1 Comment

ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው


ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው

ሰሞኑን በAugust 13,2019 Kaffamedia በFB ድህረገፁ ላይ የካፋ ቦንጋን ብሔራዊ ቡና ሙዚዬምን አላውቅም ያለው ቡናና ሻይ ልማት መ/ቤት አአ ላይ የቡና ፓርክ እገነባለሁ ማለቱን ያስፈረውን አስደንጋጭ አሳፋሪና አስዛኝ ዜና ስመለከት ዓይኔንም ጆሮየንም ማመን አቃተኝ: በህልምና ቅዠትም መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ተሳነኝ:: ዛሬ ላይ ሁሉ ነገር ከሃገርና ከሕዝብ ጥቅም ይልቅ በዘር መነፅር በመመልከትና እኛ ብቻ ተጠቃሚ እንሁን የሚሉት ምሁር ነን ተብዬ ደደቦች ሃገሪቱን ወዴት እያመሩ ነው? ስለ ሀገር አንድነት የሚያቀነቅኑት የጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድስ ሥልጣን ምን ላይ ነው? በሙሉ ለብሔራቸው (ያዩትን ሁሉ ለሚመኙ ዘረኞች ካስረከቡ በግልፅ ይንገሩን:: አሁን ላይ የካፋ ምድር ለምለምነት ያስጎመጃቸው የካፋን ምድርና ሕዝቧን በጨለማ አኑረው መሬቱንም ሃብቱንም ለመቆጣጠር እያሉ በስውር ደባ እየሸረቡ ይገኛሉ:: ያለነው ድንጋይ ዳቦ ዘመን ላይ ሳይሆን 21ኛው መቶ ክ/ዘመን ማብቂያ መረጃ በመዳፋችን ውስጥ ባለበት ዘመን ላይ መሆናችንንና በዓለም ዙሪያ በተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥብቃ ህጎች መኖራቸውን የረሱት ይመስላል:: ታሪክ አይሰረቅም:: ሌቦችንና ወራሪዎችን በፅኑ ማውገዝ ብቻ ሳይሆን የካፋም ሆነ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ በህልውናው ላይ በሚቃጣው አደጋ አይደራደሩም::

የቄስ ሚስት አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት የቄሱን መፅሐፍ አጥባ ቄሱ ከቤተክርስቲያን ወደ ቤት ሲመለሱ ለዘመናት ጠብቀው በጥንቃቄ ያቆዩት መፅሐፎቻቸውን መሀይሟ ባለቤታቸው አውድማ ጠበቀቻቸው:: ቀደም ብለው የማይመለከታት ሥራ ውስጥ እንዳትገባ ባለማድረጋቸው: ዛሬ ላይ ድግሞ ለዘመናት አብሮ ይኖር የነበረውን የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር ፓለቲካ ከፋፍለው ጉልበተኛው በጉልበት እንዲጠቀም እየፈቀዱ ዘመን የተሻገረውንና ከአያት ቅድመ አያቶቻችንና ካባቶቻችን የወረስንውን አኩሪ ታሪክና ሀገር በሴረኞችና በዘር ፖለቲካ ቁማርተኞች ቁጥጥር ሥር በማዋል ሀገር አልባ በማድረግ በሀብትና ንብረቱ ተጠቃሚ (ያለፈው አልበቃ ብሏችው) ላለማድረግ የሰብአዊ መብቶችን በተፃረረ መልኩ ህዝባችንን ለዳግም ጭቆናና ብዝበዛ ለመዳረግ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም:: ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል:: ከታሪክ እንደተረዳነው የካፋን ልዑላዊነት በመፈታተን የሸዋ መሳፍንትና የኦሮሞ ወራሪዎች ከመቶ ዓመት በፊት ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርጉም በየጊዜው የተነሱት የካፋ ነገሥታት በጀግንነት ተዋግተው የሽንፈት ሸማ አከናንበው ወደ መጡበት እንዳባረሯቸው በተለያየ ጊዜ የተነሱ የታሪክ ተመራማሪዎችና ፀሐፍት መዘገባቸውን የታሪክ ማህደር በማገላበጥ ሀቁን መረዳት ይቻላል::

