Leave a comment

2ኛው ብሔራዊ የቡና ሳይንስ ማህበር ኮንፈረንስ/ECSS/ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ቦንጋ – ዩኒቨርሲቲ፤


60900436_2081133198859800_7605401274552418304_n61003257_2081133292193124_8516075839001985024_n

ቦንጋ – ዩኒቨርሲቲ፤
በማህበረሰብ አገልግሎት – ከፋ -ኢትዮጵያ፤

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕ/ት ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ ዩኒቨርሲቲው ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ የማህበረሰብ አገልግሎቶችን ለአከባቢው ህዝብ እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸው የአከባቢው ዋነኛ የገቢ ምንጭ እና መተዳደሪያ በሆነው በቡና ምርት የአከባቢውን ተሞክሮ ለሌሎች አከባቢዎች ለማካፈል፣ የሌሎች አከባቢዎችን ተሞክሮዎች በምሁራን ወደ አከባቢው ለመቅዳት በማሰብ 2ኛው የኢትዮጵያ ቡና ሳይንስ ማህበር ኮንፈረንስ የኢትዮጵያና የውጭ አገር ተመራማሪዎች እና እንግዶች በተገኙበት የቡና መገኛ በሆነው ከፋ ዞን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ መካሄዱን ተናግረዋል፡፡ ኮንፈረንሱ ከግንቦት 16-17/2019 እየተካሄደ ይገኛል፡፡
******************************

የቡና ምርት በዓለም ደረጃ፤
ከ70 በላይ የአለም ሀገራት ቡናን የሚያመርቱ ሲሆን ኢትዮጵያ ከብራዚል፣ ቬትናም፣ ኮሎምቢያ፣ ኢንዶኔዢያ ቀጥላ ከአለም በቡና አምራችነት በ5ኛ ደረጃ ከአፍሪካ ደግሞ በአንደኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ የቡና ምርት የትሮፕካል ተክል ሲሆን በሁለቱ ትሮፒኮች በካንሰርና ከፒርኮርን መካከል ያለው አየር ሁኔታ እንደሚስማማው ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡በአገራችን ኢትዮጵያም በተለያዩ አከባቢዎች በብዛትና በጥራት ይመረታል፡፡
******************************
ቡና ከነዳጅ ቀጥሎ የአለማችን የውጭ ንግድ ምንዛሪ ሲያስገኝ ኮፊ አረቢካ 70%ቱን ይሸፍናል፡፡
******************************

ከፋ ዞን፣ ኮፊ እና ከፋ፤
የከፋ ዞን ዋና ከተማ – ቦንጋ – በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከመዲናችን አዲስ አበባ በ457 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ከፋ ዞን ከቡና መገኛነት አልፎ በተለያዩ የተፈጥሮ ሀብት ውጤቶች በማር፣ በቅቤ፣ በቅመማ ቅመም፣ በሻይ ተክል እና በተፈጥሮ ደን ይታወቃል፡፡ ዞኑ ከባህር ጠለል በላይ ከ500- 3000 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ፣ ከ18- 21°c አማካይ የአየር ሙቀት ያለው እና ዓመቱን ሙሉ ዝናብ የማያቋርጥ በመሆኑ አካባቢው አረንጓዴ ሲሆን የተለያየ ርዝመት ያላቸው ዛፎችና(Layered trees) ጥቅጥቅ፡ ባለ ደን ተውቦ እናገኘዋለን፡፡Evergreen plants/ ሁሌ ለምለም ከሚባሉት ተክሎች ቡና አንዱ ነው፡፡ ጎጀብ፣ ወሺ፣ ባሮ እና ቤኮ የሚባሉ የኦሞ ገባር ወንዞች በዞኑ ይገኛሉ፡፡
******************************
በዞኑ 12 ወረዳዎችና 2 የከተማ አስተዳደሮች ያሉ ሲሆን ከፋ፣ ጫራ እና ናዖ ብሔረሰቦች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻቸው ጋር ለዘመናት ተከባብረው እየኖሩ ይገኛሉ፡፡ ከጠቅላላው 10,602 የዞኑ ቆዳ ስፋት 294,181 ሄክታር መሬት በቡና ተክል መሸፈኑንና የቡናን ውጤታማነት በማጉላት በ2ኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አሁን ካለበት ደረጃ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እንዲያስገኝ በብሔራዊ ደረጃ ጭምር እየተሰራ የሚገኝ መሆኑን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ማስረሻ በላቸው ኮንፈረንሱን በከፈቱበት ወቅት ገልጸዋል፡፡እንደ አቶ በላቸው ገለጻ በዕቅዱ መሠረት ከቡና በሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ኢትዮጵያ ከብራዚል ቀጥሎ ከዓለም 2ኛ አገር ያደርጋታል፡፡
***************************
የከፋ ዞን በEcology በተፈጥሮ የታደለ አከባቢ ነው፡ ይህንን የተፈጥሮ ሚዛን ለቡና በሚደረገው እንክብካቤ የዞኑ ማህበረሰብ ለህጽዋት እና እንስሳት ጭምር ጥቅሙን ጠንቅቆ ያውቀዋል ያሉት የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ ይህንን የካበተውን የአከባቢው ማህበረሰብ ግንዛቤ በትክክለኛ ሳይንሳዊ ጥናት በመደገፍ ቡናን ለማህበራዊና ለኢኮኖሚያዊ ግብዓት በላቀ ደረጃ መጠቀም እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡ ይህንን ለማረጋገጥ ደግሞ ለዚህ ዓላማ የተቋቋመው የቡና ሳይንስ ማህበር ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚያሳካ ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
*****************************

60973260_2081134002193053_8630253352678064128_nየቡና ሳይንስ ማህበር 2ኛው ኮንፈረንስ፤
የዘመኑ ከባድ ፈተና የሆነው የአየር ንብረት ለውጥ ቡና ላይ ከሚያደርሰው ተጽዕኖ ጀምሮ የተለያዩ ችግሮችን በመቅረፍ በዋናነት የቡና ውጤታማነት ማሳደግ ላይ ለመሥራት የኢትዮጵያ ቡና ሳይንስ ማህበር ከሁለት ዓመት በፊት ተቋቁሞ በጅማ ከተማ የመጀመሪያ ኮንፈረንስ በማካሄድ በኮንፈረንሱ ምሁራን የተለያዩ ጥናቶች መቅረባቸው ይታወሳል፡፡የቡናን ምርት መገበያየት በዞኑ እና በሌሎች አከባቢዎችም ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑን ጥናት አመላክቷል፡፡

*****************************
ማህበሩ ዘንድሮ ለ2ኛ ጊዜ የቡና መገኛ በሆነው ከፋ ዞን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከ16-17/ 2011 ዓ.ም “Coffee Science and Innovation for Climate Resilience and Sustainalbe Coffee Value Chain in Ethiopia” በሚል ርዕስ ኮንፈረንሱ /ECSS/ እያካሄደ ይገኛል፡፡ ኮንፈረንሱን የ Bonga University, European Union, STARBACKS and the Institute of Ethiopian Studies በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን በኮንፈረንሱ ተመራማሪዎችና ምሁራን ጥናቶች የሚያቀርቡበት፣ የከፋ ዞን ቡና ምርት ውጤታማነት ተሞክሮ ለሌሎች አካባቢዎች የሚስፋፋበት እንደሆነ፤ ለዩኒቨርሲቲ ምሁራን እና ተማሪዎች በማህበረሰብ አገልግሎትና በምርምር ስራ መነቃቃትን እንደሚፈጥር ዶ/ር ጴጥሮስ አክለው ገልጸዋል፡፡
*****************************
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ፕ/ር ሀሰን ሰይድ
በቡና ታሪካዊ አመጣጥ ዙሪያ ባቀረቡት ጥናት ወቅት እስካሁን ከኢትዮጵያ ውጭ የቡናን መገኛ የባለቤትነት ጥያቄ ያቀረበ አገር እንደሌላ፤ የቡና መገኛ ኢትዮጵያ ምድር ከፋ መሆኑን ከብዙ የታሪክ ድርሳናት አጣቅሰው አቅርበዋል፡፡ለዚህም እ.አ.አ. በ2016 ብሔራዊ የቡና ሙዚየም በከፋ ዞን ቦንጋ ከተማ መገንባቱን እና ለቡና የተገነባው ሙዚየም ቡና በሁሉም ኢትዮጵያውያን ቤት እንደሚጠጣ ሁሉ ሙዚየሙ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ቅርስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
*****************************
በቡና ምርምር የካበተ ልምድ ያላቸው አቶ ይልማ የማነብርሃን በሁለቱም፣ በመስክ ሥራዎች እና በሳይንሳዊ ጥናቶች የቡናን ውጤታማነት የሚፈታተኑትን እንደ pest/ተባይ፣ disease/የቡና በሽታ እና Climate Change/የአየር ንብረት ለውጥ፣ የፀረ-ተባይ መዲሃኒት አጠቃቀም ያሉ ችግሮች ላይ መሥራት እንደሚገባ ባቀረቡት ጥናት አሳስበዋል፡፡
*****************************
ከ250 በላይ የማህበሩ አባላት፣ ተመራማሪዎች፣ ከፌዴራል፣ ከክልልና ከዞን የተውጣጡ እንግዶች፣ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ አመራሮችና ተማሪዎችበኮንፈረንሱ ተሳትፈዋል፡፡

60991686_2081134042193049_5149253449568747520_nማጠቃለያ፤
በአጠቃላይ በሚቀርቡ ጥናቶች ዙሪያ የቡድን ውይይት እየተደረገ ይገኛል፣ የቡና መገኛ በሆነችው መንደር – በማኪራ – ብሔራዊ የቡና ሙዚየም ያረፈበት እና ተመሳሳይ የመስክ ጉብችት እንደሚካሄድ እና የቀጣይ ኮንፈረንስ አቅጣጫ እንደሚቀርብ የኮንፈረንሱ አዘጋጅ ኮሚቴ መርሀ-ግብር ያመለክታል፡፡
ሠላም
*****************************

Ministry of Science and Higher Education – Ethiopia

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: