Uncategorized

በካፋ ሕዝብ ማለትም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አከባቢ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ደባ!!


በካፋ ሕዝብ ማለትም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አከባቢ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ደባ ሕዝቡን ለማፈን ቀና እንዳይል ራሱን በራሱ እንዳያስተዳድር የመሬቱና የሃብቱ ባሌቤት እንዳይሆን ሁሌም የበይ ተመልካች ሆኖ እንዲኖር ትልቅ የሴራ ድግስ የትዘጋጀለት ይመስላል:: ይህንንም ሴራ እውን ለማድረግ በደንብ ታስቦና ታቅዶ በቴያትር መልክ ቀርቦ የተሳካ ስራ እየተሰራ ይገኛል:: ይህ ሴራ እርምጃውን በደንብ ጠብቆ ከላይ ወደ ታች […]

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ሕብረት (ደምኢህሕ) ድርጅት በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ሻተራሻ አዳራሽ ለካፋ ህዝብ ስለድርጅቱ አጠቃላይ ገለጻና ውይይት አደረጉ፣


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ሕብረት (ደምኢህሕ) ድርጅት በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ሻተራሻ አዳራሽ ለካፋ ህዝብ ስለድርጅቱ አጠቃላይ ገለጻና ውይይት አደረጉ፣ በውይይቱ ላይ የተገኙት ተሳታፊዎችም በውይይቱ በጣም ደስተኛ መሆናቸውንና ድርጅቱም ለአካባቢው እጅግ አስፈላግ መሆኑንም ገልጸዋል::  

ቀጥታ መልዕክት ለካፋ ዞን አስተዳዳሪና ለአስተዳዳሪው ጀሌዎች በሙሉ::


ማንም ሰው በሰውነቱ ክቡር ነው፣ የሰውን ልጅ የማንጓጠጥም ሆነ የማሳነስ አላማም ሆነ ፍላጎትም የለንም፣ ምክንያቱም የሰው ልጅ ያጠፋል ደግሞ ይታረማል። ነገር ግን የሰው ልጅ እየተነገረው እና እየተመከረ መታረምና መስተካከል ካልቻለ ምን ማድረግ ይቻላል? በተለይም ስልጣንን ተገን በማድረግ በህዝብ ላይ እኩይ ተግባርን ሲፈጽሙና  ለዚህች ሃገር በቀናነት እየታገሉና እየሰሩ ባሉት ሰዎች ላይ በሚያደርጉት አላስፈላጊና ኢሰብዓዊ በሆነ ድርጊት […]

የተለያዬ አጀንዳ እያመጣቹችሁ ህዝቡን እርስ በእርስ ለማቃረን ባትሞክሩ ይሻላችኋል!!!!


አማራ ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን):  አማራ ብሄራዊ ንቅናቄን እንደ ድርጅት አክብረዋለሁ ማንኛውም ማህበረሰብ በመሰለው መልክ መደራጀት ይችላል ለህዝቤ ይጠቅማል እስካለ ድረስ፣ ነገር ግን እያንዳንዱ ድርጅት ስቋቋም የራሱ የሆነ ዓላማና ራዕይ ያለው ነው፣ ስለሆነም እኔም ሆንኩ ለሎች ህዝቦች እንደሚያውቁት አብን የተቋቋመው ለአማራ ህዝብ መብት ብሎ ነው፣ ስለዚህ ዋነኛ ዓላማው የአማራን ህዝብ ማደራጀትና ለአማራ ህዝብ መብት መቆም ነው፣ ታዲያ […]

እውነት መንግስት ከማን ጎን ነው ያለው? እውነቱን እንነጋገር!!


  እውነት መንግስት ከማን ጎን ነው ያለው? እውነቱን እንነጋገር!! እስከም መቼ ዝምታ እስከ መቼ ባርነት? ወይስ አሁንም ስለኛ አልገባቸውም? እውነት ዛሬም መንግስት እንደትላንቱ በአፌሙዝ አፍኖ ሊገዛን እየሞከረ ነው? ታዲያ ለምን ኮማንድ ፖስት ደቡብ ምዕራብ ላይ? ደቡብ ምዕራብ ላይ የትኛው ማህበረሰብ ነው ለሃገር አስጊዎች ናቸው ተብለው የተፈሩት? እስቲ ንገሩኝ? የካፋ ህዝብ አይደለም እንዴ ማንነቴንና ታርኬን  ተነጥቄለሁ […]

ደቡብ ምዕራብን ኮማንድ ፖስቱ ተቆጣጥሮታል:: አብን ቢሮ በሚዛን ከተማ ከፍቷል::


Kaffamedia ደቡብ ምዕራብን ኮማንድ ፖስቱ ተቆጣጥሮታል:: አብን ቢሮ በሚዛን ከተማ ከፍቷል:: ምነው ሁሉም የራሱን ማንም አይድረስብኝ ብሎ ሸሽጎና ሰሲቶ የግሉ ካደረገ በሗላ የሚስኪኑን የየዋሁን የካፋን የሸካን የቤንችንና የማጂን አከባቢ እንደ ሥጋ ቅርጫ ለመቀራመት የሚሯሯጠው? የገረመኝ የመንግሥት በፀጥታ ስም ኮማንድ ፖስት እያለ የክርስትና ስም እየሰጠ ሰላማዊዉን አከባቢ የጦር ቀጠና ይመስል በወታደርና በክላሽ ጋጋታ ውዥምብር መፍጠሩ ነው:: […]

የካፋ አከባቢ ክልልነት ጥያቄ የፋሽን ጉዳይ ወይስ መሰረታዊነት ያለው?


Samuel Tamiru Amade የወቅቱ የክልልነት ጥያቄዎች በተለይም ቀድሞ ደቡብ ተብሎ በሚጠራው የአገራችን አከባቢ መሰረታዊ በሆነ መልኩ በአብዛኛው እየተጠየቀ ያለ ሲሆን ሁሉም አከባቢዎች የየራሳቸው መነሻና ምክንያት እንዳላቸው እውን ነው፡፡ ለነዚህም ጥያቄዎች መንግስት እየሰጠ ያለው ትኩረትና ምላሽ ከህዝቡ ጥያቄ አንፃር ምን ደረጃ ላይ እንዳለና ምን ያህል ህጋዊነትን የተከተለ እንደሆነ ለቀባሪ ማርዳት ነው የሚሆነው፡፡ ከእነዚህ የክልልነት ጥያቄዎች መካከል […]