ምን ያድርጉ ህግና ሥርዓት በሌለበት ሀገር “አባት ዳኛ ልጅ ቀማኛ” እንደ መሀይሟ የቄሱ ባለቤት ሀገርና ታሪክ ሲያወድሙ “ተው ተሳስታችኃል የሚል ዳኛ በመጥፋቱ ሀገር እያመሱ ይገኛሉ::

ጠ/ሚ ዶክተር አቢይ አህመድ ከዓመት በፊት ወደ ሥልጣን ሲመጡ በተዋቡ ቃላት የኢትዮጵያን ህዝብ ስሜት ከተቆጣጥሩ በኃላ ኢሀዲግን ድርጅቴ እያሉ ቁርኝታቸውን ሲገልፁ በሌላ በኩል የዋሁን የኢትዮጵያን ህዝብ “ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ” በማለት ፍቅርን እያቀነቀኑ በኢሀዲግ አመራር የተንገሸገሸውን ኢትዮጵያውያዊ ልብ ሰርቀው ነበር::

ሁሉን ነገር ትተን በፍቅር እንሻገር ሲሉት የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ስትወልድ ጥሎ ገደል ይገባል እንዲሉ መገዳደል ያብቃ እስር ቤቶች ሙዝየም ይሁኑ በሰላም ለመኖር መደመር ነው የሚያዋጣን (የቀማ ሳይመልስ የበደለ ሳይከሰስ) በደለኞችን በይቅርታ እንለፋችው የውጭ ግንኙነት እናዳብር ዳያስፖራው ወደ ሀገሩ ገብቶ በፈልገው መስክ በሀገሩ እድገትና ብልፅግና ላይ ይሳተፍ (ብቻ 1 ዶላር በቀን ይስጥ) ተቀናቃኝ የሚለው የፓርቲዎች ታፔላ ወደ “ተፎካካሪ” ይለወጥና ሀገራቸው ይግቡና ለምርጫ ይደራጁ “ሁሉንም እሺ እሜን” የፓስተሩ ስብከት ህዝቡ ሁሉንም ነገር እርሶ እንዳሉ ሜዳውም ፈረሱም ይኸውልዎት እንደፈለጉ አሉና ገና ከአፋቸው የሚውጣውን ቃል በቅጡ ሳያዳምጥ ማስተጋባትና ማጨብጨብ አዎንታ እንጂ ማንም አሉታዊ ምላሽ ለመስጠት የደፈረ ኢትዮጵያዊ ምሁርም ሆነ ተፎካካሪም በሉት ተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅት የሃይማኖት መሪ አለመኖሩ ዛሬ ላይ ብዙዎቻችን ራሳችንን መጠየቅ ከጀመርን ውለን አድረናል::

በሚያማልል ርቱእ አንደበት ከሊቅ እስከ ደቂቅ ተጠልፎ ያልወደቀ ለውጥ የተጠማ ኢትዮጵያዊ ጥቂት ሲሆን ያንን ሁሉ የዋህ ህዝብ የሞቀና የደመቀ አክብሮት ዓመት ሳይሞላው የአንታርቲክን በረዶ አምጥተው አወረዱበት:: ስሜቱን አቅዘቀዙት ተስፋውን አጨለሙበት:: ከድጡ ውደ ማጡ ሆነበት::የፍቅር ሐዋርያውና ፓስተሩ መሪ የኢትዮጵያ ሙሴ ቃላቸውን መጠበቅና ህዝቡን ወደ ታለመው እድገትና ብልፅግና ማሽጋገር ተሳናቸው:: እሁን አስፈላጊ ከሆነ ጥይትም አለን አሉ: ህገ መንግሥቱን እራሳቸው ናዱት::ከጎናችው የተሰለፈን ህዝብ አሳዘኑት::

ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱን ነብር ዥንጉርጉርነቱን አይለውጥም እንዲሉ ተኩላም ምንም የበግ ለምድ ለብሶ ከበጎች ጋር ለመመሳሰል ቢሞክርም ተፈጥሮው ግድ ስለሚለው በግ ሊሆን በምንም መንገድ አይችልም:: ውሎ አድሮ ተኩላነቱ ይጋለጣል:: አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተንፀባረቀ ያለው እውነታ ይህ ነው::

የዚህ ፅሑፍ አቅራቢ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በጠ/ሚ ግሩምና አፍ አስከፋች ንግግር ከተጠለፉት ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ እንደነበርና ብዙ ኪሎ ሜትር በመጏዝ ለመደመር የበቃ ቢሆንም ውሎ አድሮ ግን በሃገር ውስጥ መቀነስ እንጂ መደመር ያለመኖሩን ሲረዳ ልቡ በሐዘን ጦር ክፉኛ እየደማ ይገኛል::

በጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ ላይ ጥርጣሬ ያሳደረብኝ የመጀመሪያው የፖርላማ ንግግር ነበር:: የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰብ በዝርዝር እያነሱ ሲያወድሱ በንቀትም ይሁን ባለማወቅ የታሪክ ባለቤትና የቡና መገንኛ ብሎም የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆንውን በተለይም እትብታቸው የተቀበረበትን አፈር ፈጭተው ጭቃ አቡክትው ያደጉባትን ምድር የኢትዮጵያ አካል ካፋን ለይተው በዝርዝሩ ውስጥ ለማካተት ያልቻሉበት ምክንያት በግልፅ ባይታወቅም ጉዳዩ እህል ላበደረ አፈር ወርቅ ላበደረ ጠጠር ሆነብኝ:: የተዉለዱባት አጋሮ የካፋ አካል ስትሆን ጅማ ደግሞ የካፋ ምድርና የካፋ ዋና ከተማ መሆኗን ሌላው ቢቀር በሳቸው የእውቀት ደረጃ ጠፍቷችው ይሆን ወይንስ ሌላ ድብቅ ሴራና አጀንዳ ከመጋርጃው በስተጀርባ አለ በማለት ጥርጣሬ አጫረብኝና በትለያየ ጊዜ የሚያደርጉትን ንግግር መከታተል ጀመርኩና አንድም ቀን በየትኛውም ሥፍራ የካፋን ስም አንስተው አያውቁም ለምን????:::::::: ሰሞኑን እየወጡ ያሉ መረጃዎች ለጥርጣሬው ፍንጭ እየጠቆሙ ይመስላል:: የቡና ሙዚየም ሥራ ይጀምር መልስ የለም:: የክልል ጥያቄ ሲንሳ ማስጥንቀቂያ:: በሰላምዊ ህዝብ ላይ የኮማንድ ፖስት ጋጋታ እኮ ለምን??? ዛሬ ደግሞ የቡና ፓርክ አአ ላይ ለመገንባት ለምን አስፈለገ? ግንባታው መሆን ያለበት ካፋ ውስጥ ቦንጋ አልነበረም ወይ? ይህ ሁሉ ደባ የካፋን ሕዝብ ማሳጣትና የቡና ባለቤት እንደመሆኑ መጠን ከቡና ኢኮኖሚ እንዳይጠቀም የተደረገ ግልፅ ሴራ አይደለም ወይ? ይህም በካፋ ሕዝብ ላይ ጦርነት ማወጅ ነው ብሎም እናንተ ኢትዮጵያዊ አይደላችሁም ማለት ነው::

ምንም እንኳን በበደል ላይ በደል በግፍ ላይ ግፍ ቢደራረብበትም ህዝቡ ጠ/ሚሩ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ያቀረቡትን “የመደመር” ጥይቄ ሞቅ ደመቅ ባለ ሰላማዊ ሰልፍ በነቂስ ወጥቶ ሹመት ያዳብር ከጎንዎ ነን ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶ ወደቤቱ ትመልሶ ከነገ ዛሬ ከተማችንን ጎብኝተው ብሶታችንን አዳምጠው ሌላው ቢቀር ያበረታቱናል ብሎ መንገድ መንገድ ሲያይ ከየዋሁ ህዝብ ጅርባ ደባ እየተሰራበት መሆኑን የተረዳው ቡና የካፋ ሳይሆን የኦሮሚያ ነው የሚለውን መርዶ የሰማ እለት ነው:: ህዝቡ ጆሮውን ማመን አቃትው:; ነገሩ ግልፅ ሲሆንለት በነቂስ ወጥቶ በህልውናው ላይ እንደማይደራድር አምስት ቀን የፈጀ ሰላማዊ የተቃውሞ ድምፁን ቦንጋ ላይ አሰማ::ሌላው የሚገርመው በተለያየ አጋጣሚ የድርጅታቸውን ክልል ህዝብ በወርቅ ሲመስሉ ለሌሎች ክልሎችም የተለያየ ዝናና ክብር ሲችሩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ መፈጠሩን ሳያውቁ እሳችው ልባቸው ውስጥ ተደብቆ ያለው (ለኦሮምያ የገቡትን ቃል ኪዳን ለመተግበር የቡና መገኛን የኦሮሚያ ክልል ነው ለማለት እየዳዳቸው የታሪክ ሌቦችን በመደገፍ የተዛባ አመለካከት ለመፍጠር ለዓለም ለማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ:: ኦሮሚያም ጅማን ዳኛ በሌለበት ሀገር ከነሽፈራው ሽጉጤ ጋር በተደረገ የውስጥ ለውስጥ ስምምነት ባለቤት የሆነውን የካፋን ህዝብ ነቅለው የራሳቸው ለማድረግ ካፊቾን በማፈናቀል ኦሮሞን በብዛት ከሌላ አካባቢ እያመጡ በማስፈር ላይ እንደሚገኙና ውለው አድረው ካፊቹን ለማስወጣት እቅድ እንዳለ ጅማ ውስጥ በስፋት ይነገራል:; ሌላውና የሚደንቀው ጉዳይ ደግሞ ሰሞኑን በተነሳው የክልል ጥያቄ ለካፋና ወላይታ ባለሥልጣናት ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ አካባቢውም ላይ ህዝቡ ነፃነቱን ያለበቂ ምክንያት ተነጥቆ ትንፍሽ እንዳይል በግዞት ላይ በኮማንድ ፖስት ቁጥጥር ሥር መውደቅ አሳዛኝና አሳፋር ድርጊት ነው::

ምንም እንኳን በጭቆና ላይ ጭቆና በግፍ ላይ ግፍ ቢደራረበትም የካፋ ሕዝብ ወይም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉንም እንዳመጣጡ በአስትዋይነት ተቀብሎ በማስተናገድ ከዛሬ ነገ የጠ/ሩ አመለካከት ይሻሻል ይሆናል ጊዜ እንስጣቸው በማለት የለውጥ አጋርነትን ከመደመር ጀምሮ ሊያሳያቸው ቢሞክርም ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቄስ አይተውም እንዲሉ እሳቸውና አስተዳደራቸው ከመጋረጃ በስተጀርባ እያሴሩ ያሉትና እስትራቴጂ የነዱፉት ይህን ህዝብ ሀብትና መሬቱን ተነጥቆ ለባለግዜዎች ገፀ በረከት አቅርበው ሥልጣን ከኢሀዲግ ወስደው የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም እየሞከሩ ያለ ይመስላል:: ሰሞኑን ከክልል ጥያቄው ራሱን እንዲያገል በደህዴንና በግብረ አበሮቹ አማካይነት ካፋ እንዳይበረታ እንዳይጠነክር ለማድረግ ሽር ጉድ እያሉ ባሉበት ወቅት መቸም ጆሮ አልሰማ አይል ዛሬ ደግሞ አስደንጋጭና አደገኛ የሆነ ዜና ከወደ አዲስ አበባ እየተናፈሰ ይገኛል:: ግዛኝ ግዛኝ ብለው ለመሽጥ አሰበኝ እንደተባለው እየሆነ ነው ነገሩ::
የቡና መገኛው ካፋ እንጂ አአ አይደለም ወደዳችሁም ጠላችሁም ይህ አያከራክረንም:: ህልም ማለምና መመኝት መብታችሁ ነው ቅዠትም መቃዠት ትችላላችሁ:: እኛ አያገባንም አይመለከተንም:: መለስ “መላጣ ማለት ይቻላል ችግር የሚሆነው መላጣው በጣት ሲነካ ነው” ብሏል

እሁን ላይ ህዝቡ የሚጠይቃችው አንገብጋቢ ጥያቄዎች::

1. የክልል ጥያቄ መልስ በአስቸኳይ እንዲሰጠን እንጠይቃለን
2. ቦንጋ ላይ የተገነባው የቡና ሙዝየም በአስቸኳይ ሥራ እንዲጀምር የታሰበውም የቡና ፓርክ በቦንጋ እንዲገነባ እንጠይቃለን
3. በ50 ሚልየን የአሜሪካን ዶላር ሊገነባ የታቀደው የቡና ፓርክ በተገቢው ቦታ ካፋ ውስጥ መሆን አለበት እንጂ አዲስ አበባ ላይ መሆኑን በጥብቅ እንቃወማለን እናወግዛለን::
4. ከህዝቡ እውቅና ውጭ በህልውናው ላይ የሚሽረበውን ደባና ስምምነት አጥብቀን እናወግዛለን
5. በራሱ ሀብት ላይ መወሰን ያለበት የካፋ ህዝብ እጂ በቡናና ሻይ መስርያ ቤት አአ የተሰገሰጉት ዘረኞች አይደሉም
6. የቡና መገኛ ካፋ እንጂ አአ አይደለም::
7. በሀገር ጉዳይ ላይ ካፋ መገለል የለበትም
8. በህልውናውና በኢትዮጵያዊንቱ አይደራደርም

ድል ለተጨቆኑ ህዝቦች
ክልላችን ካፋ ነው
የጊዜ ጉዴይ እንጂ ኢትዮጵያ በነፃነት ለዘለዓለም ትኖራለች:: ጠላቶችዋ ግን ይወድማሉ::
ፋንታዬ መኮ
ካፋ ሚድያ kaffamedia

One comment on “ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው

 1. ካፋ በዓለም ላይ በሰዉ ልጅ ላይ ሊደርስ የሚችለዉን ግፍ ሁሉ የተቀበለ ነዉ፡፡ መንግሥቱን በሃይል ያዉም ከጠላት በተሰበሰበ ዘመናዊ መሣሪያና በአዉሮፓዊያን የጦር ባለሙያዎች እርዳታ ካጣበት ዕለት ጀምሮ፣ ደኑ ሁሉ የሰዉ ዓፅምና ሥጋ ብቻ ሆኖ እስኪሸት ድረስ ተጨፍጭፏል፡፡ ይህ ያልተነገረለት የጦር ወንጀል ነዉ፡፡ የተረፈዉ በባርነት ተሸጧል፡፡ ይህም አልበቃ ብሎ እንዲሰደድ ሲደረግ እንኳን በአገሪቱም በሁሉም አቅጣጫዎች በተወሰነ ቁጥር ብቻ እንዲሰፍር ተደርጎ ተበታትኗል፡፡

  ይህም ሁሉ ሆኖ ኢትዮጵዊነቱን ተቀብሎ ለጋራ ልማትና ብልፅግና ለመሥራት ወስኖ፣ ቂምና በቀል ረስቶ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር በሰላም በምሳሌነት መኖርን መርጧል፡፡ በሰፈራ፣ በንግድ፣ በሥራም ይሁን በስደት ወደ ካፋ የመጡትን ኢትዮጵዊያን ብቻ ሳይሆን የጎረቤት አገር ዜጎች ተንከባክቦ አብሮ መኖርን አሳይቷል፡፡

  በአፄ ምንሊክ ዘመን የንግሳዊ ሥርዓቱ ምልክቶች ለፈረንጅ ተለግሰዉ ደብዛዉ እንዲጠፋ መደረጉን ያዉቃል፡፡ በሃይለሥላሴ ዘመን ደግሞ ወደ አዉራጃነት ደረጃ ዝቅ ተደርጎ ሲተዳደር፤ በካፋ ላይ የተፃፉ ማንኛቸዉም መፅሐፎች ወደ አገር እንዳይገቡ ሲደረግ፣ እንኳን በአዉራጃ ደረጃ በወረዳና በመንደር ደረጃ እንኳን ካፈቾ የተባለ አንድም ግለሰብ በሃላፊነት እንዳይመደብ ተደርጎ፣ የሰሜን ሰዎች በብዛት ሲሾሙበትና ሲሰለጥኑበት፣ ሌላዉ ቀርቶ ከቤንች፣ ከኩሎ፣ ከወላይታና ከኦሮም አስተዳዳሪዎችና የበታች ሹሞች ሲሾሙበትና፣ በፖሊስ አቅም ሳይቀር ከኩሎና ከኦሮሚያ እየተመለመሉ ሲመደቡበት፣ በየመንደሩ ከኩሎና ከአጎራባች አካባቢዎች የተመለመሉ ነጭ ለባሾች ተመድበዉ እጅ ከእግር ተጠፍሮ በተለይም አጠራጣሪ በሆኑት ካፈቾዎች ላይ በየሳምንቱ ሪፖርት እየተደረገበት ሲገዛ ቆይቷል፡፡

  በአብዮታዊዉ ደርግም ጊዜ ቢሆን ከሃይለሥላሴ ባልተናነሰ ሲገዛና በጥርጣሬ ሲታይ፣ ማለቂያ ለሌለዉ ጦርነት ልጆቹን ሲገብር፣ በአስራ ሰባት ዓመት ዉስጥ ስልጣን የነበራቸዉ በተለያየ ጊዜ ሁለት ከንቲባዎች፣ አንድ የገበሬዎች ማህበር ሊቀ መንበርና አንድ የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ብቻ ነበሩ፡፡ ለወድቅ ሲቃረብ እንኳን ኢህዲሪ ብሎ በመሰረተዉ አስተዳደር፣ በሁሉም (ከ31 በላይ) አስተዳደር አካባቢዎች የየአካባቢዉ ተወላጆች ሲሾሙ፣ ካፋ ላይ ግን የኢሠፓ ዋና ፀሐፊዉም ሆነ ዋና አስተዳዳሪዉ ከሌላ አካባቢ የመጡ ሹመኞች ተመድበዉ በክልሉ አንድ ምክትል አስተዳዳሪና የሸንጎ ፀሐፊ ብቻ ከካፋ ልጆች መመደባቸዉን እናዉቃለን፡፡ በቦንጋ አዉራጃ የተመደቡ የኢሠፓ ፀሐፊና አስተዳዳሪዎች መመደባቸዉ ሣያንስ፣ ኮ/ል መንግሥቱ ለመጨረሻ ጊዜ የክልሉን ህዝብ በሰበሰቡበት ጉባዔ፣ “የካፋን ሰዎች አልቻልንም“ ብለዉ ሪፖርት አድርገዉ ተስፋ በቆረጡት ፕሬዚዳንት ህዝቡን ሊያስመቱ ሞክረዉ ነበር፡፡

  የካፋ ህዝብ ይህንን ሁሉ እያወ፣ ችሎ በአብሮ መኖር፣ በኢትዮጵያዊነቱ ፀንቶ፣ በሰብአዊነትና በአርቆ አስተዋይነት በሰላማዊ መንገድ ብቻ ትንሹን መብቱን እየተየቀ ነዉ፡፡ ለራሳቸዉ “ ተገፋን፣ ተበደልን፣ተገደልን፣ባህላችን ተጨቆነ“ ብለዉ የተነሱ ወገኖች እንኳን ዓለም ከአራት መቶ ዓመታት በፊት ያረጋገጠዉን፣ ቡና የተገኘዉ ከእኛ ነዉ ሲሉ በሰላማዊ መንገድ ብቻ ነዉ የተቃወመዉ፡፡

  ብልህነትን፣ ሰላማዊነትንና አርቆ አስተዋይነትን እንደስንፍና የቆጠሩት የወቅቱ ገዢዎቻችን ይህንን ትዕግሥታችንን በመፈታተን፣ ህዝባችንን በተለይም ወጣቱን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ሊገፉት ይፈልጋሉ፡፡ አሁንም ተደራጅተን በጥንቃቄ ታግለን ወደ ግባችን መድረሳችን፣ ተገቢዉን ክብራችንን ማግኘታችን የማይቀር ነዉ፡፡ በዚህ ሁኔታ የበለጠ እያስከፉን ህዝባችን ለሌሎች መሣሪያ እንዲሆን ቢሞክሩም አናደርገዉም፣ ምክንያቱም እኛ የአስተዋዮቹ የካፋ ልጆች ነን፡፡

  ከሮ ኬቶ ጋዎ

  Liked by 1 person

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: