Leave a comment

በጠቅላይ ሚ /ር ዶ/ር አቢይ አህመድ ጉዞ የተሰሙኝ 3 እይታዎች


Amanuel Karlo Gano

በጠቅላይ ሚ /ር ዶ/ር አቢይ አህመድ ጉዞ የተሰሙኝ 3 እይታዎች70672943_388282588772278_3114441907732742144_n
ባብዛኛው አጅግ የተደሰትኩበት ሲሆን አንዳንድ ቅሬታዎቼንም ሳልደብቅ አጋራለሁ::

በ1ኛ: ደረጃ: ምንም ያህል አንደ ካፋ ህዝብ ጉጉትና ፍላጎት ጉብኝታቸዉ የዘገየ ቢሆንም ጊዜ ሰጥቶ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ: ከክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮነን: ከክቡር የመከላከያ ሚኒስትር ኦቦ ለማ መገርሳ አንዲሁም ከክብርት ቀዳማዊት ኢሜበት ዝናሽ ታያቸዉ ጋር በመሆን ካፋን መጎብኘታቸዉና በተለያዩ መድረኮች ሲነሱ የቆዩትን የካፋ ህዝብ ጥያቄዎች ከህዝቡ አንደበት መስማት መቻላቸዉ በኔ አይታ ትልቅ ነገር ነው:: ከዚህም ይበልጥ ባለፉት 28 አመታት ተደፍኖና ታፍኖ: ተረስቶ የቆየዉ የማንነት ገናና ታሪካችን: አኩሪ እትዮጵያዊነታችን: ከመሃላችን የኖሩትን ማንኛዉንም የአትዮጵያ ልጆች አቅፈን አብሮ የመኖር ባህላችን: ከሰዉም አልፎ የተፈጥሮን ደን ጠብቀን ለትዉልድ ስናሸጋግር የቆየን ህዝብ መሆናችን:: 20 ነገስታትን በሰላም ከስልጣን ወደ ስልጣን ስናሸጋግር የቆየን ስልጡን ሕግና ስነስርዓት ያለን: የራሳችን ፓርላማና ምክርቤት (ምክረችኦ): አንዲሁም የተለያዩ የስራ ዘርፎችን የሚመሩ አንዴዎደራኖ: ጉቸራኖ: የመሳሰሉ በዛሬዉ ሚኒስቴር ደረጃ የነበሩ መሪዎች የነበሩን: ህዝብ መሆናችን:: የአስተዳደር ታሪካዊ እሴቶቻችን ለዛሬዋ ኢትዮጵያ አጅግ የምያስፈልጔት አንደሆነም ጭምር በትናንትናዉ እለት በጠቅላይ ሚ/ሩ አንደበትና በቦታዉ በነበሩት በአባቶቻችንም አንደበት ጭምር መስማታችንና በስፍራው በተገኙት ብሔራዊ የሚድያ ኔትዎርኮች አማካይነት የአትዮጵያ ህዝብ ገናናዉን የካፋ ህዝብ ታሪክ መስማት መቻሉ በኔ አይታ ለካፋ ህዝብ አንድ ድል ነው::

በ2ተኛ ደረጃ አንደ ታላቅ ድል የያዝኩት አሁንም ላለፉት 28 አመታት ለመጀመርያ ያየሁት: እንደ አንድ ህዝብና አንደ አንድ ቡድን: የካፋ ምክር ቤትና የርዕሰ መስተዳድሩ: የካፋ ጉርማሾ: የተለያዩ የካፋ አክትቪስቶች: የካፋ: ምሁራን: የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ህብረት ተወካዮች በአንድነትና በአንድ ግንባር ቆመን የህዝባችንን አንኴር ጥያቄዎች ማንሳት መቻላችን ነው:: ጥያቄአችን የተፈለገዉን መልስ ባያገኝ አንኴን ይህ በቀላሉ የምናየዉ ድል አይደለም:: በአንድነትና በአንድ ድምፅ ከህዝባችን ጎን ከቆምን የማንፈነቅለው ድንጋይ የማንገለብጠዉ: ተራራ: አይኖርም:: ጊዜ ይወስድ አንደሆን አንጂ የማናስመልሰዉ ጥያቄም አይኖርም:: የዛሬዉ አንድነት በግልፅ የሚያሳየን ለመጀመርያ ጊዜ ለራስ ትርፍ ሳይሆን ለካፋ ህዝብ ብሶት የሚኒቆረቆር: የካፋ ልጆች አንድ መሆንና በአንድነት መቆም መቻላችንን ነዉ:: ለካፋ በአንድነት በመቆም የህዝባችንን መብትና ህልዉና ማስከበር ከቻልን ለሀገራችን ኢትዮጵያም ኢትዮጵያዊነት ማንነታችንን አንደኛ ከሚወዱ ወገኞች ጋር አብረን መቆም እንችላለንና የኛ በአንድነት መቆም ትርፉ ለካፋ ብቻ ሳይሆን ለአኢትዮጵያም ጭምር ነው ብዬ አምናለሁ::

በ3ተኛ ደረጃ ለተነሱ ጥያቄዎች በተሰጡ መልሶች ዙርያ አንድ ሁለት ነገር መናገር እፈልጋለሁ::
1: ለክልል ጥያቄ የተሰጠዉን መልስ በተመለከተ ተስፋ የምያስቆርጥ ነገር አላየሁም:: ጥያቄዉ በአዎንታ ወይም በአሉታ የሚመለስበት መድረክም አልነበረም:: ለኔ ዋናዉ የህዝቡን የጥያቄ ይዘትና ትክክለኛ ምክንያት ጠ/ሚ ከህዝቡ አንደበት መስማት መቻላቸዉ ነዉ:: ምክንያቱም ህዝቡ ሌሎች ስላነሱ ሌሎችን ኮርጆ ያነሳው ጥያቄ ሳይሆን ላለፉት28 አመታት ሲካሄድ ለቆየዉ የህዝብ ስቃይ የፍትህ ጥያቄ ነዉ:: ዉሳኔዉ የሚሰጥበት የራሱ ሕጋዊ መዋቅር ያለዉ ጉዳይ ስለሆነ አሁንም ሳንታክት መስፈርቶቹን በሙሉ አሟልተን የምንቀጥለዉና የምንጠይቀዉ ጉዳይ ይሆናል:: አንግዲህ አንደቀሞዉ አባባል ”ሰማይ አይታረስ ንጉሥ አይከሰስ” የሚባለው አሁንም ይሰራል ካልተባልን በስተቀር ህገ መንግስቱ በግልፅ ያስቀመጠዉ ጉዳይ ስለሆነ የሕግ ከለላም ይኖረናል::

2: የቡናን መገኛና ባለቤትነትን በተመለከተ ለተነሳው ጥያቄ የተሰጠዉ መልስ: አልደብቃችሁም አሳዝኖኛል አስቆጥቶኛል:: ከዚህ ቀደም የፌደራል መንግስት ወስኖ ያፀደቀዉ ጉዳይ ቢሆንም አሁንም ለዉዝግቡ ክፍት መንገድ ተሰቷል።
ይህንን ዉዝግብ ለአንዴና ለመቸረሻ ለመዝጋት ጥሩ አጋጣሚ ነበር: አጋጣሚዉ ግን ታልፏል:: የቡናና የካፋ ቁርኚት ከአትዮጵያ አልፎ ዓለም ያወቀው በታሪክ ፅሁፎች ብቻ ሳይሆን በአርክኦሎጂ ሳይንስም ድጋፍ ያለዉ በመሆኑ እዉነቱ ቢፈርጥ መልካም ነበር። ስለካፋና የካፋ ነገስታት ተነስቶ በዘመኑ ወደ ካፋ ሲጎርፍ ለነበረዉ ንግድ አንደኛዉና ታላቁ ምክንያት የቡና በካፋ መገኘት መሆኑ ሳይጠቀስ ሊታለፍ አይገባም:: ከዝያም አልፎ ለጅማ አድገት በወቅቱ ከነበሩት ዋንኛ ምክንያቶች አንዱ በንጉሥ አባ ጅፋርና ከርሳቸዉም ቀድመዉ በጅማ አካባቢ በነበሩት የኦሮሞ ባላባቶች ከካፋ ከሚጫነዉ ቡናና ቂመማ ቂመምን ከመሳሰሉ የሸቀጥ ንግዶች የሚሰበሰበዉ የቀረጥ ገቢ አንደነበር በታሪክ መረጃዎች የተደገፈ አዉነት ነው:: ስለዚህ አኛ ጅማን ያለማነዉ የካፋ ክፍለሀገር ዋና ከተማ በነበረችበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከካፋ ነገስታት ዘመን ጀምሮ ነዉ::

ማጠቃለያ::
ደስታችንና ቂሬታችን አንዳለ ሆኖ የክቡር ጠ /ሚ መምጣት ለካፋ ሕዝብ በብዙ መልኩ ፋይዳ ያለው ነበርና ምስጋና ይገባቸዋል:: ሌላዉ ቢቀር መምጣታቸዉ የህዝባችንን ጥያቄዎች ለማስመለስ አጅግ ተጠናቅረንና ተግተንመስራትናመቀጠልአንዳለብን አስታውሶናል::

የካፋ ህዝብ የህልዉና ትግል አሁንም በአዲስ ዓመት በአዲስና በተጠናከረ መልኩ ሰላማውነትና ስብዕና በተመላበት መልኩ መቀጠል አለበት:: በከፍተኛ በደልና የፍትህ መጔደል ላይ ተመርኩዘው የተነሱ የካፋ ህዝብ ጥያቄዎች ፍትሃዊ መልስ አስክያገኙ ድረስ ትግሉን መቀጠል ግድ ይላል:: ሳንታክትና ተስፋ ሳንቆርጥ ከተጋን በተለይ ዛሬ አንዳሳየነዉ በአንድ ድምፅ በአንድነት መጔዝ ከቻልን ከግባችን አንደምንደርስ አኒጠራጠርም::

ፍትህ ለካፋ ህዝብ::
ኢትዮጵያ ለዘላዓለም ትኑር::

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: