁማሩ ትክክል እዳልሆነ ተገንዝቦ በአከባቢው ባሉት ባለስልጣናት ላይ መዝመት ሲግባው ኮማንድ ፖስት በማቋቋም በወታደርና በክላሽ ጋጋታ ሰላማዊዉን ሕዝብ ማስፈራራቱና ውዥንብር መፍጠሩ በፍፁም ተገቢ አይደለም:: በደቡብ ምዕራብ አከባቢ ከኢህአደዴግ በስተቀር የተደራጀ የሕዝብን ሰላም ማወክ የሚችል ድርጅት ወይም የታጠቀ ሃይል የለም::
3. የኮማንድ ፖስቱን መኖር ተጠቅሞ በሕዝብ አመኔታን እያገኙ የመጡትን ለሕዝብ ከሕዝቡ ጋር ተባብሮ ለመስራት እየተሯሯጡ ያሉትን የቦንጋ ከተማን ከንቲባና መሰሎቹን ቶሎ ከቦታቸው አስነስቶ ሕዝቡን ለባርነትና ለውድቀት ለመሸጥ ዝግጁየሆኑትን ለሆዳቸው ያደሩትን ግለሰቦች መሾም ናቸው::

እነዚህ ከላ የተጠቀሱት ሁሉ በትክክል ተተግብረው እውን ሆነዋል::

በነገራችን ላይ የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለፁት ከንቲባው የተባረሩበት ምክንያት ከከተማው ሕዝብ ጎን መቆማቸው ከቦንጋ ዩንቨርሲቲ ተባብረው መስራታቸውና ዩንቨርሲቲው ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ማቅረባቸው ከባንጋ ከተማ ጉርማሾ ጋር አብረው ተደጋግፈው በመስራታቸው እና ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ የስብሰባ አደራሽ በመፍቀዳቸው ነው::

እንደምታወቅው የቦንጋ ጉርማሾና የቦንጋ ዩንቨርሲቲ ለሃገራቸውና ለሕዝባቸው ካላቸው ትልቅ ክብርና ፍቅር ተነስተው መንግስት ለማድረግ ያልቻለውን እና ያልደፈረውን ድንቅ ስራ በመስራት ለአከባቢው ሕዝብ እድገትና ልማት ትልቅ የተስፍ ጮራ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ: አሁን ግን ህዝቡ ጥንቃቄ መውሰድ የሚገባው ከከንቲባው ቀጥሎ ማን ሰለባ ይሆናል ነው? ስለዚህ ከዚህ በሗላ ክንዳቸውን በጉርማሾና በዩንቨርሲቲው መሰንዘራቸው የማይቀር ነው:: በተለይ የቦንጋ ዩንቨርሲቲ ምንም እንኳ ከተቋቋመ ገና አንድ ዓመት ቢሆንም ነባር ዩንቨርሲቲዎች በረዥም ዓመታት መስራት ያልቻሉትን ድንቅ የሆኑ ስራዎችን በመስራት የካፋ ሕዝብ ኩራት በመሆን እያግለገለ ነው:: እነዚህን ተቋማትንና ሰራተኞቻቸውን እንደ ዓይን ብሌናችን የመጠበቅና የማሳደግ ግዴታ የሁላችንም መሆን አለበት:: የአከባቢው ባለስልጣናት ስራቸው ሕዝባቸውን መሸጥና የግል ጥቅማቸንና ኪሳቸውን ማደለብ ነው:: አከባቢው ለሕዝቡ ተቆርቋሪና በእውቀት ተመስርቶ ሕዝቡን መምራት የሚችል አንድም መሪ በኢህአዴግ ድርጅት ውስጥ የለውም:: ያሉት ባለስልጣናት ለእርካሽ ክብርና ለሆዳቸው ያደሩ ለሕዝቡ ቅንጣት ታክል ስሜትና ተቆርቋሪነት የሌላቸው ሕዝባቸውን የሁሉ የበታች ሆኖ እንዲኖር ሕዝቡን ወደ ጨለማ የሚመሩ ናቸው::

በደቡብ ምዕራብ አከባቢ አንድ የታቀደ ሴራ እንዳለ ግልፅ ሆኖ እየታየ ነው:: መንግሥት እውነት ለእነዚህ አከባቢዎች ከልቡ የሚቆረቆር ከሆነ እርምጃው መሆን ያለበት በሦስቱም ዞን ያሉትን ለውጡን ያልተቀበሉትንና ለውጡን ለማደናቀፍ የሚያሴሩትን አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎችን ጠራርጎ ሙሉ በሙሉ ማባረርና አከባቢውን ነፃ ማውጣት ነው:: ታዲያ ይህን የመሰለ ያፈጠጠ እውነት እያለ አከባቢውን የጦር ቀጠና ይመስል በኮማንድ ፖስት ሕዝቡን ማስፈራራት ምን የሚሉት ብልጣ ብልጥነት ነው?

መንግስት በተለይም የደቡብ መንግስት ሕዝቡን ከመጠን በላይ ንቋል:: የንቀቱም ብዛት በአከባቢው ምንም ሰው እንደሌለ በአከባቢው ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ የአከባቢውን ተወላጅ ባንዳዎችን በመጠቀም በማን አለብኝነት እየፈነጨ ነው:: ለነገሩስ ምን ይደረግ:: ከሞኝ ደጆፍ ሞፈር ይቆረጣል ይሉ የለ:: የአከባቢው ሕዝብ ኢትዮጵያ ሃገሩን ከልቡ ስለሚወድ አረንጏዴ ቢጫ ቀዩን ባንዲራ ይዞ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ ልክ እብድ እንዳባረረው ወደ ላይና ታች መሮጥ እንጂ መች ለራሱ አወቀበት:: ራሱ ሳይጠነክር ሌላኛውን ለማጠንከር በከንቱ የሚባክን ሕዝብ ነው:: ኢትዮጵያ እንድትጠነክር ከፈለክ መጀመሪያ አንተ ራስህ መጠንከር አለብህ:: ያንተ ያለመጠንከርና ደካማ መሆን ሃገሪቱን ኢትዮጵያን ደካማና ዝልፍልፍ ያደርጋታል:: ኢትዮጵያ ጠንካራ ሃገር እንድትሆን አንተ መጀመሪያ ጠንክርህ በእግርህ ቁም:: ያኔ ለምትወዳት ሃገርህ የብረት ምሰሶ ሆነህ ትታደጋታለህ:: ምስጢሩ ይሄ ነው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ካፋ ሸካ ቤንች ማጂ እወቅበት::

ካፋ ሚድያ kaffamedia

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: