Leave a comment

በቅርቡ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በቦንጋ ከተማ


ደምኢህህ በካፋ ዞን በቦንጋ ከተማ ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ ለመጥራት ዝግጅትን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል:: በቅርቡም ሕጋዊ በሆነ መልኩ የሰልፉን ቀን ሰዓትና ባታውን ለመላው ሕዝብ እንደሚያሳውቅ የድርጅቱ አመራሮች ገልፀዋል::

ሰልፉ የሚጠራበትም ዋና ዓለላማ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ሕዝቡ ያለውን ቅሬታና የራሱን ዕድል በራሱ ለመወሰን ቁርጠኝነቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያሳውቅበት ይሆናል:-

1. ካፋ ወይም ደቡብ ምዕራብ አከባቢ በግዴታ ሆነ በውዴታ በጉልበት ሆነ በፀባይ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብትና አቅም ያለው መሆኑን ማረጋገጥና ለዚህም ሁሉም የአከባቢዉ ሕዝብ ይህንን ዓላማ ለማሳካት በቆራጥነት ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ለማቅረብ ነው:: የደቡብ መንግስት የሲዳማን ሕዝብ የክልልነት ጥያቄ በምክር ቤት አቅርቦ ሲያስወስን የካፋ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄ ግን ምንም ዓይነት ምላሽና ትኩረት ተነፍጎት የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል::

2. የቡና ሚውዚዬም በሕዝብ ጉልበትና ገንዘብ ገንብቶ እስከ ዛሬ ድረስ ፌዴራል መንግስት ሃላፊነት ወስዶ ሚውዚዬሙ ስራ ያለማስጀመሩ ፌዴራል መንግስቱ በሕዝቡ ላይ ያለውን ንቀትና በአከባቢው የሚኖረውን ሕዝብ እንደ ዜጋ እንደማያይና ቦታ እንደማይሰጠው ፍንትው አድርጎ ያሳያል:: ይህም ሸፍጥ ከቡና ባለቤትነት ጋር የተያያዘ ጉዳይ በመሆኑ የፌዴራል መንግስት በግልፅ የቡና ባለቤትነትን ጉዳይ ለአንዴን ለመጨረሻ ግልፅ እንዲያደርግና ሚውዚዬሙም ነገ ዛሬ ሳይል በአስቸኳይ ስራውን እንዲጀምር ጥሪ ለማቅረብ::

3. የካፋ አከባቢ በተፈጥሮ ሃብት እጅግ የበለፀገ ሆኖ ሳለ የሃብቱ ተጠቃሚ ሳይሆን የበይ ተመልካች ሆኖ በድህነት የሚማቅቅና በልማት እጅግ ወደሗላ የቀረ ነው:: በኢትዮጵያ ውስጥ ትላልቅ የእርሻ እንቬትሜንት ሴክቴር ያለው ይህ አከባቢ ሆኖ ሳለ ከውሽውሽ በበቃ ጎጄብ ገማድሮና ቴፒ ካሉት እርሻ ልማቶችና እንቬስትሜንት ሌላው አከባቢ ሲበለፅግ የካፋ ሕዝብ የሃብቱ ባሌቤት ሆኖ ሳለ የአንድ ሳንቲም አንኳ ተጠቃሚ አይደለም:: እነዚህም እንቬስትሜንቶች ሕዝቡ በላስቲክ አፈር ጠቅጥቆ ያለማቸው ሲሆን ያለአግባብና ህግን ባልተከተለ መንገድ ከሕዝቡ እጅ ተነጥቀው የጥቂት ግለሰቦች ሃብት ማካበቻ ሆነዋል:: ስለዚህ በዚሁ ሰልፍ ሕዝቡ የአከባቢው ሃብት ባለቤትና የሃብቱም ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚ የመሆን መብቱን የሚገልፅበት መድረክ ይሆናል::

4. የእንዳስትሪ ፓርክ በአስቸኳይ በአከባቢው እንዲገነባና የባቡር መንገድ እንዲዘረጋለት ሕዝቡ ጥያቅውን ያቀርባል:: ሌላ አከባቢ እንዳስትሪያል ፓርክ ሲገነባ የካፋ አከባቢ የጥሬ ሃብቱ አቅራቢ መሆኑን በመተማመን ነው:: ሕዝቡ የጥሬ ሃብቱ ባለቤት እንደመሆኑ መጠን እንዳስትሪ ገንብቶ የጥሬ ሃብቱን በፋብሪ አሻሽሎ ማቅረብና የገበያውም ተጠቃሚ የመሆን መብቱ እንደ ማንኛውም ዜጋ የተጠበቀና ማንም ሊገድበው የማይችል መሆኑን በአንክሮ ለመግለፅ ይሆናል:: በዚሁ ሰልፍ እነዚህንና የመሳሰሉት አንገብጋቢ የሆኑ ጥያቆዎችን የሚቀርቡ ይሆናል::

የካፋ ሕዝብ ከአስሩም ወረዳዎች እንደሚስተፍ ይጠበቃል:: ስለዚህ የአከባቢው ነዋሪ የሆናችሁ በሙሉ ዘር ሃይማኖትና የፖለቲካ አመለካከት ሳይገድባችሁ ለአከባቢው እድገትና ልማት የምትቆረቆሩ ያለ ምንም ጥርጣሬ ይህን ሰልፍ ለመሳተፍ ከውዲሁ እንድትዘጋጁ የድርጅቱ አመራር ጥሪ ያቀርባል::
በተለይም በመንግስት ፖለቲካ መዋቅር ውስጥ ያላችሁ አመራሮችና ካድሬዎች ይህ ሰልፍ እናንተንም የሚመለከት በመሆኑ የፖለቲካ አመለካከት ሳይገድባችሁ በአንድነት ከሕዝቡና ከደምኢህህ ጎን እንድትቆሙ ድርጅቱ ጥሪ ያቀርባል:: ተለያይተን ለአከባቢያችን የምናመጣው ለውጥ አይኖርም: ነገር ግን አንድ ሆነን ለአንድ ዓላማ ተባብረን ከቆምን ያሰብነውንና ያለምነውን ከመፈፀም በምድር ላይ የሚያግደን ሃይል አይኖርም:: አንድነት ወሳኝ ነው:: በአንድነት እንደ አንድ ሕዝብ እንቁም በአንድነት ጥያቄያችንን እናቅርብ::
ካፋ ሚድያ kaffamedia

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: