Leave a comment

የኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ በደሎችን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለማስቀረት


Menwuyelet Melaku

Menwuyelet Melaku

ኑሯቸውን በአሜሪካ ያደረጉትና የሕዝባቸው መበደል ያንገበገባቸው የደቡብ ምዕራብ ፈርጦች አቶ ተስፋዬ ወ/ሚካኤል፡ ዶ/ር አቻሜ ሻና፡ አቶ ጎዲ ባይከዳኝ፡ አቶ ብርሀኑ ወ/ሰንበት፡ ወ/ሮ ፋንታዬ ገብሬ፡ አቶ አማኑኤል ካርሎ፡ አቶ ያሮን ቆጭቶ የዛሬ አራት ዓመት ገደማ በሰሜን አሜሪካ ያቋቋሙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ሕብረት (ደምኢሕሕ) በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አስፈላጊ ፎርማሊቲዎችን በሟሟላት ተመዝግቧል፡፡
ዋነኛው መሠረቱን በካፋ፡ ሸካ፡ ቤንች ማጅ ውስጥ ያደረገው ይህ ፓርቲ የተቋቋመበት ዋንኛው ዓላማ የቀጠናው ሕዝብ ላለፉት በርካታ ዓመታት የደረሰበት የኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ በደሎችን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለማስቀረትና ሕዝቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥ ነው፡፡
የምርጫ ቦርድ ምዝገባውን የጨረሰው ይሄው ፓርቲ ለመጭው የሰኔ 2012 ሀገራዊ ምርጫ ዝግጂቱን ጀምሯል፡፡ ለዚሁ ይረዳው ዘንድ አጠቃላይ የፓርቲውን ምንነትና የተመሠረተበት ዓላማ ብሎም ቀጣይ አቅጣጫ ለቀጠናው ሕዝብ አቅርቦ ማወያየት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት እሁድ መጋቢት 15/2011 ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ በሻተራሻ ገሮ ገብሬ አዳራሽ እንድትገኙለት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ያጣነው ስለ እኛ በአደባባይ የሚሞግት አካል ነውና በነቂስ መጥተን በውይይቱ እንሳተፍ፡፡ የካፋ ጉርማሾ የጀመረው ትግል በሌሎች መሠል ማህበራትና ፓርቲዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

ጊዜው አሁን ነው!

Advertisements
Leave a comment

“Majority rule, minority right” የሚባል ነገር አለ፡፡ !!


Menwuyelet Melaku

Menwuyelet Melaku

By: Menwuyelet Melaku

ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያስቸገረው ጉዳይ ቢኖር ሕገወጥነት ፡ አለመደማመጥ፡ የሕግ የበላይነት ያለመከበር፡ ሰብአዊነትን ማጣት የመሳሰሉት ናቸው፡፡
በይበልጥ እየጎዱን ያሉት ያለመደማመጥ /በራስ መንገድ ማድመጥ/ እና የሕግ የበላይነት መታጣት ሲሆኑ እነዚህ ኩነቶች በይበልጥ እየተስተዋሉ የሚገኙት ልሂቃን ተብለው በሚፈረጁና ከተሜ በሆኑት መሆኑ ሁኔታውን እንዲከፋ ያደርጉታል፡፡
ማንኛውም አካል በሰከነና ሕግን በጠበቀ መልኩ ጥያቄዎችን መጠየቅ ይችላል፡፡ ጥያቄዎቹ ተገቢም ይሁን ተገቢ ላይሆኑ ይችላሉ ግን መልስ የሚያገኙት በሀገሪቱ ብሎም በአለም አቀፍ ሕግጋት መሠረት ነውና ምላሹ ምንም ይሁን ምን ሕጋዊ እስከሆነ ድረስ የመቀበል ግዴታ በጠያቂውም ሆነ በሌላው የሚመለከተው አካል ዘንድ ይኖራል፡፡
ምላሾች መቼም ቢሆን ሁለትና ከዛ በላይ የሆኑ አካላትን አስደስተው አያውቁም እንዲያስደስቱም አይጠበቅም፡፡ ሽንፈትን በፀጋ መቀበል ከአንድ የሰለጠነ ማህበረሰብ የሚጠበቅ ይሆናል፡፡
አንድ ሕገወጥ ተግባርን ለመመከት ሌላ ሕገወጥ አካሄድን መጠቀም ማለት ከእጅ አይሻል ዶማነትን ያስከትላል፡፡ ሕገወጥ ተግባር በሕጋዊ አካሄድ ብቻ ነው ሊስተካከል የሚገባው፡፡ የብሽሽቅ ፖለቲካ ለማናችንም አይበጅም፡፡ ለኢትዮጵያ ካሰብን ሰከን ማለት ይበጀናል፡፡
ሌላውና አስቸጋሪው ጉዳይ የሚሆነው መንግስት ሕግን ለማስከበር ያለው ቁርጠኝነት የደከመ መሆኑ ነው፡፡ በተገቢው ቦታና ጊዜ ሕግን ማስከበር የግድ አስፈላጊ ነው ልጅ እንኳን ሲያጠፋ ካልተቀጣ ጥፋቱ ትክክለኛ ተግባር እየመሠለው ደጋግሞ ያጠፋል፡፡ ወይም አንድ የዕግር ኳስ ዳኛ ጥፋቶች ሲፈጠሩ በቃል ተግሳፅ በቢጫና ቀይ የማይቀጣ ከሆነ ከዚህም ከዚያም ወገን ጥፋቶች እየተፈፀሙ ጨዋታው በአግባቡ እንዳይሄድ ያደርጋል፡፡ ይባስ ብሎም የተጨዋቾቹ ተግባር ወደ ደጋፊው ተዛውሮ መላው ስታዲየም ይበጠበጣል፡፡
አንድ መንግስት ዴሞክራሲያዊ የሚያሰኘው የራሱ የሆኑ የተለዩ ባህርያት አሉ፡፡ ሕግን አለማስከበር ግን በፍፁም የዴሞክራሲያዊ መንግስት መገለጫ ሊሆን አይችልም፡፡ አይደለምም፡፡ የምንወስደው እርምጃ በሁሉም ቦታዎችና ጊዜያት ተመሣሣይነት ያላቸውና ወጥ ከሆኑ በፍፁም ለትችት መፍራት የለብንም፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ችግር አንድ ግለሰብ ወደ ስልጣን ሲወጣ ዘሩንም አብሮ ይዞ ስለሚወጣ ነው፡፡ በዚህ ረገድ እስካሁንም ሀገራችንን እየበጠበጡ ያሉት በቁጥር በርከት ያሉ ብሄረሰቦች ናቸው በዋነኛነትም ትግሬ፡ አማራና ኦሮሞ ሲሆኑ እነዚህን ለመቀላቀል እየተንደረደረ ያለው ሲዳማም ለኢትዮጵያ ቀጣይ ስጋት ይሆናል፡፡
አነዚህ ብሄሮች ኢትዮጵያን ተፈራርቀው መርተዋል እየመሩም ነው፡፡ በአንዳቸውም ግዜ ግን ኢትዮጵያ ከድህነት አረንቋ ወጥታ አታቅም፡፡ ይህንን አሳፋሪ ሪከርድ ይዘው የእኔ ዘር ያንተ ዘር ሲሉ ጥቂት አለማፈራቸው በጣም ያሳዝናል፡፡ ሌሎች በቁጥር ያነሱ ብሄረሰቦች ግን ማንም ዞር ብሎ አያያቸውም ድምፃቸውም አይሰማም ነገር ግን በግጭቶች መሀል ሲጎዱ ይስተዋላል፡፡ ወትሮስ የዝሆኖቹ ጥል ጉዳቱ ለሳሩ ነው ይባል የለ?
እስኪ ከተራ መበሻሸቅና የዘር ፖለቲካ ወጥታችሁ ሀገሪቷን ከሌሎች ሀገራት ተርታ አሰልፏት፡፡ ረሀብ ሞት ስደትና መፈናቀልን አስቁሙ የዛኔ ስለእናንተ ዘር ትልቅነት እኛ እንመሠክራለን፡፡
አንድ ነገር ልብ በሉ
ሀገራችንን እግዚአብሔር ይጠብቃት ፡፡ አበቃሁ፡፡

Leave a comment

ጉዞአችን ወደፍት ትግላችን ለጋራ እድገትና ለጋራ ለውጥ ይሁን።


ውድ የተከበራቹ የካፋ ሸካና ቤንቺ ማጂ ህዝቦች፣ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በጥንቃቄ እና በማስተዋል የተገኘውን አጋጣሚ ሊንጠቀምበት የምንችልበት ወቅት ላይ ነን፣ ስለዚህ አሁን እጅ ለእጅ ተያይዘን የራሳችንን መብት ልናስከብርና ክልላችንን ልናደራጅ ይገባል፣ አላማችን የሁላችንም አንድ እና አንድ ነው፣ ለዘመናት የተበደልን እና የተጨቆንን እንደመሆናችን መጠን ዛሬ መብታችንን አስከብረን ማንነታችንን አስጠብቀን ያለንን ሀብቶቻችንን በአግባቡ መጠቀም የምንችልበት ራሳችንን በራሳችን ማስተዳደር እንደሆነ ለመግለጽ እወዳለሁ፣ ስለዚህ ውድ ህዝቦቼ አባቶች እናቶች ወጣቶች ምሁራኖች በአካባቢያችን ጉዳይ ይመለከተኛል የምትሉ ሁሉ አሁን ሰዓቱና ጊዜው ስለሆነ በመተባበር በመመካከር በበሳል አካሄድ ጥበብና ብልሃት በሞላበት ህደት በጋራ እንዲንቆምና ይሄንን የባርነት ቀንበረ ለአንደና ለመጨረሻ ጊዜ በማስወገድ ለመጭው ትውልድ የድርሻችንን በመወጣት አሻራችንን ልናስቀምጥ ይገባል። ውድ የካፋ ሸካና ቤንቺ ማጂ ህዝቦች ያለን የቴጥሮ ሃብቶቻችን እንኳን ሌኛ ለሃገራችን ኢትዮጵያ አልፎም ለዓለም ተርፎዋል። ግን እኛ እስከዛሬ ድረስ የበይ ተመልካቾች ነበርን። አሁን ግን በቃን። ጉዞአችን ወደፍት ትግላችን ለጋራ እድገትና ለጋራ ለውጥ ይሁን።

Leave a comment

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ በፅናት ይታገል!!!!


ከአጎ አሺሎ

38023561_282102385890705_1514103197361242112_nበኢትዮጵያ ታሪክ በራሱ መንግስታዊ አወቃቀር የተደራጀ በባህል በሀይማኖት ሳይለያይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፍ ትልቅ ሚና የነበረው ይህ ታላቅ ሕዝብ በወያኔ /ኢህአዴግ አገዛዝ በሁለንተናዊ መንገድ ከፍተኛ ቀውስ የደረሰበት መሆኑ ይታወቃል ።
ይሁን እንጂ ገና ከ1983 አም ጀምሮ ሕልናውን ለመጠበቅ በፓለቲካ ፖርቲ ተደራጅቶ በኢትዮጵያ ውስጥ መንቀሳቀስ ብሞከርም የሕዝቡን የመደራጀት መብት በማፈን ብዙ የክልሉ ተወላጆች ከአገር እንዲሰደዱና ለተለያየ እንግልት ተዳረገዋል
በየትኛውም አገር እና አምባገነኖች ስረዐት የሕዝብን መብት ለማፈን አቅም እንደማይኖራቸው የሚታወቅ ሲሆን ጀግና የምዕራብ ኢትዮጵያ አከባቢ ተወላጆች በአገረ አሜርካ እንደ እ. ኤ.አ በ2016 የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረት
አቋቁመው ከፍተኛ ትግል ሲያደርጉ ቆይቷል። በአገራችን በዶክተር አብይ በተጀመረው ለውጥ በተለያዩ አገር የሚንቀሳቀሱ ፖርቲዎች አገር ውስጥ ገብተው እንድታገሉ በተጋበዙት መሠረት የደምኢሕህ ፖርቲ አባልና አመራር ተጋብዘው አገር ውስጥ መግባቱ ይታወቃል ።
ለስላም ለዴሞክራሲ ስርዐት ግንባታ ትላልቅና ወሳኝ አጀንዳዎችን ይዞ የሚንቀሳቀስ ፖርቲ በመሆኑ የፓርቲው አመራሮች አገር ውስጥ ገብተው በዋና ዋና የክልሉ ከተሞች ሕዝቡን ካወያዮ በኃላ የፓርቲውን አወቃቀር እና አደረጃጀት በመተከል ስራ ላይ የተጠመዱ በመሆኑ በአገሪቱ ሕግ መሠረት ከማንኛውም ፖለቲካ ፖርቲ ቀድሞ ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና ማግኘታቸው ይታወቃል ።
ፓርቲው ከክልሉ በተጨማሪ ተወላጆች ባሉበት ቦታ መዋቅሩን እያደራጀ ይገኛል ።በዚሁ መሠረት በአዲስአበባ የሚገኝ የቅርንጫፍ ፅ/ቤት ቀጣይና ተከታታይነት ያለው ግኑኘት እያደረጉ እና በቀጣይ የሚኖሩ ስራዎችንና በተለይ በ2012 የሚካሄደው ምርጫን እና አጠቃላይ የፓርቲው ፕሮግራሞችን ባካተተ መልኩ የምርጫ ማንፈስቶ አዘጋጅቶ ከተወያየ በኃላ በፓርቲው ጉባኤ አፀድቆ ወደ ከሕዝብ ጋሪ ለመወያየት ዕቅድ ላይ ይገኛል።
የተከበራችሁ በክልል ከክልሉ ውጭ እና ከአገር ውጭ የምትኖሩ አባላት ደጋፊዎች እና ሕዝባችን በክልላችን የምናደርገው ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፍትህ ለማረጋገጥ በመሆኑ የተሻለ ስርዐት እና ሰላም ለማስፈን የሁሉንም ድርሻ የሚጠይቅ እንደሆነ ፓርቲያችን ደምኢሕህ ስለሚያሚን ሁሉም የባለድርሻ አካል ከጎኑ እንዲቀም ጥሪውን ያቀርባል ።

“የተደራጀ ሕዝባዊ ትግል ለዴሞክራሲዊ ስረዐት!”

2 Comments

ሰሚ ያጣው እና ባለቤት አልባው ህዝብ!!


By: Coffee Kaffa

መንግስት የማያቀው የደቡብ ምዕራብህዝብ!!
ቦንጋ፣ ሚዛን፣ ቴፒ….

– በዚህ ቀጠና እንደትላንቱ ሁሉ ዛሬም፤ በፈጣሪ ዘንድ ክብር ያላት ነብስ ያለርህራሄ በግፍ የረገፈች ነው። በካፋ ዴቻ፣ በቴፒ፣ እና በሌሎችም።
– በሶስቱም ዞኖች ላይ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች፤ ዛሬም እንደትላንቱ ከማያቀንእና ከማይወክለን ደኢህዴን ከሚባል ድርጅት ጋር መሞዳመዱን ቀጥለውበታል።

እነዚህን ሁሉ የህዝቡን ብሶት እና ለቅሶ ወደጎን በመተው፤ የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግስት ተገቢውን መልስ ከመስጠት ይልቅ፤ ቸልታን መርጠው በቁጥር ደረጃ ብዙ ለሆኑ ህዝቦች ብቻ መቆማቸውን ባገኙት መድረክ ላይ ያሳዩን ነው።

ለዚህ ማሳያ ደግሞ ባሳለፍነው ሳምንት፤ ጠቅላይ ሚኒስተራችን በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርበው ከሰጡት መግለጫዎች ይህን ማየት በቂ ነው።
” ‘የደቡብ ክልል’ ዞኖችን የክልል ጥያቄ መመለስ መፍትሔ አይሆንም። ሕገ መንግስታዊ ጥያቄ ቢሆንም መፍትሔ አይደለም። ስለሆነ የወሰንና የአስተዳደር ጉዳዮች ኮሚሽን በሚያቀርበው ጥናት መሰረት መልስ ያገኛል። በጥናቱ ኢትዮጵያ 20 ክልሎች ያስፈልጋታል ከተባለ በዚያ መልክ የሚታይ ይሆናል። ከዚህ ውጭ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ጥያቄ ላቀረቡ 10 ዞኖች መልስ መስጠት አይቻልም።”

በሌላ በኩል ደግሞ በዛሬው እለት የሰላም ሚኒስተሯ የሰጡትን መግለጫ እንይ፤ “ከህብረተሰቡ ጋር በተቀናጀ ተግባር 1 ሚሊየን 20 ሺህ ያህል ዜጎችን ወደ ቀያቸው መመለስ መቻሉን በእምባ የታጀበ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አሁን ቁምነገሩ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው ለምን ተመለሱ አይደለም። እሰይ እንኳን ተመለሱ ጥሩ ተግባር ነው።

ግን የመንግስት ረፓርት የሚቀርበው፤ በጎ ተግባሩን እና ለመመለስ የሚመቻቸውን ብቻ ነው? ይህማ እኮ ድሮ በህወሓት ዘመንም ነበር።

ሰላም በሌለባት አገር የሰላም ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የተቋማቸውን የ6 ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ለህዝብ ተወካች ምክር ቤት ለውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ስያቀርቡ ሶፍት ከእጃቸው አልተለየም ነበር፡፡

ስለዚህ ወገኔ ሆይ፤ ቦንጋ፣ ሚዛን፣ ቴፒ እና አካባቢዋ ያላችሁ፤ ለራሳችን ስንል ከትላንቱ በይበልጥ ልንደራጅ፣ ልንመካከር ይገባል።

1 Comment

ምነውሳ መነፅሩ ሁሉ “የማንነት” ብቻ ሆነ?


by:- Yaroon Kochito

Yaroon Kochito

Yaroon Kochito

አገራችን ውስጥ አንድ አካባቢ ግጭት በተከሰተ ቁጥር ከዘር ጋር ማገናኘት ቀላልና ብዙ ማሰብና ስራ የማይጠይቅ ትኩረት ማግኛ ዘዴ ከሆነ ውሎ አድሯል። ይህ ደግሞ እንደ አገር አይደለም ሰው እንደተሰኘ ክቡር ፍጡር ወዴት እየወሰደን እንደሆነ ስጋት ውስጥ የሚጥል ነው።
ይህንን ሃሳብ እንድፅፍ ያነሳሳኝ እኔ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ስለማውቀው አካባቢ ኅላፊነት በጎደለው መልኩ በአንዳንድ ሚድያዎች፣ማህበረሰብ ተቋማት አንቀሳቃሾች እና አንድ አንድ ግለሰቦች አማካኝነት እየተነገረ ያለ እውነታን ያልተከተለ ዘገባ ነው።

ዜናውም ከከንባታ አካባቢ ወደ ካፋ ዞን መተው እንዲሰፍሩ የተደረጉ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በማንነታቸው ምክንያት እንዲፈናቀሉ የቱደረጉ አድርጎ የምያሳይ ነው። በነገራችን ላይ ከከንባታ ወደ ካፋ ሲመጡ የተቀበላቸውና አቅፎና ደግፎ ያኖራቸው ከንባታ የቀረው ወገናቸው ሳይሆን የካፋ በተለይ ደግሞ የዴቻ ወረዳ ሕዝብ መሆኑን እዚህ ጋር ልናስተውል ይገባል።
እኔ ወደተረዳሁበት እውነታ ከመሻገሬ በፊት ከትውልድ አገሬ ውጭ መብቴ ተከብሮ እንደሚኖር ዜጋ ብቻ ሳይሆን እንደ ሰው በማንኛውም አካባቢ ለሚፈናቀሉ ፍጡራን-አራዊትም ጭምር- ያለኝን ሃዘን ልገልፅ እወዳለሁ።
ሆኖም የክስተቶችን እውነተኛ መንስኤ ግዜ ወስዶ ለመረዳት መጣር ዘላቂ መፍትሄዎቻቸውንም በጋራ በመፈለግ እንደ አንድ ሕዝብ ወደ ፊት ለመራመድ ያስችለናል የሚል እምነት አለኝ።
ነገሩ ወዲህ ነው:-ከወራቶች በፊት የወገኖቻችን መፈናቀል የተከሰተበት አካባቢ ካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ይባላል። ይህ አካባቢ ደግሞ በደቡብ ምዕራቡ የአገራችን አከባቢ የሚገኝ ዞን ሲሆን በስተደቡብ ምዕራብ ከቤንችና ማጂ ዞን፣ በስተሰሜን ምዕራብ ከሸካ ዞን፣ በስተደቡብ ከደቡብ ኦሞና በስተ ስሜንና ሰሜን ምስራቅ ደግሞ ከጅማ ዞን ጋር ይዋሰናል።
በአካባቢው ከ11 በላይ ብሔሮች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም መሃከል “ሜኒቶች”አንዱ ናቸው። “ጥቃቱም”የተፈፀመው ከወራት በፊት በእነዚሁ ሜኒቶች ነው። ይህ ደግሞ ማንንም እንደ ግለሰብ ወይም ዘር፣ ማህበረሰብ፣ ወዘተ ያነጣጠረ አይደለም፤ በጥላቻ ወይም በበቀል ተነሳሽነት የተደረገም አይደለም፤ ምክንያቱም ” ለሜኒቶች” የኛ የማህበረሰብ ክፍፍል ጉዳያቸው አይደለም፤ እነርሱ የሚፈልጉት ከብት ብቻ ነው።
ሜኒቶች ከብት በማርባት በአጠቃላይ በደቡብ ምዕራቡ የአገራችን አካባቢዎች ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የሚኖሩ ሲሆን ባህላቸውን ከምያውቁት እንደተረዳሁት “ዓለም ላይ ያሉ ከብቶች ሁሉ የእነርሱ ናቸው ብለው የምያምኑ ናቸው። ለጋብቻ ጥሎሽም ብዙ ከብቶች ማቅረብ ስለሚጠበቅባቸው ከብት ወዳለበት አካባቢ ተንቀሳቅሰው ይወስዳሉ፤ሊከላለል የሚመጣ ካለም ይገድላል( ምክንያቱም ከብቶቹ የማንም ይሁኑ የማን ባለሙሉ መብቶቹ እነሱ ናቸውና)።
እንደዚህ አይነት ክስተቶች ደግሞ ለዘመናት የዘለቁና የአካባቢውን ማህበረሰብ ያለ ዘር ልዩነት እየተፈታተነ የሚገኝ ጉዳይ ነው።
ሌላው ሊሰመርበትና ዓዕምሮ ያለው ሁሉ ሊገነዘበው የሚገባ ነገር ቢኖር:- ወገኖች ከከንባታ አካባቢ ወደ ካፋ ሄደው ኑሯቸውን ማድረግ የጀመሩት ገና ትላንት አይደለም። ይልቁንም ለብዙ ዓመታት የዘለቀ እንጂ። ብዙዎች እስከዛሬ በአካባቢው ቤተሰብ መስርተው፣ ሃብት ገንብተው በተለያዩ ተቋማት እንደማንኛውም ነዋሪ ተቀጥረው እየኖሩ ይገኛል፤ ወደ ፊትም ይኖራሉ።
የእነሱ አሰፋፈር “በማንነታቸው ተጠቁ” ፋሽን ከመሆኑ በፊት ዘመናትን የዘለቀ መሆኑን ተረድተን፤ ይልቁንም እየተከሰተ ላለው የጋራ ችግር የጋራ ዘላቂ መፍትሔ መሻቱ እውነተኛ ወገናዊ ስሜት መኖሩን ማሳያ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ።
በዚህ መንፈስ ችግሮችን በጋራ እየተጋፈጡ ከሚገኙ ማህበረሰቦች ውስጥ አንዱን ብቻ ተጎጂ ሌላውን እንደ ጎጂ በማቅረብ ስምን ለማጠልሸት መሞከር የስብዕናችንን ልክ እና ለለውጥ ያለንን የቁርጠኝነት ሚዛን ከማሳየት በዘለለ ምንም አይነት አዎንታዊ ጥቅም እንደማያመጣ ተረድተን በተሻለ ግንዛቤ የተሻለ ስራ እንስራ እላለሁ። የመገናኛ ብዙሃንም ቢሆኑ ከተባራሪ ወሬ በተሻለ መንገድ ቢሰሩ ሃላፊነታቸውን ከመወጣት በላይ የሆነ ተግባር ይከውናሉ የሚል ተስፋ አለኝ።

Leave a comment

ከብሔሩ ምክር ቤት ውሳኔና ከኮሚቴ ጥናት የቱ ነው ህገ መንግስታዊ???


by:- Asaye Alemayehu

ከብሔሩ ምክር ቤት ውሳኔና ከኮሚቴ ጥናት የቱ ነው ህገ መንግስታዊ???
ሰሞኑን ዴኢህዴን የምሰጣቸው መግለጫዎች አስተውሎ ለተመለከተ ሁሉ ግራ የሚያጋባ እየሆነ ነው:: አብዛኛዎቹ መግለጫዎች ከህገ መንግስቱና ከህዝቡ ፍላጎት ጋር እልህ የተጋባ ይመስላል:: እንደምታወቀው ሰሞኑን የተወሰኑት በክልሉ ያሉ ዞኖች ህገ መንግስቱን መሰረት በማድረግ ህጋዊ መብታቸውን በመጠቀም በየጊዜው በህዝቡ ስነሱ የቆዩ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎችን በብሔሩ ምክር ቤት በአብላጫ ድምጽ እንዶውም በሙሉ ድምፅ እያጸደቁ ይገኛሉ:: ለእኔ እንደምገባኝ እና እንደ ካፋ ዞን ሁኔታ እንደማውቀው የዞኑ ምክርቤት ዴኢህዴን እንደምለው ሳይሆን የክልል ጥያቄውን እንደ አጀንዳ የያዘውም ሆነ ውሳኔ ያሳለፈው ዝም ብሎ በቅዥት ሳይሆን የካፋ ህዝብ ቀድሞ የነበረው ታርክ’ላለፉት 28 ዓመታት ብሔረሰቡ ላይ የደረሰውን ታርካዊ’ፖለትካዊ’ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ በደሎችን ወይም ቅሬታዎችን በዝርዝር ካስጠናና ከተወያየ በኋላ እንደሆነ ነው:: ስለዚህ ይህ ህጋዊ ጥያቄን ከህገ መንግስቱ ውጪ ኮሚቴ አዋቅሬ በሳይንሳዊ መንገድ ካላስጠናው ሙቼ እገኛለው ማለት በመጀመሪያ ደረጃ የህጎች ይህም ማለት የድርጅት አቅጣጫን ጨምሮ የበላይ የሆነውን ህገ መንግስት ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም መናድ ሲሆን በሌላ መልኩ በህገ መንግስቱ ላይ በየደረጃው ላለው ምክር ቤቶች የተሰጠውን ስልጣን የመናቅና የህዝብ ተዎካዮችን ያለማክበር ነው:: በተለይ የካፋ ዞን ጥያቄ የፌደራሉንም ሆነ የክልሉን ህገ መንግስት ተከትሎና ሂደቱን ጠብቆ ለክልል ምክር ቤት የቀረበ ስለሆነ መልሱ መሰጠት ያለበት በህገ መንግስቱ መሰረት ክልሉ ምክር ቤት ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝቤ ውሳኔ እንዲያደራጅ በማድረግ እንጂ ህገ መንግስቱን በጣሰ መልኩ ህገ ወጥ ኮሚቴ አደራጅቶ ከዜሮ ጀምሮ በማጥናት አይመስለኝም:: የካፋ ዞን ምክር ቤት ራስን በራስ የማስተዳደር ውሳኔውን ስወስን ሌሎች አጎራባች ህዝቦች ማለትም ዞኖች’ልዩ ወረዳዎችና ወረዳዎች አብሮ መኖር ከፈለጉ ደግሞ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ጭምር ነው:: ስለዚህ ክልሉ ማሰብ ያለበት /እንዶውም ፌደራሉ/ ከካፋ ጋር በፈቃደኝነታቸው አብሮ መኖር የምፈልጉ ህዝቦች ካሉ ማመቻቸት እንጂ በድርጅት አቅጣጫ ጥናቱን ከዜሮ መጀመር አያዋጣም::ዴኢህዴን ይህንን የተለመደውን ህዝቡን የመናቅና ከህዝቡ ፈቃድና ፊላጎት እንድሁም በህገ መንግስቱ ላይ ከተቀመጡ መስፈርቶች ውጪ ዳግም ግዞት ላይ ለማቆየት ከህገ መንግስቱ ውጪ ጥናት ብሎ ኮሚቴ ማቋቋሙ ‘ከዚህ በፊት የአለቆቹን ትዕዛዝ ብቻ ስፈፅሙ የቆዩና አሁን የህዝቦቻቸው መበደል ቆጭቷቸው የህዝቡን ድምፅ መስማትና ለህዝቡ መወገን የጀመሩ የካፋ ተወላጅ አመራሮችን በግምገማ ሰበብ ማሸማቀቅና ከዚህም አልፎ ከተለያዩ ከቦርድ ሰብሳቢነት ቦታዎች በማፈነቀል ተግባሩን ውስጥለውስጥ መተግበር ጀምራል:: በጨማሪም ለተግባራዊነቱ እንዲያመቻቸውም ለእንሱ ተላላክ አመራር እስከሚያገኙ የሚጠብቁ በሚመስል አኳኋን እስካሁን የዞን መዋቅር አመራር ያለመደራጀቱም ለዚህ ማሳያ ልሆን ይችላል::
የተከበራችሁ የካፋ አካባቢ ነዋሪዎች’አመራሮች’ተቆርቋሪዎች’አክትቭስቶች’በሁሉም ወረዳ ያላችሁ የጉርማሾ ኮሚቴዎች እና የተከበራችሁ የካፋ ዞን ምክር ቤት አባላት ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄው በዞን ምክር ቤት በመወሰኑ ረክትን ዝም ያልን ይመስለኛል::አሁን ዝምታው ዳግም ግዞት ውስጥ ልጥለንና እንደምናውቀው ማንነታችንና ታርካችንን በማይመጥን አደረጃጀት እየተጨፈለቅን የተለያዩ ከተሞችን ስናለማ በአንፃሩ እኛ ደግሞ የኋሊት ስንቆረቁዝ መኖራችንን ልያስቀጥለን ነው::እንደ አንድ ግለሰብ እኔ የማስበው፤
በየወረዳው የተዋቀረው የጉርማሾ ካሚቴ ህዝቡን ስብሰባ በመጥራት ኮሚቴውን አስተካክሎ ማዋቀርና ጠንካራ ስራ መስራት መጀመር ይኖርበታል
በየደረጃው ያለው ምክር ቤት ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅሞ የወሰኑት ውሳኔ ተከብሮ ህገ መንግስታዊ ህደቱን ተከትሎ መልስ እንዲሰጥ ድምፃቸውን ማሳማት መጀመር
አክትቭስቶችም ርስበእርሳችን መነቋቆርና ግለሰቦች ላይ አተኩረን መፃፍ ትተን ከእነችግራቸውም ብሆን መኖራቸው ልጠጠቅመን ስለምችል ዋናውንና የካፋ ማንነት ላይ ክልሉ እየሰራ ያለውን ሴራ በማጋለጥና ህዝቡ በአንድነት ድምፁን ማሰማት የምችልበት ሁኔታ ላይ መፃፍ ብቻል
በየደረጃው ያላችሁ የካፋ ተወላጅ የሆናችሁ አመራሮችም ብሆኑ ለህዝባችሁ ጥቅም ስትሉ ማድረግ የምችሉትን በማድረግ ተያይዘን ካልሰራን ዳግም በኮሚቴ ጥናት ሰበብ እኛ ቆስለንና ደምተን አዋሳን አልምተን ውጡ እንደተባልን አሁን ተረኛውን ከተማ ወደ ማልማት ልንገባ በመደመር ጭንብል ልንጨፈለቅ ነው::
ካፋ በኢትዮጵያዊነቱ አይደራደርም በመደመር ሰበብ ግን አይጨፈለቅም

%d bloggers like this: