Leave a comment

ክፍል ሁለት:- ይድረስ ከጊቤ እስከ ኦሞ ከበደሌ አጋሮ እስከ ማጂ ቤንች ያላችሁ የቀድሞ ካፋ ክ/ሀገር ወይም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ምሁራን የእናሪያ የጎንጋ ቤተሰብና ሕዝብ::


ክፍል ሁለት

ይድረስ ከጊቤ እስከ ኦሞ ከበደሌ አጋሮ እስከ ማጂ ቤንች ያላችሁ የቀድሞ ካፋ ክ/ሀገር ወይም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ምሁራን የእናሪያ የጎንጋ ቤተሰብና ሕዝብ::

ክፍል እንድን ሳጠናቅቅ ሃሳቤን መቋጨት ባለመቻሌ በይደር ክፍል ሁለትን ይዤላችሁ እንደምመለስ ቃል ገብቼ ነበር:: መቸም ምሁራን በማንበብ አትታሙም ተግባራችሁ የሚያጠነጥነው እውቀት ላይ ነውና:: ጥቂቶቻችሁ ጊዜ ወስዳችሁ ፅሑፌን አንብባችሁ አስተያየት የስጣችሁኝ ለጋደኞቻችሁ (Share) ያደረጋችሁ ወዳጆቼ መረጃ መለዋወጥ እውቀት ያዳብራል (awareness) ይፈጥራልና ምሥጋናየ ይድረሳችሁ:: እድል አግኝተን በአካል ተገናኝተን ቁጭ ብለን ብንወያይ እንዴት ደስ ባለኝ:: ማን ያውቃል አንድ ቀን የክልል ጥያቄ ከተመለሰ ከያለንበት ተስባስበን የበደልነውን ህዝብ ክሰን እኛም ይቅር ተባብለን ንስሀ ገብተን ጉልበታችንንና እውቀታችን አስተባብረን ህዝባችንን ከድህነትና ኃላ ቀርነት እናላቅቀው ይሆናል:: የጅግናውን ንጉሠ ንገሥት ጋኪ ሽሮቾን ታሪክ በመዘከር::

ውድ ምሁራኖች ዛሬ ላስታውሳችሁ የምፈልገው ሀገሬ ምን ሰራችልኝ ሳይሆን እኔ ለሀገሬ ምን ሰራሁላት; ወገኔ ምን አደረገልኝ ሳይሆን እኔ ለወገኔ ምን አደረግኩለት የምለውን አስተሳሰብ ነው:: ለምን ብትሉ እውነት ለምናገር መቀበል ሳይሆን መስጠት በጣም ያስደስታል:: ሰማያዊና ምድራዊም ዋጋ ያሰጣል:: ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያትን አስተምሮ ወደ ዓለም ሲያሰማራችው “ሂዱና አስተምሩ” ያውም ያለምንም ክፍያ በነፃ እውቀትን አስተላልፉ (create awareness) ነው ያለው:: ህዝቡ ግንዛቤና መረጃ ካለው እራሱን በራሱ መርዳት ይችላል:: እናንተም የሐዋርያት ተምሳሌት ስለሆናችሁ ህዝባችሁንና ወግናችሁን ማስተማር ማንቃትና ማደራጀት ይጠበቅባችኃል:: ሀገርና ወገን የምታከብሩ ችግሩ ችግሬ ብሶቱ ብስቴ ነው የምትሉ ከሆነ በወሬ ሳይሆን በተግባር ማሳየት አለባችሁ:: ለነገሩ ምሁራን ስንል ክፍል አንድ ላይ እንደገለፅኩት ወጥታችሁ ወርዳችሁ “ጥረህ ግረህ በግንባርህ ወዝ ብላ” የሚለውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ተከትላችሁ በጥረታችው ለከፍተኛ እውቀትና ማዕረግ የበቃችሁትን ሲሆን ጥቂት የማይባሉ በፎርጅድና የሌሎችን የመመረቂያ ፅሑፍ እየሰረቁ በገንዘብ እየገዙ የሐሰት ከፍተኛ ትምህርት አለን በማለት በእውቀታቸው ሳይሆን በፖለቲካ አመለካከታቸው ሥልጣን ላይ ቁብ ብልው ሀገር የሚያተረማምሱና የገዛ ህዝባችውን ከጨቋኛች ጎራ ተሰልፈው የሚያሰቃዩትን ሐሰተኞች ምሁራንና ላሉበት ወይም ለነበሩበት ሥልጣን ድጎማ “የክብር ዲግሪ” የሚጭኑትን ግለስቦችን አይጨምርም::

አሁን የምንገኝበት ዘመን ወጣት ምሁራን እንደ እንጉዳይ የፈሉበት አብዛኛዎቻችሁ ወጣት ምሁራን ናችሁ:: እውቀቱም አቅምና ጉልበቱም ሀብቱም በመጡኑም ቢሆን አላችሁ:: ከሌላው ወገናችሁ የተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ ናችሁ ሀገር ቤት የምትኖሩ ማለቴ ነው:: ውጭ ሀገር የምትኖሩት ሀገር ቤት ካሉት ምሁራን ጋር ኑሮአችሁ ሲነፃፀር የሰማይና የምድር ያህል ይራራቃል:: ሁላችሁም ግን የሚጎላችሁ አንድ ነገር አለ:: እርሱም ብዙዎቻችሁ የሀገርም ሆነ የወገን ጉዳይ ሲጨንቃችሁ አይታይም:: ግድም የላችሁም; ስለማንነታችሁም ሆነ ስለታሪካችሁ ለማወቅ አትፈልጉም ስትፈልጉም አንታይም:: ያለፉት አያት ቅድመ አያቶቻችሁ ለሀገርና ለወገን የከፈሉት መስዋዕት እኛ ዘንድ ዋጋ አልተሰጠውም: ብዙዎቻችን ፊታችንን ተወልደን ወደ አደግንበት አካባቢ ሆነ ማህበረሰብ ላለመመልስ የማልን አንታጣም:: ከራሳችን ማንነትና ባህል ይልቅ የፈረንጁን(የውጭውን) አለባበስም ሆነ አመጋገብ በአጠቃላይ የኑሮ ዘዴ ለመከተል ስንሞክር የራሳችንን አኩሪ ታሪክ ወግና ባህል እሴቱን ጭምር አሽቀንጥረን በመጣል ህልውናችንን ጭምር የረሳን ብዙ ነን:; ምንም ለመምስልና ለማስመሰል (identity crises) ብንሞክር እውነታው ግን እኛ ከእኛ ውጭ ሌላውን መሆን አንችልም:: ዘር ከልጏም ይስባል :: ራስን መካድና በራስ አለመተማመን መድሐኒት የማይገኝለት በሽታ ስለሆን መድሐኒቱ ምንም ይሁን ምን ወደ ራስ ማንነት መመለስና በራስ መተማመን ነው (self confidence and identity):: ከማንም የተሻለ አኩሪ ታሪክ አለን:: ምንም እንኳን እንደ ሌላው ማህበረሰብ በአደባባይ ወጥቶ ስለማንነታችን የሚናገርልን ባይኖርም ምሁራንም ዝምታን መርጣችሁ እንደ የዋህዋ እንስሳ የተጫናችሁ የግፍ አገዛዝ እየከበዳችሁም ቢሆን መገዛትን ስለመረጣችሁ:: አስተዳድሩም ተብላችሁ ሥልጣን ተቀንጭቦ የተሰጣችሁ ደግሞ ለህዝብ ከመወገን ይልቅ የውሎ አበልና የሥልጣን ጥም ስለያዛችሁ ተነስ! እሺ:: ተቀመጥ! እሺ:: እጅ አውጣ! እሺ ሁሉን እሺ እንጂ ለምን ብላችሁ የማትጠይቁ ብዙዎች ናችሁ:: ጥቂቶች መስዋዕት ሊከፍሉ ቢሞክሩም የብዙሀኑ ካድሬዎችና አድርባዮች ዱላ ያርፍባችዋል:: ታዲያ ምን ይሻለናል እኛም ሆን ህዝባችን ብዙ ምሁራን እያሉን ቆራጥና ደፋር አመራር በማጣታችን ተጠላልፈን በሙውደቅ ለበይዎች ሲሳይ በመሆን ለእጥፍ ድርብ አፈናና ጭቆና እራሳችንንም ህዝቡንም እየዳረግነው ነው:: ነፃ ለመውጣትና የራስን እድል በራስ ለመውሰን ክልል መሆን ግድ ይላል:: ደህዴን ግን ህገመንግሥቱን ንዶ ለበልጠ ጭቆና እየተዘጋጀ መሆኑ እየተስማ ነው:: በሰላማዊ መንገድ የህዝባችንን ህይወትና ንብረት በማይጎዳ መልኩ ቀፎው እንደተነካ ንብ በህብረት ወጥተን ጭቆናው እንዳንግፈገፈን በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ማስማት ግድ ይላል:: ለዚህም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት የምኖሩ ምሁራንና ባለሀብቶች በሳል እመራርና ድጋፍ ያስፈልጋል::

ሀገር የነበርን ክልል መሆን አይበዛብንምና ጥያቄው በህገ መንግሥቱ ይመለስ

ፋንታዬ መኮ
ነሐሴ 15 ቀን 2011 ዓም
21 August 2019
ክፍል ሶስት ይቀጥላል:: ቸር ይግጠመን
ካፋ ሚድያ kaffamedia

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: