Leave a comment

የክቡር ጠ/ሚ አቢይ አሕመድ የቦንጋ ጉብኝት ውጤት::


ፋንታዬ መኮ
መስከረም 5 ቀን 2012 ዓም
September 16, 2019

የክቡር ጠ/ሚ አቢይ አሕመድ የቦንጋ ጉብኝት ውጤት::

70672943_388282588772278_3114441907732742144_nምሥክርነታቸውን እንደሰጡት እንኳን ከሰው ልጅ ከራሱ አልፎ ከተፈጥሮም ጋር ተስማምቶ መኖር የሚችል ብልህ የሠለጠነና አስተዋይ ህዝብ ስለሆነ እንደ አመጣጣቸው አክብሮ ተቀብሎ በጉጉት የጠበቀውን የአስተዳደራዊ ጉዳይ እመርቂ መልስ ባያገኝም በትእግሥት ለመጠበቅ ወስኖ እንዳቅሙ አስትናግዶ በሰላም ወደ መጡበት ሸኝቷቸዋል:: ለዚህ ተግባር አስተባባሪዎችም ሆኑ መላውን ታዳሚ (ማህበረሰቡን) ባጠቃላይ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ህብረት (ደምኢህህ) ስም ላመሰግን እወዳለሁ:: እግዚአብሔር ይስጥልን ደስ ብሎናል::

በመቀጠል ጉብኝቱ ያልተጠበቀና ለዝግጅት እንኳ በቂ ግዜ ሳይሰጥ በሁለትና ሶስት ቀናት ውስጥ ይፋ መደረጉ የማንኛውንም ሚድያ ቀጥታ ሽፋን ያላገኘ የራሱ የደቡብ ሚድያን ጨምሮ ሲሆን ለማሕበራዊ ሚድያ ምሥጋና ይግባው ብዙም ባይሆን በFB በማስተጋባት ድምፅ አሰምተውለታል:: ጉብኝቱ በመግቢያ ንግግራችው እንዱገለፁት ወንድም የሆነውን ካፈቾ ለመጠየቅ በጎ ፈቃድ የመነጨ ከሆነ እሰየው:: ጀግናው የካፋ ጎርማሾ ሐዋሳ ላይ በደህዴን ተጠርቶ በክልል ጉዳይ አልደራደርም ብሎ አቋም ወስዶ ስብሰባውን ረግጦ በመውጣት ቅሬታውን በሰላማዊ መንገድ ገልፆ ወደ ቀየው መመለሱ ባለሥልጣናቱን አስበርጎት የሳቸው ጣልቃ ገብነት ክልል የመሆን ዓላማውን የሚያስቀይረው መስሏቸው ከሆነ ስህተት ይመስለኛል:: ያም ሆነ ይህ የጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ የመስከረም 4 ቀን 2012 ዓም የቦንጋ ጉብኝት ፍሬ አልባ አልነበረም ሆስፒታሉን ጎብኝተው በተመለሱ 24 ሰዓት ውስጥ የህክምና ልዑካን ቡድን ቦንጋ መግባቱ የመጀመሪያ መልካም እርምጃ ነው:: ነገር ግን አንገብጋቢው የክልል ጥያቄ እስካልተመለሰ ድረስ መዘናጋት አይኖርብንም::

ይህ ህዝብ ስለ እራሱ ምንንትና ማንነት ለመናገር በነራስ ወልደጊዮርጊስና ከዚያም በኃላ ካፋን እንዲያስተዳድሩ በየጊዜው በማዕከላዊ መንግሥት በተሾሙ መኳንንቶች ምኒሊክ “ለካፋ ህዝብ አትራራለት:: አጥብቀህ ግዛው:: ገብር ብለው አሻፈረኝ ብሎ ወታደሬን አስጨርሷል:: መሬቱን ነጥቀህ ገባር/ጭሰኛ አድርገው:: ሚስቱንና ልጆቹን ለወታደሮቼ እንዲገዙ አድርጋቸው:: ቤትና ንብረቱን አቃጥል ወዘተ ብለው የሰጡትን መመሪያ ተግባራዊ በማድረጋቸው መስከረም 4 ቀን 2012 ዓም ቦንጋ ላይ ያደረጉት ንግግር ከወረራው በፊት ጀግና የነበረው ህዝብ ሥነ ልቦናዊ ጫና በተደጋጋሚ እየደረሰበት ማንነቱን ክዶ ስሙን ሳይቀር ቀይሮ ይህን የመሰለ ጀግናና አኩሪ ታሪክ ያለው ወጣት ትውልድ ከፈቾ ነኝ ብሎ ደፍሮ ታሪኩን ከመናገር ይልቅ የሌላ ተለጣፊ ሆኖ የራሱን ታሪክ ጠንቅቆ ባለማወቁና ወላጆችም ከባድ ተፅእኖ እየተደረገባቸው ማንነታቸውን ለማስተላለፍ ሳይችሉ ቀርተዋል::

ሆኖም ከ2012 ዓም የጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ ጉብኝት አንድ ትልቅ ትርፍ ካፈቾ አትርፏል:: ካፈቾ አፉን የተሸበበ ይመስል ስለ ካፋ ማንነት ስለሃገሩ ስለ ጀግንነቱ በአስተዳደራዊ መዋቅር የሰለጠነ እንደነበረ መናገር እየከበደው “ታሪክና ሃገር ያለኝ ካፈቾ ነኝ” ለማለት የማይደፍርበት የነበረውን የራሱን ጀግንነት ታላቅነት ራስን በራስ የመምራት ብቃት የዲሞክራሲ ባህል ለካፈቾ አዲስ እንዳልሆነ ወዘተ ዘርዝረውና ተንትነው ስለነገሩትና ማንነቱን ከሚያከብረው የለውጥ እራማጅ አንደበት ስለሰማ ትውልዱ አንብቦ ከተረዳው በላይ ሀቁን ስላስቀመጡለትና ስለካፋ የተሳሳተ አመለካከት ላላቸው ብሔረሰቦችና ህዝቦች ማነታችንን ካፋ ቡናን ለዓለም ከማበርከቱም አልፎ በዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ቀደምት መሆኑን ለመላው ዓለም ምሥክርነትዎን ስለሰጡ ታሪክ በዚህ ሥራዎ ይመዘግቦታል በካፋ ህዝብ ልብም ለትውልድ ተቀርፆ ይኖራል::

ከላይ ከተጠቀሰው ትርፍ ውጭ የጉብኝቱ ውጤት ለሴረኞች ኪሳራን ለከፈቾ ድልን አስመዝግቧል::

– ጉብኝቱና ድንገተኛ ቢሆንም ካፈቾ አንድነቱን አስመስክሯል
– የተቻለውን ሁሉ ተጠቅሞ አቀባበል አድርጏል
– ጥያቄውን በሰላማዊና በሰልጠነ መንገድ አቅርቦ መልስ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል
– ያለ እንድ ኮሽታ ወደመጡበት በሰላም ልዑካኑን ሸኝቷል::

ጥቂት ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የጋዜጠኝነት ሙያ ባይኖረኝም

(ሀ) አጠቃላይ ጉብኝቱን አስመልክተው መግልጫ ቢስጡ ሌላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰብ እርስዎ እንዳሉት ከካፈቾ የሚማረው ለምሳሌ የሰው ህይወት ሀብትና ንብረት ሳይወድም በስለጠነ ሰላማዊ መንገድ ትግል ማራመድ መቻሉን

(ለ) ካፋ ለዓለም የቡና መገኛ ብቻ ሳይሆን የዲሞክራሲን ቀደምት አራማጅ ሆኖ ለብዙ ዘመን ሀገር መምራቱን ሌላም ሌላም

በመጨረሻም ተበደልኩ ፍትህ ፈልጋልሁ ለሚል ህዝብ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ወቅታዊና ተገቢም ነው:: ይህ ጊዜ ገንዘብና ጉልበት የባከነበት ጉብኝት የሚድያ ሽፋን ቢሰጠው መልካም ነበር:: ክልል መሆን ይጥቀመውም አይጥቀመውም ህዝቡ ለይቶ ያውቃል:: የቡና ባለቤትነትን ጥያቄ መመለስ ታሪክ ከማገላበጥ ውጭ ጥናት አይፈልግም ሌላ እጀንዳ ከሌለ በስተቀር:: የሙዚየሙም ጉዳይ አፋጣኝ ምላሽ ያሻዋል ንብረት እየባከነ ስለሆነ:: የቡና ፓርክ መግንባት ያለበት ካፋ እንጂ አዲስ አበባ መሆን አይገባውም:: ክልል መሆን ጥቅም ካላመጣ ለሲዳማ ለምን ተፈቀደ? ካፋ ሀብታም ነው ትግራይ ክልል በመሆኑ ምን ተጎዳ? ጋምቤላም በመሰረታዊ ልማት ከካፋ የላቀ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ግልፅ ነው:: የጊዜ ጉዳይ ሆነና ፊተኞች ኃለኞች እንዲሆኑ ተደርገዋል::

ሕገ መንግሥቱ የሰጠን መብት ላይ አንደራደርም
የቡና መገኛ በየትኛውም መስፈርት ካፋ እንጂ ሌላ ቦታ ወይም በጥቅሉ ምዕራብ አከባቢ ሊባል አይገባም::

ፋንታዬ መኮ
መስከረም 5 ቀን 2012 ዓም
September 16, 2019
ካፋ ሚድያ Kaffamedia

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: