Leave a comment

ለካፋ ሕዝብ በሙሉ


ለካፋ ሕዝብ በሙሉ

እንደሚታወቀው ላለፋት 27 አመታት በደኢህዴን የተሳሳተ አካሄድና አግላይ ውሳኔ በማይመጥነው ክልል በመታቀፉ በብዙ የልማት እንቅስቃሴዎች የተጎዳው የካፋ ህዝብ ከዝህ ኮሮጆ ለመውጣት ስንቀሳቀስ ቆይቷል ።እንቅስቃሴውም የተጀመረው አንዳንዶቹ እንደሚሉት አሁን ደኢህዴን መውደቁን ተከትሎ ሳይሆን ገና በጧቱ በህወኃቱ ቢተው በላይ ምዲረ-ደቡብ ትጠርነፍ የምል ፋሽስታዊ ውሳኔ በተወሰነበት ወቅት ነበር። በተለይ በአባታችን በፍታውራር ዘውዴ ኦተሮ መሪነት የተቋቋመው የካፋ ህዝብ ደሞኪራስያዊ ኣንድነት(KPDU) በ1985 በመለስ ዜናዊ ይመራ ለነበረው ለሽግግሩ መንግስት በጻፋት ደብዳቤ ካፋ በአፍሪካ የራሷ የሆነ መንግስታዊ መዋቅር የነበራት ሉአላዊ ሀገር መሆኗን ጠቅሶ ከርቀት ፣ከፖለቲካዊ ተሳትፎና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በማያያዝ ካፋ ከደቡብ ክልል ጋር መጨፍለቅ ተገቢ አይደለም ፤በመሆኑም ራስ ገዝ ትሁን ብሎ ነበር።ከዝህ ጊዜ ጀምሮ የካፋ ህዝብ እኩል የመልማትና ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ -መንግስታዊ መብት እንዲጠበቅለት ካስፈለገ አሁን ደኢህዴን እያደረገ ካለው በካፋ ጉዳይ ሌሎች ከሚወስኑበት ሁኔታ ወጥተን በራሳችን ጉዳይ ራሳችን የምንወስንበት ካፋ ብሄራዊ የክልላዊ መንግስት ማቋቋም እንደምያስፈልግ በተደጋጋሚ ሲነሳ ቆይቷል ።በይበልጥ ደግሞ በ1986 የካፋ ቋንቋ ስምፖዝዬም ስካሄድ እና በ1998 የካፋ ፎረም ስመሰረት ተነስቶ ደኢህዴን ከህገ መንግሥት ውጭ ጫና በማዲረግ በእስር እና ወከባ በማፈኑ ሳይፈጸም ቆይቷል ።

ይህ ሁሉ እንዳለ ሆኖ የዘንዲሮ ይለያል ፤ከተላላኪነት ባለፈ በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ያን ያህል ቦታ ያልነበረው ደኢህዴን መውደቅን ተከትሎ የህዝቡ የክልል እንሁን ጥያቄ የህገ መንግስቱን የመጀመሪያ መስፈርት አሟልቶ ክልል ምክር ቤት ድርሷል ።ህጋዊው የካፋ ህዝብ ተወካይ የዞኑ ም/ቤት የካፋ ህዝብ የክልል እንሁን ጥያቄ በሙሉ ድምጽ አጽድቌል ።በመሆኑም ክልል ም/ቤቱ በአስቸኳይ ለምርጫ ቦርድ እንዲጻፍ ካፋን ወክሎ ምክር ቤት ያላችሁ ሚናችሁን ሊትወጡ ይገባል ።ካልሆነ ግን የሁልጊዜ ይቅርታ ፣ንስሃ የለም ።ህዝብ እየከሳ ራስን ማወፈር ፣ህዝብን እያደሄዩ ሀብታም መሆን መቼም ተገቢ አይሆንም ።ስለሆነም እድሉ ቢጠቢም ካፋ ህዝብ የጠየቀው ክልል የመሆን ጥያቄ ከግለሰብ የስልጣን ጥያቄ የሚበልጥ እና የትውልድ ጥያቄ ነው።ስለዝህ እየወደቀ ካለው ደኢህዴን ወጣ ብላችሁ ዘላለማዊውን የካፋ ህዝብ ትግል ተቀላቀሉ ።

የተወደዳችሁ የጉርማሾ ኮሚቴ አባለትና የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝብ በህብረት(ደምኢሕህ)አመራር አካላት፦በአሁን ሰዓት የካፋ ህዝብ እየተመኘው ያለው ክልል የመሆን ጥያቄ በአንድም በሌላ ስትጠይቁት የነበረው ጥያቄ በመሆኑ መከፈል ያለበትን መስዋእትነት በመክፈል ለተግባራዊነቱ ዘብ እንዲቆሙ ጥሪዬን አቅርባለሁ።
የተከበራችሁ የካፋ ህዝቦች እንደ ህዝብ ከቆምን እና በእራሳችን ሉአላዊ ሀገርነት ከቆምን ዘመናት ተቆጥሯል ።ብዙዎች እንደ ህዝብ ዓለም ሳያውቃቸው እኛ ግን እንደ መንግስት የታወቅን ፣የራሳችን ባንዲራ የነበረን ሚክራቾ በመባል የሚታወቀው የመንግስት ሰርዐት ያቋቋምን ህዝቦች ነን።ደኢህዴን ዛሬ የምለማመዳትን ፖለቲካ አያቶቻችን ከዛሬ 150 ዓመታት በፍት የካፋ የፖለቲካ ጠበብት በዛ ጨለማ ዘመን በብቃት ተወጥቷል ።ስለሆነም በደኢህዴን ካፋ ይመራ ዘንድ አይመጥነንም ።ስልሆነም ደኢህዴን ያወፈራቸውን ግሌሰቦችን በመተው ወደ ህዝባችን በመመለስ ታርካዊ ክብራችንን እናስመልስ ።በመሆኑም የካፋ ህዝብ የክልል ጥያቄ በተጠየቀበት ህገ መንግስታዊ መንገድ እንዲመለስ ህገ መንግስታዊ ትግል በማካሄድ ካፋ ክልላዊ መንግስት እንዲቋቋም በያለንበት የድርሻችንን እንወጣ።
Injustice anywhere is a threat for justice everywhere!
መልካሙ ሸገቶ
ቦንጋ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: