Leave a comment

በካፋ አከባቢ ያለው ደምኢህህ የፖለቲካ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር መዋሄድ ምን ማለት ነው?


38023561_282102385890705_1514103197361242112_nKaffamedia Kaffamedia

ደምኢህህ ፓርቲ

በካፋ አከባቢ ያለው ደምኢህህ የፖለቲካ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር መዋሄድ ምን ማለት ነው?

የአንድ ሃገር ህዝብ ጥንካሬና መሰረቱ በኤኮኖሚና በፖለቲካ የመሳተፍ አቅሙ ነው:: በካፋ ወይም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አከባቢ የሕዝቡ የኤኮኖሚ ሆነ የፖለቲካ ተሳትፎ በጭራሽ እንዳይኖር የተደረገና መድረሻው እንደማይታወቅ ሰማይ የራቀ ነው:: ይህም የሆነበት በጣም ብዙ ምክንያቶች አሉ ዛሬ ግን ስለሱ አናወራም::

ብዙ የካፋ አከባቢ ሰዎች መች ነው ደምኢህህ ከሌላ ፓርቲ ጋር የሚዋሄደው? ለምን ከሌሎች ጋር እትዋሃዱም? እያሉ ሌት ተቀን ይጠይቃሉ ይጨቀጭቃሉ:: ይህም ደምኢህህ ለምን እንደተመሰረተ ካለማወቅ የተነሳ ነው:: በርግጥ ጠያቂዎቹ ሆኑ ጨቅጫቂዎቹ በጣም ትክክል ናቸው:: ምንያትም በትላንቱ ወያኔ ወይም በዛሬው ኦዴፓ ሚድያዎች ማለቲም እንደ ኢቢሲ ዋልታና ፋና የሚራገቡት ወሬዎች የሕዝባችንን ሰላም ይነሳሉ:: የእኛ ሕዝብ እኛ ከማን ጋር ነው የቆምነው ብሎ እንዲያስብና እንዲጨነቅ እያስገደዱት ነው:: ሕዝቡ ምንም አልተሳሳተም እውነቱን ነው::

ችግሩ ያለው ደምኢህህ በሕዝቡ መሐል ገብቶ ሕዝቡን ከዳር እስከ ዳር አወያይቶ የደምኢህህ ዓላማና ለአከባቢው ሕዝብ ያለውን የፖለቲካ ህልም ለማስረዳት ባለመቻሉ ነው:: በእርግጥ የደምኢህህ ተመራጮች ተኝተዋል ማለት አይደለም:: በጣም ደክመው ሌት ተቀን እየሰሩ ይገኛሉ:: ትኩረታቸውን ምርጫ ቦርድ የጠየቃቸውን መስፈርቶች በሟሟላቲና ውስጥ ለውስጥ በአከባቢው ሕዝብ ላይ ጫና ከሚፈጥሩት ግለሰቦች ጋር መደራደር ላይ ስላደርጉ ነው:: የደምኢህህ ተመራጮች ስራቸውን ቢሰሩም ጊዜው የመረጃ ዘመን መሆኑን ዘንግተው ለሕዝቡ የሚፈለገውን መረጃ እየሰጡ አይደለም:: ሕዝብ ለሕዝብ ውይይትም እያደረጉ አይደለም:: ስለዚህ ስራቸው ሁሉ የጋን ውስጥ መብራት ሆኖ ለማንም እየታየ አይደለም:: ይህንን ድክመታቸውን በአስቸኳይ ለማረም እንደተዘጋጁም እናምናለን::

ወደ ዋናው ቁም ነገር ስንመለስ የመዋሄድ ጥቅሙ ምንድነው? ደምእህህ ሲመሰረት ከምንሊክ ጀምረው የመጡት የኢትዮጵያ ገዥዎች የካፋን ሕዝብ እጅግ ስለሚፈሩ በተቻለቸው መጠን እርስ በእርሱ እያባሉት እንደ ባሪያ መግዛት ነው:: ከምንሊክ ጀምሮ ዛሬ እስከ አብይ ድረስ ያሉት መሪዎች ይህንን ህዝብ በመዘውራቸው ስር አድርገው ማሽከርከር እንጂ ሕዝቡ እንዲጠነክርና በእግሩ እንዲቆም እንደማይፈልጉ የአደባባይ ምስጢር ነው:: እነዚህ እየተቀያየሩ የሚመጡት መሪዎች መሬቱንና በመሬቱ ላይ ያለውን ሃብት እንጂ ከሕዝቡ ምንም ጉዳይ የላቸውም ሕዝብ እንዳለም አይቆጥሩም እይገነዘቡምም:: ፍላጎታቸው ሃብቱን እንደፈለጉ አዝዘው መጠቀም ብቻ ነው:: ደምኢህህ የተመሰረተው ይህንን ሸፍጥና ተንኮል ስለተረዳ ይህንን ተንኮልና ሸፍጥ ለአንዴና ለመጨረሻ ለማስቆምና ለማጥፋት ነው::

ደምኢህህ አንድ ዓይነት አመለካከትና የካፋን ማለትም የደቡብ ምዕራብን ህዝብ ጥቅም ያስከብራሉ ብሎ ከሚያምንባቸው ፓርቲዎች ጋር ግንባር የመፍጠር ሆነ የመዋሄድ ችግር የለውም::

ጥያቄው ግን ተዋህዶ አብይ አህመድ ወይም ብርሃኑ ነጋ የሚዘውሩት ፓርቲ አሸከር ሆኖ ከእነሱ ቀጭን ትዕዛዝ እየተቀበሉ ሕዝብን እየሸጡ መኖር ወይስ አብይን ሆነ ብርሃኑን መዘወር የሚችል ፓርቲ ፈጥሮ የአብይ ወይም የብርሃኑ ፓርቲ አጋር ሆኖ የካፋን ሕዝብ ጥቅም ማስጠበቅ ነው::

ሰሞኑን መዋሄድ በኢትዮጵያ ፋሽን ሆኗል:: በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አንድና ሁለት ግለሰብ ሆነው ፓርቲ ነን ብለው የተመዘገቡ እጅግ በጣም ብዙ ናቸው:: ወደ ውህደትም የሚቸኩሉት እነዚህ ናቸው ምክንያቱም ምንም አይነት ተከታይ ስለሌላቸው ቢያንስ በሚድያ ስማቸው ሲጠራ ስለምኩራሩ::

ስለዚህ የደምኢህህ ዓላማ ግልፅ ነው:: ይህም በአከባቢው ልጆች የተመሰረተ ፓርቲ ለአከባቢው ሕዝብ ጥቅም ምንም ሳይፈራ የማንንም ፍቃድ ሳይሻ ወይም ሳይጠይቅ የቆመ የሚከራከር ሕይወቱንም ለመሰዋት የተዘጋጀ የፓርቲ አመራርንና አባላትን ማፍራት ነው:: እነዚህም አባላት የአከባቢያቸውን ሕዝብ ጥቅም ማስከበር ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ አንድነትም የማይደራደሩ መሆናቸውን ያረጋግጣል:: ስለዚህ መቅደም ያለበት መዋሄድ ወይም ግንባር መፍጠር ሳይሆን በእግሩ የቆመ በሕዝቡ በፍፁም አመኔታ ያለውን ፓርቲ መፍጠር ነው:: አሊያ ዛሬ ስልጣን በእጁ ካደረገው ከኦዴፓ ውይም ስሙን ከቀየረው ግንቦት ሰባት ጋር መዋሄድ በጣም ቀላል ነው:: ምናልባትም በአምስት ደቂቃ ውስጥ ትንሽ ወረቀት ሞነጫጭሮ የቀድሞው ወያኔ የአሁኑ የኦዴፓ ድምፅ የሆኑት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ምዲያዎች እንዲዘግቡ ማድረግ ነው:: ግን መጠየቅ ያለብን ከዚያ በሗላ የህዝባችን ህሊውና ምን እንደሚሆን ነው:: ከሁሉም ኢትዮጵያ አከባቢዎች እንደ ካፋ ወይም ደቡብ ምዕራብ አከባቢ የተባረከ የለም:: ካወቅንበት ኢትዮጵያን በኤኮኖሚ ሆነ በፖለቲካ ማሽከርከር የሚችል ግዙፍ አቅም ያለው አከባቢ የእኛ ነው:: ብዙዎቹ ይህንን ስለሚረዱ እንድንደራጅና እንድንጠነክር አይፍልጉም:: ግን እነሱ ቢፈልጉም ባይፈልጉም ምርጫው የእኛው ነው:: ኳሷም በእኛ እጅ ነው የምትገኘው:: ብቻ ጨዋታው ላይ በልጠን መገኘት ብቻ ነው የሚያስፈልገን::
ካፋ ሚድያ kaffamedia

Kaffamedia Kaffamedia

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: